Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ሳሙኤል 30:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 ከበ​ለ​ሱም ጥፍ​ጥፍ ቍራጭ ሰጡ​ትና በላ፤ ነፍ​ሱም ወደ እርሱ ተመ​ለ​ሰች፤ ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት እን​ጀራ አል​በ​ላም፤ ውኃም አል​ጠ​ጣም ነበ​ርና።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 እንደዚሁም የበለስ ጥፍጥፍ ቍራሽና ሁለት ደረቅ የወይን ዘለላዎች ሰጡት። ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት ምንም እህል ስላልበላ፣ ውሃም ስላልጠጣ ይህን ከበላ በኋላ ነፍሱ ተመለሰች።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 እንደዚሁም የበለስ ጥፍጥፍ ቁራሽና ሁለት ደረቅ የወይን ዘለላዎች ሰጡት። ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት ምንም እህል ስላልበላ፥ ውሃም ስላልጠጣ ይህን ከበላ በኋላ ነፍሱ ተመለሰች።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 ደረቅ የበለስ ፍሬና ሁለት ጥፍጥፍ ዘቢብ አቀረቡለት፤ ወጣቱም ከተመገበ በኋላ እንደገና በረታ፤ ከዚያ በፊት ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት እህል ውሃ አልቀመሰም ነበር።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 ከበለሱም ጥፍጥፍ ቁራጭና ሁለት የወይን ዘለላ ሰጡት ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት እንጀራ አልበላም ውኃም አልጠጣም ነበርና በበላ ጊዜ ነፍሱ ወደ እርሱ ተመለሰች።

参见章节 复制




1 ሳሙኤል 30:12
9 交叉引用  

ካፍ። ሕዝ​ብዋ ሁሉ እን​ጀራ አጥ​ተው ያለ​ቅ​ሳሉ፤ ሰው​ነ​ታ​ቸ​ውን ለማ​በ​ር​ታት ፍላ​ጎ​ታ​ቸ​ውን ስለ መብል ሰጥ​ተ​ዋል፤ አቤቱ! ተጐ​ሳ​ቍ​ያ​ለ​ሁና እይ፤ ተመ​ል​ከ​ትም።


“ጌታ ሆይ! ያ አሳች በሕይወቱ ገና ሳለ ‘ከሦስት ቀን በኋላ እነሣለሁ፤’ እንዳለ ትዝ አለን።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የዚ​ያ​ችን የአ​ህያ መን​ጋጋ አጥ​ንት ስን​ጥ​ቃት ከፈተ፤ ከእ​ር​ስ​ዋም ውኃ ወጣ፤ እር​ሱም ጠጣ፤ ነፍ​ሱም ተመ​ለ​ሰች፤ ከውኃ ጥሙም ዐረፈ። ስለ​ዚ​ህም የዚያ ቦታ ስም እስከ ዛሬ ድረስ “ነቅዐ አጽመ መን​ሰክ” ተብሎ ተጠራ።


ዮና​ታን ግን አባቱ ሕዝ​ቡን ባማለ ጊዜ አል​ሰ​ማም ነበር፤ እር​ሱም በእጁ ያለ​ች​ውን በትር አን​ሥቶ ጫፍ​ዋን ወደ ወለ​ላው ነከረ፤ እጁ​ንም ወደ አፉ አደ​ረገ፤ ዐይ​ኑም በራ።


በበ​ረ​ሃ​ውም ውስጥ አንድ ግብ​ፃዊ አግ​ኝ​ተው ወደ ዳዊት ይዘ​ውት መጡ፤ እን​ጀ​ራም ሰጡ​ትና በላ፤ ውኃም አጠ​ጡት።


ዳዊ​ትም፥ “አንተ የማን ነህ? ከወ​ዴት መጣህ?” አለው። ያም ግብ​ፃዊ ብላ​ቴና፥ “እኔ የአ​ማ​ሌ​ቃዊ ባሪያ ነኝ፤ ከሦ​ስት ቀንም በፊት ታምሜ ነበ​ርና ጌታዬ ጥሎኝ ሄደ።


跟着我们:

广告


广告