1 ሳሙኤል 3:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)1 ብላቴናው ሳሙኤልም በዔሊ ፊት እግዚአብሔርን ያገለግል ነበር፤ በዚያም ዘመን የእግዚአብሔር ቃል ክቡር ነበረ፤ ራእይም አይገለጥም ነበር። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም1 ብላቴናው ሳሙኤል ከዔሊ በታች ሆኖ እግዚአብሔርን ያገለግል ነበር። በዚያም ዘመን የእግዚአብሔር ቃል ብርቅ ነበረ፤ ራእይም አይታይም ነበር። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)1 ብላቴናው ሳሙኤል ከዔሊ በታች ሆኖ ጌታን ያገለግል ነበር። በዚያም ዘመን የጌታ ቃል ዘወትር የሚሰማ አልነበረም፤ ራእይም አይታይም ነበር። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም1 ወጣቱ ሳሙኤል በዔሊ የአመራር ሥልጣን ሥር ሆኖ እግዚአብሔርን ያገለግል ነበር፤ በዚያን ጊዜ የእግዚአብሔር ቃል ዘወትር አይሰማም ነበር፤ ራእይም አይታይም ነበር። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)1 ብላቴናውም ሳሙኤል በዔሊ ፊት እግዚአብሔርን ያገለግል ነበር፥ በዚያም ዘመን የእግዚአብሔር ቃል ብርቅ ነበረ፥ ራእይም አይገለጥም ነበር። 参见章节 |