1 ሳሙኤል 25:29 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)29 የሚያሳድድህና ነፍስህን የሚሻ ሰው ቢነሣ፥ የጌታዬ ነፍስ በአምላክህ በእግዚአብሔር ዘንድ በሕይወት ማሰሪያ የታሰረች ትሆናለች፤ የጠላቶችህ ነፍስ ግን በወንጭፍ እንደሚወነጨፍ ትሁን። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም29 ማንም ሰው ሕይወትህን ለማጥፋት ቢያሳድድህ እንኳ፣ የጌታዬ ሕይወት በሕያዋን አንድነት እስራት ውስጥ በአምላክህ በእግዚአብሔር ዘንድ በሰላም ትጠበቃለች፤ የጠላቶችህን ሕይወት ግን፣ እንደ ወንጭፍ ድንጋይ ይወነጭፋል። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)29 ማንም ሰው ሕይወትህን ለማጥፋት ቢያሳድድህ እንኳ፥ የጌታዬ ሕይወት በሕያዋን አንድነት እስራት ውስጥ በአምላክህ በጌታ ዘንድ በሰላም ትጠበቃለች፤ የጠላቶችህን ሕይወት ግን፥ እንደ ወንጭፍ ድንጋይ ይወነጭፋል። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም29 ማንም ሰው በአንተ ላይ አደጋ ጥሎ ሊገድልህ ቢፈልግ አንድ ሰው ውድ የሆነ ሀብቱን እንደሚጠብቅ አምላክህ እግዚአብሔር አንተን በሰላም ይጠብቅሃል፤ ስለ ጠላቶችህም የሆነ እንደ ሆነ አንድ ሰው ድንጋዩን ከወንጭፍ እንደሚያስፈነጥር እግዚአብሔር ራሱ አሽቀንጥሮ ይጥላቸዋል። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)29 ያሳድድህ ዘንድ ነፍስህንም ይሻ ዘንድ ሰው ቢነሣ፥ የጌታዬ ነፍስ በሕያዋን ወገን በአምላክህ በእግዚአብሔር ዘንድ የታሰረች ትሆናለች፥ የጠላቶችህንም ነፋስ ከወንጭፍ እንደሚጣል እንዲሁ ይጥላታል። 参见章节 |