Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ሳሙኤል 27:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 አን​ኩ​ስም ዳዊ​ትን፥ “ዛሬ በማን ላይ ዘመ​ታ​ችሁ?” አለው፤ ዳዊ​ትም፥ “በይ​ሁዳ ደቡብ፥ በያ​ሴ​ሜጋ ደቡብ፥ በቄ​ኔ​ዛ​ው​ያን ደቡብ ላይ ዘመ​ትን” አለው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 አንኩስም፣ “ዛሬ በማን ላይ ዘመታችሁ?” ሲል በጠየቀው ጊዜ ዳዊት፣ “የዘመትነው በይሁዳ ደቡብ፣ ወይም በይረሕምኤላውያን ደቡብ፣ ወይም በቄናውያን ደቡብ ላይ ነው” በማለት ይመልስ ነበር።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 አኪሽም፥ “ዛሬ በማን ላይ ዘመታችሁ?” ሲል በጠየቀው ጊዜ ዳዊት፥ “የዘመትነው በይሁዳ፥ ወይም በይራሕመኤላውያን፥ ወይም በቄናውያን ላይ ነው” እያለ ይመልስለት ነበር።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 አኪሽ “በዚህ ጊዜ ወረራ ያደረጋችኹት በየት በኩል ነው” ብሎ ሲጠይቀው ዳዊት “እኛ የዘመትነው ከይሁዳ በስተ ደቡብ ባለው ክፍል፥ እንደገናም በይራሕመኤል ነገድ ግዛትና ቄናውያን በሚኖሩበት ግዛት ነው” እያለ ይመልስለት ነበር።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 አንኩስም፦ ዛሬ በማን ላይ ዘመታችሁ? አለ፥ ዳዊትም፦ በይሁዳ ደቡብ፥ በይረሕምኤላውያንም ደቡብ፥ በቄናውያንም ደቡብ ላይ ዘመትን አለ።

参见章节 复制




1 ሳሙኤል 27:10
21 交叉引用  

አለ​ውም፥ “አንተ ልጄ ዔሳው ነህን?” እር​ሱም፥ “እኔ ነኝ” አለ።


የአ​ቤ​ሴ​ሎ​ምም አገ​ል​ጋ​ዮች ወደ ሴቲቱ ወደ ቤት መጥ​ተው፥ “አኪ​ማ​ሆ​ስና ዮና​ታን የት አሉ?” አሉ፤ ሴቲ​ቱም፥ “ፈፋ​ውን ተሻ​ግ​ረው ሄዱ፤ ጥቂ​ትም ቀደ​ሙ​አ​ችሁ” አለ​ቻ​ቸው። እነ​ር​ሱም ፈል​ገው አጡ​አ​ቸው፤ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ተመ​ለሱ።


የኤ​ስ​ሮ​ምም የበ​ኵር ልጁ የኢ​ያ​ሬ​ም​ሄል ልጆች በኵሩ ራም፥ በአ​ናን፥ አራን፥ አሶም፥ አኪያ ነበሩ።


ለኤ​ስ​ሮም የተ​ወ​ለ​ዱ​ለት ልጆች፤ ኢያ​ሬ​ሄም፥ አራም፥ ካሌብ ነበሩ።


ቄኔ​ዎ​ና​ው​ያ​ን​ንም አይቶ በም​ሳሌ ይና​ገር ጀመር፤ እን​ዲ​ህም አለ፦ “ማደ​ሪ​ያህ የጸ​ናች ናት፤ ጎጆ​ህም በአ​ንባ ላይ ተሠ​ር​ቶ​አል፤


ስለ​ዚ​ህም ሐሰ​ትን ተዉ​አት፤ ሁላ​ች​ሁም ከወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ችሁ ጋር እው​ነ​ትን ተነ​ጋ​ገሩ፤ እኛ አንድ አካል ነንና።


