Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ሳሙኤል 25:23 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

23 አቤ​ግ​ያም ዳዊ​ትን ባየች ጊዜ ከአ​ህ​ያዋ ላይ ፈጥና ወረ​ደች፤ በዳ​ዊ​ትም ፊት በግ​ን​ባ​ርዋ ወደ​ቀች፤ ምድ​ርም ነክታ ሰገ​ደ​ች​ለት።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

23 አቢግያም ዳዊትን ባየች ጊዜ ወዲያው ከአህያዋ ወርዳ፣ በዳዊትም ፊት በግምባሯ ተደፍታ እጅ ነሣች።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

23 አቢግያም ዳዊትን ባየች ጊዜ ወዲያው ከአህያዋ ወርዳ፥ በዳዊትም ፊት በግምባርዋ ተደፍታ እጅ ነሣች።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

23 አቢጌልም ዳዊትን ባየችው ጊዜ በፍጥነት ከአህያዋ ወርዳ በዳዊት ጫማ አጠገብ መሬት ላይ ለጥ ብላ እጅ ነሣች፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

23 አቢግያም ዳዊትን ባየች ጊዜ ከአህያዋ ላይ ፈጥና ወረደች፥ በዳዊትም ፊት በግምባርዋ ወደቀች፥ በምድርም ላይ እጅ ነሣች።

参见章节 复制




1 ሳሙኤል 25:23
12 交叉引用  

በሦ​ስ​ተ​ኛ​ውም ቀን፥ እነሆ፥ ከሰ​ፈር ከሳ​ኦል ወገን አንድ ሰው ልብ​ሱን ቀድዶ፥ በራ​ሱም ላይ ትቢያ ነስ​ንሶ መጣ፤ ወደ ዳዊ​ትም በመጣ ጊዜ በም​ድር ላይ ወድቆ ሰገ​ደ​ለት።


እን​ዲ​ሁም የቴ​ቁ​ሔ​ዪቱ ሴት ወደ ንጉሥ ገብታ በግ​ን​ባ​ርዋ በም​ድር ላይ ወደ​ቀች፤ ሰግ​ዳም “ንጉሥ ሆይ፥ አድ​ነኝ፤ አድ​ነኝ” አለች።


አኪ​ማ​ሖ​ስም ጮኾ ንጉ​ሡን፥ “ሰላም ለአ​ንተ ይሁን!” አለው። በን​ጉ​ሡም ፊት በም​ድር ላይ በግ​ን​ባሩ ሰግዶ፥ “በን​ጉሡ በጌ​ታዬ ላይ እጃ​ቸ​ውን ያነ​ሡ​ትን ሰዎች አሳ​ልፎ የሰጠ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይመ​ስ​ገን” አለ።


የሳ​ኦ​ልም ልጅ የዮ​ና​ታን ልጅ ሜም​ፌ​ቡ​ስቴ ወደ ዳዊት መጣ፤ በግ​ን​ባ​ሩም ወድቆ ሰገ​ደ​ለት፤ ንጉሥ ዳዊ​ትም፥ “ሜም​ፌ​ቡ​ስቴ ሆይ፥” አለ፤ እር​ሱም፥ “እነ​ሆኝ አገ​ል​ጋ​ይህ” አለ።


ዳዊ​ትም ወደ ኦርና መጣ፤ ኦር​ናም ከአ​ው​ድ​ማው ወጥቶ ዳዊ​ትን ተቀ​በ​ለው። በም​ድ​ርም ላይ ወድቆ ሰገ​ደ​ለት።


እር​ስ​ዋም ወደ እርሱ በመ​ጣች ጊዜ “አባ​ቴን እርሻ ልለ​ም​ነው” ብላ አማ​ከ​ረ​ችው፤ እር​ስ​ዋም በአ​ህ​ያዋ ላይ ሆና ጮኸች፤ ካሌ​ብም፥ “ምን ሆንሽ?” አላት።


እር​ስ​ዋም ወደ እርሱ በመ​ጣች ጊዜ የእ​ርሻ ቦታ ይሰ​ጣት ዘንድ አባ​ቷን እን​ድ​ት​ለ​ም​ነው ጎቶ​ን​ያል መከ​ራት። እር​ስ​ዋም በአ​ህ​ያዋ ላይ ሆና አን​ጐ​ራ​ጐ​ረች፤ “ወደ ደቡብ ሰድ​ደ​ኸ​ኛል” ብላም ጮኸች። ካሌ​ብም፥ “ምን ሆነ​ሻል?” አላት።


በግምባርዋም ተደፍታ በምድር ላይ ