1 ሳሙኤል 26:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)5 ዳዊትም በቀስታ ተነሥቶ ሳኦል ወደ ሰፈረበት ቦታ መጣ፤ ሳኦልና የሠራዊቱ አለቃ የኔር ልጅ አቤኔርም የተኙበትን ስፍራ አየ፤ ሳኦልም በድንኳን ውስጥ ተኝቶ ነበር፤ ሕዝቡም በዙሪያው ሰፍሮ ነበር። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም5 ዳዊትም ተነሥቶ ሳኦል ወደ ሰፈረበት ቦታ ሄደ፤ ሳኦልና የሰራዊቱ አለቃ፣ የኔር ልጅ አበኔር የተኙበትን ስፍራ አየ። ሳኦል በሰፈሩ መካከል ተኝቶ ሳለ፣ ሰራዊቱ በዙሪያው ሰፍሮ ነበር። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)5 ዳዊትም ተነሥቶ ሳኦል ወደ ሰፈረበት ቦታ ሄደ፤ ሳኦልና የሠራዊቱ አለቃ፥ የኔር ልጅ አበኔር የተኙበትን ስፍራ አየ። ሠራዊቱ በዙሪያው ሰፍሮ፥ ሳኦል በሰፈሩ መካከል ተኝቶ ነበር። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም5 ከዚያም በፍጥነት ተነሥቶ በመሄድ ሳኦልና የሠራዊቱ አዛዥ የኔር ልጅ አበኔር የሚተኙበትን ቦታ አረጋገጠ፤ ሳኦል በሰፈሩ መካከል ተኝቶ ሳለ ወታደሮቹ በዙሪያው ይገኙ ነበር። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)5 ዳዊትም ተነሥቶ ሳኦል ወደ ሰፈረበት ቦታ መጣ፥ ሳኦልና የሠራዊቱ አለቃ የኔር ልጅ አበኔርም የተኙበትን ስፍራ አየ፥ ሳኦልም በሰፈሩ ውስጥ ተኝቶ ነበር፥ ሕዝቡም በዙሪያው ሰፍሮ ነበር። 参见章节 |