Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ሳሙኤል 8:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 እን​ዲ​ህም አለ፥ “በእ​ና​ንተ ላይ የሚ​ነ​ግ​ሠው የን​ጉሡ ሥር​ዐት ይህ ነው፤ ወን​ዶች ልጆ​ቻ​ች​ሁን ወስዶ ሰረ​ገላ ነጂ​ዎ​ችና ፈረ​ሰ​ኞች ያደ​ር​ጋ​ቸ​ዋል፤ በሰ​ረ​ገ​ሎ​ችም ፊት ይሮ​ጣሉ፤

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 እንዲህም አለ፤ “በላያችሁ የሚነግሠው ንጉሥ የሚያደርግባችሁ ይህ ነው፤ ወንዶች ልጆቻችሁን ወስዶ ሠረገለኞችና ፈረሰኞች ያደርጋቸዋል፤ በሠረገሎቹም ፊት ይሮጣሉ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 እንዲም አለ፤ “በላያችሁ የሚነግሠው ንጉሥ የሚያደርግባችሁ ይህ ነው፤ ወንዶች ልጆቻችሁን ወስዶ ሠረገለኞችና ፈረሰኞች ያደርጋቸዋል፤ በሠረገሎቹም ፊት ይሮጣሉ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 እንዲህም ሲል ገለጠላቸው፤ “ንጉሣችሁ የሚያደርግባችሁ ነገር ይህ ነው፦ ልጆቻችሁን ወስዶ ሠረገለኞችና ፈረሰኞች ያደርጋቸዋል፤ አንዳንዶቹም በሠረገሎቹም ፊት የሚሮጡ ያደርጋቸዋል፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 እንዲህም አለ፦ በእናንተ ላይ የሚነግሠው የንጉሡ ወግ ይህ ነው፥ ወንዶች ልጆቻችሁን ወስዶ ሰረገለኞችና ፈረሰኞች ያደርጋቸዋል፥ በሰረገሎቹም ፊት ይሮጣሉ፥

参见章节 复制




1 ሳሙኤል 8:11
14 交叉引用  

ከዚ​ህም በኋላ አቤ​ሴ​ሎም ሰረ​ገ​ላና ፈረ​ሶች፥ በፊ​ቱም የሚ​ሮጡ አምሳ ሰዎች አዘ​ጋጀ።


የአ​ጊ​ትም ልጅ አዶ​ን​ያስ፥ “ንጉሥ እሆ​ና​ለሁ” ብሎ ተነሣ፤ ሰረ​ገ​ሎ​ች​ንና ፈረ​ሰ​ኞ​ችን በፊ​ቱም የሚ​ሮጡ አምሳ ሰዎ​ችን አዘ​ጋጀ።


ሰሎ​ሞ​ንም ለሰ​ረ​ገ​ሎቹ ዐራት ሺህ እን​ስት ፈረ​ሶች ነበ​ሩት፤ ዐሥራ ሁለት ሺህ ፈረ​ሰ​ኞ​ችም ነበ​ሩት፤ በሰ​ረ​ገ​ሎ​ችም ከተ​ሞች ከን​ጉሡ ጋር በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም አኖ​ራ​ቸው። ሰሎ​ሞ​ንም ከወ​ንዙ ጀምሮ እስከ ፍል​ስ​ጥ​ኤም ምድ​ርና እስከ ግብፅ ድን​በር ድረስ በነ​ገ​ሥ​ታቱ ሁሉ ላይ ንጉሥ ነበር።


ከእ​ር​ሱም ጋር ያደ​ጉት፥ በፊቱ የሚ​ቆ​ሙት ብላ​ቴ​ኖች እን​ዲህ አሉት፥ “አባ​ትህ ቀን​በር አክ​ብ​ዶ​ብ​ናል፥ አንተ ግን ዛሬ አቃ​ል​ል​ልን ለሚ​ሉህ ሕዝብ፦ ታና​ሺቱ ጣቴ ከአ​ባቴ ወገብ ትወ​ፍ​ራ​ለች።


“አባ​ትህ ቀን​በር አክ​ብ​ዶ​ብን ነበር፤ አሁ​ንም አንተ ጽኑ​ውን የአ​ባ​ት​ህን አገ​ዛዝ፥ በላ​ያ​ች​ንም የጫ​ነ​ውን የከ​በ​ደ​ውን ቀን​በር አቃ​ል​ል​ልን፤ እኛም እን​ገ​ዛ​ል​ሃ​ለን።”


ንጉ​ሡም ሮብ​ዓም በፋ​ን​ታው የናስ ጋሾ​ችን ሠራ፤ በፊ​ቱም ለሚ​ሮ​ጡና የን​ጉ​ሥን ቤት ደጅ ለሚ​ጠ​ብቁ የዘ​በ​ኞች አለ​ቆች ሰጣ​ቸው።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እጅ በኤ​ል​ያስ ላይ ነበ​ረች፤ ወገ​ቡ​ንም ታጥቆ ወደ ኢይ​ዝ​ራ​ኤል እስ​ኪ​ገባ ድረስ በአ​ክ​ዓብ ፊት ይሮጥ ነበር።


ሳሙ​ኤ​ልም የን​ጉ​ሡን ሥር​ዐት ነገ​ራ​ቸው፤ በመ​ጽ​ሐ​ፍም ጻፈው፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት አኖ​ረው። ሳሙ​ኤ​ልም ሕዝ​ቡን ሁሉ ወደ እየ​ቤ​ታ​ቸው አሰ​ና​በ​ታ​ቸው። ሕዝ​ቡም ሁሉ ወደ እየ​ቤ​ታ​ቸው ሄዱ።


በሳ​ኦ​ልም ዘመን ሁሉ ከፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ጋር ጽኑ ውጊያ ነበረ፤ ሳኦ​ልም ጽኑ ወይም ኀያል ሰው ባየ ጊዜ ወደ እርሱ ይሰ​በ​ስብ ነበር።


ሳኦ​ልም በአ​ጠ​ገቡ የቆ​ሙ​ትን ብላ​ቴ​ኖች፥ “ብን​ያ​ማ​ው​ያን ሆይ! እን​ግ​ዲህ ስሙ በእ​ው​ነት የእ​ሴይ ልጅ እር​ሻና የወ​ይን ቦታ ለሁ​ላ​ችሁ ይሰ​ጣ​ች​ኋ​ልን? ሁላ​ች​ሁ​ንስ መቶ አለ​ቆ​ችና ሻለ​ቆች ያደ​ር​ጋ​ች​ኋ​ልን?


አሁ​ንም ቃላ​ቸ​ውን ስማ፤ ነገር ግን ጽኑ ምስ​ክር መስ​ክ​ር​ባ​ቸው፤ በእ​ነ​ር​ሱም ላይ የሚ​ነ​ግ​ሠ​ውን የን​ጉ​ሡን ሥር​ዐት ንገ​ራ​ቸው።”


跟着我们:

广告


广告