Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ሳሙኤል 30:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 ወደ እዚ​ያም ባደ​ረ​ሰው ጊዜ፥ እነሆ፥ ከፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንና ከይ​ሁዳ ምድር ከወ​ሰ​ዱት ከብዙ ምርኮ ሁሉ የተ​ነሣ በል​ተው፥ ጠጥ​ተው፥ የበ​ዓ​ልም ቀን አድ​ር​ገው፥ በም​ድር ሁሉ ላይ ተበ​ት​ነው አገ​ኛ​ቸው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 ዳዊትን ወደ ታች መርቶ ባደረሰው ጊዜም፣ ወራሪዎቹ ከፍልስጥኤማውያንና ከይሁዳ ምድር ከወሰዱት ታላቅ ምርኮ የተነሣ በየቦታው ተበታትነው ይበሉ፣ ይጠጡና ይዘፍኑ፣ ይጨፍሩም ነበር።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 ዳዊትን ወደ ታች መርቶ ባደረሰው ጊዜም፥ እነሆ ወራሪዎቹ ከፍልስጥኤማውያንና ከይሁዳ ምድር ከወሰዱት ታላቅ ምርኮ የተነሣ በየቦታው ተበታትነው ይበሉ፥ ይጠጡና ይዘፍኑ፥ ይጨፍሩም ነበር።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 ከዚያም በኋላ ዳዊትን ወራሪዎቹ ወዳሉበት እየመራ አደረሰው። ወራሪዎቹም በየቦታው ተበታትነው በመብላትና በመጠጣት ተድላ ደስታ በማድረግ ላይ ነበሩ፤ ከፍልስጥኤምና ከይሁዳ ያገኙት ምርኮ እጅግ ብዙ ነበር፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 ወደ ታችም እንዲወርድ ባደረገው ጊዜ፥ እነሆ፥ ከፍልስጥኤማውያንና ከይሁዳ ምድር ከወሰዱት ከብዙ ምርኮ ሁሉ የተነሣ በልተው ጠጥተውም የበዓልም ቀን አድርገው በምድር ሁሉ ላይ ተበትነው ነበር።

参见章节 复制




1 ሳሙኤል 30:16
22 交叉引用  

አቤ​ሴ​ሎ​ምም እንደ ንጉሥ ግብዣ ያለ ግብዣ አደ​ረገ፤ አቤ​ሴ​ሎ​ምም አገ​ል​ጋ​ዮ​ቹን፥ “አም​ኖን የወ​ይን ጠጅ ጠጥቶ ልቡን ደስ ባለው ጊዜ እዩ፦ አም​ኖ​ንን ግደሉ ባል​ኋ​ችሁ ጊዜ ግደ​ሉት። አት​ፍ​ሩም፤ ያዘ​ዝ​ኋ​ች​ሁም እኔ ነኝና በርቱ፤ ጽኑም” ብሎ አዘ​ዛ​ቸው።


ያመ​ለ​ጡ​ት​ንም የአ​ማ​ሌ​ቃ​ው​ያ​ንን ቅሬታ መቱ፥ በዚ​ያም እስከ ዛሬ ድረስ ተቀ​ም​ጠ​ዋል።


የኀ​ጢ​ኣ​ተ​ኞች ደስታ ታላቅ ሰልፍ ነው፥ የዝ​ን​ጉ​ዎ​ችም ደስታ ጥፋት ነው።


አሮ​ንም በነ​ጋው ማልዶ ተነሣ፤ የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕ​ት​ንም ሠዋ፤ የደ​ኅ​ን​ነት መሥ​ዋ​ዕ​ት​ንም አቀ​ረበ ሕዝ​ቡም ሊበ​ሉና ሊጠጡ ተቀ​መጡ፤ ሊዘ​ፍ​ኑም ተነሡ።


እነ​ሆም፥ በዓ​ልን፥ ደስ​ታ​ንና ሐሴ​ትን አደ​ረ​ጋ​ችሁ፤ በሬ​ዎ​ች​ንና በጎ​ች​ንም አረ​ዳ​ችሁ፤ “ነገ እን​ሞ​ታ​ለን፤ እን​ብላ፤ እን​ጠ​ጣም፤” እያ​ላ​ችሁ ሥጋን በላ​ችሁ፤ ወይ​ን​ንም ጠጣ​ችሁ።


ብዙ ሕዝ​ብን በደ​ስታ አወ​ረ​ድህ፤ በመ​ከር ደስ እን​ደ​ሚ​ላ​ቸው፥ ምር​ኮ​ንም እን​ደ​ሚ​ካ​ፈሉ በፊ​ትህ ደስ ይላ​ቸ​ዋል።


ሰላምና ደኅንነት ነው ሲሉ ያን ጊዜ ምጥ እርጕዝን እንደሚይዛት ጥፋት በድንገት ይመጣባቸዋል፤ከቶም አያመልጡም።


“በብዙ ብል​ጥ​ግና፥ በእ​ጅ​ግም ብዙ ከብት፥ በብ​ርም፥ በወ​ር​ቅም፥ በና​ስም፥ በብ​ረ​ትም፥ በእ​ጅ​ግም ብዙ ልብስ ወደ ቤታ​ችሁ ተመ​ለሱ፤ የጠ​ላ​ቶ​ቻ​ች​ሁ​ንም ምርኮ ከወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ችሁ ጋር ተካ​ፈሉ።”


ጌዴ​ዎ​ንም በድ​ን​ኳን የሚ​ኖሩ ሰዎች ባሉ​በት መን​ገድ በኖ​ቤ​ትና በዮ​ግ​ቤል በም​ሥ​ራቅ በኩል ወጣ፤ ሠራ​ዊ​ቱም ተዘ​ልሎ ሳለ አጠ​ፋ​ቸው።


እኛም በከ​ሊ​ታ​ው​ያን አዜብ፥ በይ​ሁ​ዳም በኩል፥ በካ​ሌ​ብም አዜብ ላይ ዘመ​ትን፥ ሴቄ​ላ​ቅ​ንም በእ​ሳት አቃ​ጠ​ል​ናት” አለው።


ዳዊ​ትም፥ “ወደ እነ​ዚያ ሠራ​ዊት ልት​መ​ራኝ ትወ​ድ​ዳ​ለ​ህን?” አለው፥ እር​ሱም፥ “እን​ዳ​ት​ገ​ድ​ለኝ፥ ለጌ​ታ​ዬም እጅ አሳ​ል​ፈህ እን​ዳ​ት​ሰ​ጠኝ በአ​ም​ላክ ማል​ልኝ፤ እኔም ወደ እነ​ዚያ ሠራ​ዊት እመ​ራ​ሃ​ለሁ” አለው።


跟着我们:

广告


广告