Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ሳሙኤል 31:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 በሸ​ለ​ቆ​ውም ማዶና በዮ​ር​ዳ​ኖስ ማዶ የነ​በሩ እስ​ራ​ኤ​ላ​ው​ያን የእ​ስ​ራ​ኤል ሰዎች እንደ ሸሹ፥ ሳኦ​ልና ልጆ​ቹም እንደ ሞቱ ባዩ ጊዜ ከተ​ሞ​ቹን ለቅ​ቀው ሸሹ፤ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም መጥ​ተው ተቀ​መ​ጡ​ባ​ቸው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 በሸለቆው ማዶና ከዮርዳኖስ ባሻገር ያሉ እስራኤላውያን፣ የእስራኤል ሰራዊት መሸሹን፣ ሳኦልና ልጆቹም መሞታቸውን ሲያዩ፣ ከተሞቻቸውን ለቅቀው ሸሹ፤ ፍልስጥኤማውያንም መጥተው ተቀመጡባቸው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 በሸለቆው ማዶና ከዮርዳኖስ ባሻገር ያሉ እስራኤላውያን የእስራኤል ሠራዊት መሸሹን፥ ሳኦልና ልጆቹም መሞታቸውን ባዩ ጊዜ ከተሞቻቸውን ለቀው ሸሹ፤ ፍልስጥኤማውያንም መጥተው ተቀመጡባቸው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 ከዮርዳኖስ ወንዝ በስተ ምሥራቅና በኢይዝራኤል ሸለቆ ማዶ የነበሩ እስራኤላውያንም የእስራኤል ሠራዊት መሸሹን፥ ሳኦልና ልጆቹም መገደላቸውን ሰምተው ከተሞቻቸውን እየጣሉ ሸሹ፤ ፍልስጥኤማውያንም መጥተው ከተሞቹን ያዙ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 በሸለቆውም ማዶና በዮርዳኖስ ማዶ የነበሩ እስራኤላውያን የእስራኤል ሰዎች እንደ ሸሹ፥ ሳኦልና ልጆቹም እንደ ሞቱ ባዩ ጊዜ ከተማቹን ለቅቀው ሸሹ፥ ፍልስጥኤማውያንም መጥተው ተቀመጡባቸው።

参见章节 复制




1 ሳሙኤል 31:7
8 交叉引用  

ምድ​ሪ​ቱ​ንም የተ​ፈ​ታች አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ የሚ​ቀ​መ​ጡ​ባት ጠላ​ቶ​ቻ​ች​ሁም ከእ​ር​ስዋ የተ​ነሣ ይደ​ነ​ቃሉ።


በጠ​ላ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ምድ​ሮች ሳሉ ከእ​ና​ንተ ተለ​ይ​ተው በቀ​ሩት ላይ በል​ባ​ቸው ድን​ጋ​ጤን እሰ​ድ​ድ​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ በነ​ፋ​ስም የም​ት​ን​ቀ​ሳ​ቀስ የቅ​ጠል ድምፅ ታሸ​ብ​ራ​ቸ​ዋ​ለች፤ ከሰ​ይፍ እን​ደ​ሚ​ሸሹ ይሸ​ሻሉ ፤


የም​ድ​ር​ህን ፍሬ፥ ድካ​ም​ህ​ንም ሁሉ የማ​ታ​ው​ቀው ሕዝብ ይበ​ላ​ዋል፤ አን​ተም ሁል​ጊዜ የተ​ጨ​ነ​ቅህ፥ የተ​ገ​ፋ​ህም ትሆ​ና​ለህ።


የም​ድ​ያ​ምም እጅ በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ጠነ​ከ​ረች፤ ከም​ድ​ያ​ምም ፊት የተ​ነሣ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች በተ​ራ​ሮ​ችና በገ​ደ​ሎች ላይ ጕድ​ጓ​ድና ዋሻ፥ ምሽ​ግም አበጁ።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሰዎች ወደ እነ​ርሱ መሄድ እን​ደ​ሚ​ያ​ስ​ጨ​ን​ቃ​ቸው ባዩ ጊዜ ሕዝቡ በዋ​ሻና በግ​ንብ፥ በገ​ደ​ልና በቋ​ጥኝ፥ በጕ​ድ​ጓ​ድም ውስጥ ተሸ​ሸጉ።


ዮር​ዳ​ኖ​ስ​ንም ተሻ​ግ​ረው ወደ ጋድና ወደ ገለ​ዓድ ምድር የሄዱ አሉ፤ ሳኦል ግን ገና በጌ​ል​ጌላ ነበረ፤ ሕዝ​ቡም ሁሉ ፈር​ተው እር​ሱን መከ​ተ​ልን ትተው ተበ​ተኑ።


በዚ​ያም ቀን ሳኦል ሦስ​ቱም ልጆቹ ጋሻ ጃግ​ሬ​ውም በአ​ንድ ላይ ሞቱ።


በማ​ግ​ሥ​ቱም ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን የሞ​ቱ​ትን ለመ​ግ​ፈፍ በመጡ ጊዜ ሳኦ​ልና ሦስቱ ልጆቹ በጌ​ላ​ቡሄ ተራራ ላይ ወድ​ቀው አገ​ኙ​አ​ቸው።


跟着我们:

广告


广告