Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ሳሙኤል 4:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 በዚ​ያም ቀን አንድ የብ​ን​ያም ሰው ከሰ​ልፍ እየ​በ​ረረ ወደ ሴሎ መጣ፤ ልብ​ሱም ተቀ​ድዶ ነበር፤ በራ​ሱም ላይ ትቢያ ነስ​ንሶ ነበር።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 በዚያች ዕለት አንድ ብንያማዊ ልብሱን ቀዶ፣ በራሱም ላይ ትቢያ ነስንሶ፣ ከጦሩ ሜዳ እየበረረ ወደ ሴሎ መጣ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 አንድ የብንያም ወገን የሆነ ሰው ልብሱን ቀዶ፥ በራሱም ላይ ትቢያ ነስንሶ፥ ከጦሩ ሜዳ እየበረረ ወደ ሴሎ መጣ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 ነገዱ ከብንያም ወገን የሆነ አንድ ሰው ከጦር ሜዳ ተነሥቶ በመገሥገሥ በዚያኑ ዕለት ሴሎ ደረሰ፤ ሐዘኑንም ለማሳወቅ ልብሱን ቀዶ በራሱ ላይ ትቢያ ነስንሶ ነበር፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 በዚያም ቀን አንድ የብንያም ሰው ከሰልፍ እየበረረ ልብሱን ቀድዶ በራሱም ላይ ትቢያ ነስንሶ ወደ ሴሎ መጣ።

参见章节 复制




1 ሳሙኤል 4:12
9 交叉引用  

በሦ​ስ​ተ​ኛ​ውም ቀን፥ እነሆ፥ ከሰ​ፈር ከሳ​ኦል ወገን አንድ ሰው ልብ​ሱን ቀድዶ፥ በራ​ሱም ላይ ትቢያ ነስ​ንሶ መጣ፤ ወደ ዳዊ​ትም በመጣ ጊዜ በም​ድር ላይ ወድቆ ሰገ​ደ​ለት።


ትዕ​ማ​ርም አመድ ወስዳ በራ​ስዋ ላይ ነሰ​ነ​ሰች፤ በላ​ይዋ የነ​በ​ረ​ው​ንም ብዙ ኅብር ያለ​ውን ልብ​ስ​ዋን ቀደ​ደ​ችው፤ እጅ​ዋ​ንም በራ​ስዋ ላይ ጭና እየ​ጮ​ኸች ሄደች።


ዳዊ​ትም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወደ ሰገ​ደ​በት ወደ ተራ​ራው ራስ መጣ፤ ወዳጁ ኵሲም ልብ​ሱን ቀደደ፤ በራ​ሱም ላይ ትቢያ ነስ​ንሶ ሊገ​ና​ኘው መጣ።


በዚ​ህም ወር በሃያ አራ​ተ​ኛው ቀን የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ጾመው፥ ማቅም ለብ​ሰው፥ በራ​ሳ​ቸ​ውም ላይ ትቢያ ነስ​ን​ሰው ተሰ​በ​ሰቡ።


ከሩ​ቅም ሆነው ባዩት ጊዜ አላ​ወ​ቁ​ትም፤ በታ​ላቅ ድም​ፅም ጮኸው አለ​ቀሱ፤ መጐ​ና​ጸ​ፊ​ያ​ቸ​ው​ንም ቀደዱ፥ በራ​ሳ​ቸ​ውም ላይ ትቢያ ነሰ​ነሱ።


ይህን ቤት እንደ ሴሎ አደ​ር​ገ​ዋ​ለሁ፤ ይች​ንም ከተማ ለም​ድር አሕ​ዛብ ሁሉ ርግ​ማን አደ​ር​ጋ​ታ​ለሁ።”


በዚያ ቀን ያመ​ለ​ጠው ይህን ነገር በጆ​ሮህ ያሰማ ዘንድ ወደ አንተ ይመ​ጣል።


ድም​ፃ​ቸ​ው​ንም በአ​ንቺ ላይ ያሰ​ማሉ፤ ምርር ብለ​ውም ይጮ​ኻሉ፤ በራ​ሳ​ቸ​ውም ላይ ትቢያ ይነ​ሰ​ን​ሳሉ፤ አመ​ድም ያነ​ጥ​ፋሉ።


ኢያ​ሱም ልብ​ሱን ቀደደ፤ እር​ሱና የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሽማ​ግ​ሌ​ዎች በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታቦት ፊት እስከ ማታ ድረስ በግ​ን​ባ​ራ​ቸው ተደፉ፤ በራ​ሳ​ቸ​ውም ላይ ትቢያ ነሰ​ነሱ።


跟着我们:

广告


广告