የቄ​ና​ዊው የሙሴ አማት የዮ​ባብ ልጆ​ችም ከዘ​ን​ባባ ከተማ ተነ​ሥ​ተው ከዓ​ራድ በአ​ዜብ በኩል ወዳ​ለው ወደ ይሁዳ ምድረ በዳ ወደ ይሁዳ ልጆች ሄደው ከሕ​ዝቡ ጋር ተቀ​መጡ።


ቄና​ዊ​ውም ሔቤር ከሙሴ አማት ከኢ​ዮ​ባብ ልጆች ከቄ​ና​ው​ያን ተለ​ይቶ ድን​ኳ​ኑን በቃ​ዴስ አጠ​ገብ እስከ ነበ​ረው ታላቅ ዛፍ ድረስ ተከለ።


የቄ​ና​ዊው የሔ​ቤር ሚስት ኢያ​ዔል፥ ከሴ​ቶች ይልቅ የተ​ባ​ረ​ከች ትሁን፤ በድ​ን​ኳን ውስጥ ከሚ​ኖሩ ሴቶች ይልቅ የተ​ባ​ረ​ከች ትሁን።


ሳኦ​ልም ቄኔ​ዎ​ና​ው​ያ​ንን፥ “ከእ​ነ​ርሱ ጋር እን​ዳ​ላ​ጠ​ፋ​ችሁ ከአ​ማ​ሌ​ቃ​ው​ያን መካ​ከል ተነ​ሥ​ታ​ችሁ ሂዱ፤ ከግ​ብፅ በወጡ ጊዜ ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ቸር​ነት አድ​ር​ጋ​ች​ኋ​ልና” አላ​ቸው። ቄኔ​ዎ​ና​ው​ያ​ንም ከአ​ማ​ሌ​ቃ​ው​ያን መካ​ከል ወጡ።


ዳዊ​ትም ካህ​ኑን አቤ​ሜ​ሌ​ክን፥ “የተ​ላ​ክ​ህ​በ​ትን ነገ​ርና የሰ​ጠ​ሁ​ህን ትእ​ዛዝ ማንም አይ​ወቅ ብሎ ንጉሡ አንድ ነገር አዝ​ዞ​ኛል፤ ስለ​ዚ​ህም ‘ብላ​ቴ​ኖቼን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መታ​መን’ በሚ​ባ​ለው እን​ዲህ ባለው ስፍራ እን​ዲ​ሆኑ አዝ​ዣ​ቸ​ዋ​ለሁ።


ወደ ሳኦ​ልም መል​እ​ክ​ተኛ መጥቶ፥ “ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ሀገ​ሩን ወር​ረ​ው​ታ​ልና ፈጥ​ነህ ና” አለው።


ዳዊት እን​ዲህ አደ​ረገ፤ በፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም ሀገር በሚ​ቀ​መ​ጥ​በት ዘመን ሁሉ ልማዱ ይህ ነበረ ብለው እን​ዳ​ይ​ና​ገ​ሩ​ብን ብሎ ዳዊት ወደ ጌት ያመ​ጣ​ቸው ዘንድ ወን​ድም ሆነ ሴትም ሆነ ማን​ንም በሕ​ይ​ወት አል​ተ​ወም።


ዳዊ​ትም አን​ኩ​ስን፥ “ምን አድ​ር​ጌ​አ​ለሁ? ሄጄስ ከጌ​ታዬ ከን​ጉሡ ጠላ​ቶች ጋር እን​ዳ​ል​ዋጋ፥ በፊ​ትህ ከተ​ቀ​መ​ጥሁ ጀምሬ እስከ ዛሬ ድረስ በእኔ በአ​ገ​ል​ጋ​ይህ ምን በደል አግ​ኝ​ተ​ህ​ብ​ኛል?” አለው።


በቀ​ር​ሜ​ሎስ ለነ​በሩ፥ በይ​ረ​ሕ​ም​ኤ​ላ​ው​ያ​ንና በቄ​ኔ​ዛ​ው​ያን ከተ​ሞ​ችም ለነ​በሩ፥


跟着我们:

广告


广告