Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ሳሙኤል 27:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 አን​ኩ​ስም፥ “በሕ​ዝቡ በእ​ስ​ራ​ኤል ዘንድ እጅግ የተ​ጠላ ሆኖ​አል፤ ስለ​ዚ​ህም ለዘ​ለ​ዓ​ለም ባሪያ ይሆ​ነ​ኛል” ብሎ ዳዊ​ትን አመ​ነው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 አንኩስም በልቡ፣ “እርሱ ራሱ የገዛ ሕዝቡ የሆኑት እስራኤላውያን እጅግ እንዲጠሉት ስላደረገ፣ ለዘላለም አገልጋዬ ይሆናል” ብሎ ስላሰበ ዳዊትን አመነው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 አኪሽም በልቡ፥ “እርሱ ራሱ የገዛ ሕዝቡ የሆኑት እስራኤላውያን እጅግ እንዲጠሉት ስላደረገ፥ ለዘለዓለም አገልጋዬ ይሆናል” ብሎ ስላሰበ ዳዊትን አመነው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 አኪሽ ግን ዳዊትን ስለሚተማመንበት በልቡ “በወገኖቹ በእስራኤል ሕዝብ ዘንድ የተጠላ ስለ ሆነ በሕይወቱ ዘመን ሁሉ ያገለግለኛል” በማለት ያስብ ነበር።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 አንኩስም፦ በሕዝቡ በእስራኤል ዘንድ እጅግ የተጠላ ሆኖአል፥ ሰለዚህም ለዘላለም ባሪያ ይሆነኛል ብሎ ዳዊትን አመነው።

参见章节 复制




1 ሳሙኤል 27:12
6 交叉引用  

ያዕ​ቆ​ብም ስም​ዖ​ን​ንና ሌዊን እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ክፉ አደ​ረ​ጋ​ች​ሁ​ብኝ፤ በዚች ሀገር በሚ​ኖሩ በከ​ነ​ዓ​ና​ው​ያ​ንና በፌ​ር​ዜ​ዎ​ና​ው​ያን ሰዎች ዘንድ አስ​ጠ​ላ​ች​ሁኝ። እኔ በቍ​ጥር ጥቂት ነኝ፤ እነ​ርሱ በእኔ ላይ ይሰ​በ​ሰ​ቡና ይወ​ጉ​ኛል፤ እኔና ቤቴም እን​ጠ​ፋ​ለን።”


የአ​ሞ​ንም ልጆች የዳ​ዊት ወገ​ኖች እንደ አፈሩ ባዩ ጊዜ፥ የአ​ሞን ልጆች ልከው ከቤ​ት​ሮ​ዖብ ሶር​ያ​ው​ያ​ንና ከሱባ ሶር​ያ​ው​ያን ሃያ ሺህ እግ​ረ​ኞ​ችን፥ ከአ​ማ​ሌቅ ንጉ​ሥም አንድ ሺህ ሰዎ​ችን፥ ከአ​ስ​ጦ​ብም ዐሥራ ሁለት ሺህ ሰዎ​ችን ቀጠሩ።


እነ​ር​ሱም፥ “በፈ​ር​ዖ​ንና በሹ​ሞቹ ፊት ሽታ​ች​ንን አግ​ም​ታ​ች​ሁ​ታ​ልና፥ ይገ​ድ​ለ​ንም ዘንድ ሰይ​ፍን በእጁ ሰጥ​ታ​ች​ሁ​ታ​ልና እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይመ​ል​ከ​ታ​ችሁ፤ ይፍ​ረ​ድ​ባ​ች​ሁም” አሉ​አ​ቸው።


እስ​ራ​ኤ​ልም ሁሉ ሳኦል የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንን ጭፍራ እንደ መታ፥ ደግ​ሞም እስ​ራ​ኤል በፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ዘንድ እንደ በረቱ ሰሙ፤ ሕዝ​ቡም ደን​ፍ​ተው ሳኦ​ልን ለመ​ከ​ተል ወደ ጌል​ጌላ ተሰ​በ​ሰቡ።


ዳዊት እን​ዲህ አደ​ረገ፤ በፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም ሀገር በሚ​ቀ​መ​ጥ​በት ዘመን ሁሉ ልማዱ ይህ ነበረ ብለው እን​ዳ​ይ​ና​ገ​ሩ​ብን ብሎ ዳዊት ወደ ጌት ያመ​ጣ​ቸው ዘንድ ወን​ድም ሆነ ሴትም ሆነ ማን​ንም በሕ​ይ​ወት አል​ተ​ወም።


እን​ዲ​ህም ሆነ፤ በዚያ ወራት ከእ​ስ​ራ​ኤል ጋር ይዋጉ ዘንድ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ጭፍ​ሮ​ቻ​ቸ​ውን ለሰ​ልፍ ሰበ​ሰቡ፤ አን​ኩ​ስም ዳዊ​ትን፥ “አን​ተና ሰዎ​ችህ ከእኔ ጋር ወደ ሰልፍ እን​ድ​ት​ወጡ በር​ግጥ ዕወቅ” አለው።


跟着我们:

广告


广告