1 ሳሙኤል 27:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)11 ዳዊት እንዲህ አደረገ፤ በፍልስጥኤማውያንም ሀገር በሚቀመጥበት ዘመን ሁሉ ልማዱ ይህ ነበረ ብለው እንዳይናገሩብን ብሎ ዳዊት ወደ ጌት ያመጣቸው ዘንድ ወንድም ሆነ ሴትም ሆነ ማንንም በሕይወት አልተወም። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም11 ዳዊት “ ‘እርሱ እንዲህ አድርጓል’ ብለው ይነግሩብናል” ብሎ ስላሰበ፣ ወንድም ሆነ ሴት በሕይወት አስቀርቶ ወደ ጋት አላመጣም። በፍልስጥኤም ግዛት በኖረበት ዘመን ሁሉ፣ እንዲህ ማድረጉ የተለመደ ነበር። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)11 ዳዊት “ ‘እርሱ እንዲህ አድርጓል’ ብለው ይነግሩብናል” ብሎ ስላሰበ፥ ወንድም ሆነ ሴት በሕይወት አስቀርቶ ወደ ጋት አላመጣም። በፍልስጥኤም ግዛት በኖረበት ዘመን ሁሉ እንዲህ ማድረጉ የተለመደ ነበር። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም11 ዳዊት ወንድንም ሆነ ሴትን ወደ ጋት ሳያመጣ ሁሉንም ገደለ። ይህንንም ያደረገው ዳዊት ይህንንና ይህንን አደረገ ብለው እንዳይነግሩበት ነው። በፍልስጥኤም አገር በኖረበት ዘመን ሁሉ ይህን የማድረግ ልማድ ነበረው። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)11 ዳዊት እንዲህ አደረገ በፍልስጥኤማውያንም አገር በሚቀመጥበት ዘመን ሁሉ ልማዱ ይህ ነበረ ብለው እንዳይናገሩብን ብሎ ዳዊት ወደ ጌት ያመጣቸው ዘንድ ወንድም ሆነ ሴትም ሆነ ማንንም በሕይወት አልተወም። 参见章节 |