Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ሳሙኤል 9:25 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

25 ከባማ ኮረ​ብ​ታም ወደ ከተ​ማ​ዪቱ ወረዱ፤ ሳሙ​ኤ​ልም ለሳ​ኦል በሰ​ገ​ነቱ ላይ መኝታ አዘ​ጋ​ጀ​ለት፤ እር​ሱም ተኛ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

25 ከማምለኪያው ኰረብታ ወደ ከተማዪቱ ከወረዱ በኋላ ሳሙኤል በቤቱ ሰገነት ላይ ከሳኦል ጋራ ተነጋገረ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

25 ከማምለኪያው ኰረብታ ወደ ከተማዪቱ ከወረዱ በኋላ ሳሙኤል በቤቱ ሰገነት ላይ ከሳኦል ጋር ተነጋገረ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

25 ከማምለኪያውም ስፍራ ወርደው ወደ ከተማይቱ በገቡ ጊዜ በሳሙኤል ቤት ሰገነት ላይ ለሳኦል አልጋ ተዘጋጀለት፤ እርሱም እዚያ ተኝቶ ዐደረ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

25 ከኮረብታውም መስገጃ ወደ ከተማይቱ ወረዱ፥ ሳሙኤልም ለሳኦል በሰገነቱ ላይ መኝታ አዘጋጀለት፥ እርሱም ተኛ።

参见章节 复制




1 ሳሙኤል 9:25
9 交叉引用  

እን​ዲ​ህም ሆነ፤ ወደ ማታ ጊዜ ዳዊት ከም​ን​ጣፉ ተነሣ፤ በን​ጉ​ሥም ቤት በሰ​ገ​ነት ላይ ተመ​ላ​ለሰ፤ በሰ​ገ​ነ​ቱም ሳለ አን​ዲት ሴት ስት​ታ​ጠብ አየ፤ ሴቲ​ቱም እጅግ የተ​ዋ​በች መልከ መል​ካም ነበ​ረች።


ሕዝ​ቡም ወጥ​ተው አመጡ፤ እያ​ን​ዳ​ን​ዱም በቤቱ ሰገ​ነት ላይ፥ በአ​ደ​ባ​ባ​ዩም ላይ፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤት አደ​ባ​ባይ ላይ፥ በው​ኃ​ውም በር አደ​ባ​ባ​ይና በኤ​ፍ​ሬም በር አደ​ባ​ባይ ላይ ዳስ ሠሩ።


የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ቤቶ​ችና የይ​ሁዳ ነገ​ሥ​ታት ቤቶች እንደ ቶፌት የረ​ከሱ ይሆ​ናሉ፤ እነ​ዚ​ያም በሰ​ገ​ነ​ታ​ቸው ላይ ለሰ​ማይ ሠራ​ዊት ሁሉ ያጠ​ኑ​ባ​ቸው፥ ለሌ​ሎ​ችም አማ​ል​ክት የመ​ጠጥ ቍር​ባን ያፈ​ሰ​ሱ​ባ​ቸው ቤቶች ሁሉ ይፈ​ር​ሳሉ።”


በጨለማ የምነግራችሁን በብርሃን ተናገሩ፤ በጆሮም የምትሰሙትን በሰገነት ላይ ስበኩ።


በሰገነትም ያለ በቤቱ ያለውን ሊወስድ አይውረድ፤


ሰውም ተጨ​ና​ንቆ ነበ​ርና የሚ​ያ​ስ​ገ​ቡ​በት አጡ፤ ወደ ሰገ​ነ​ትም ወጡ፤ ጣራ​ው​ንም አፍ​ር​ሰው ወደ ቤቱ ውስጥ በጌ​ታ​ችን በኢ​የ​ሱስ ፊት ከነ​አ​ል​ጋው አወ​ረ​ዱት።


በማ​ግ​ሥ​ቱም ሄደው ወደ ከተ​ማ​ዪቱ በር ደረሱ፤ ጴጥ​ሮ​ስም በቀ​ትር ጊዜ ሊጸ​ልይ ወደ ሰገ​ነት ወጥቶ ነበር።


“አዲስ ቤት በሠ​ራህ ጊዜ ማንም ከእ​ርሱ ወድቆ በቤ​ትህ ግድያ እን​ዳ​ታ​ደ​ርግ ለሰ​ገ​ነ​ትህ መከታ አድ​ር​ግ​ለት።


ማል​ደ​ውም ተነሡ፤ በነ​ጋም ጊዜ ሳሙ​ኤል ሳኦ​ልን፥ “ከሰ​ገ​ነቱ ላይ ጠርቶ፦ ተነ​ሣና ላሰ​ና​ብ​ትህ” አለው። ሳኦ​ልም ተነሣ፤ እር​ሱና ሳሙ​ኤ​ልም ሁለቱ ወደ ሜዳ ወጡ።


跟着我们:

广告


广告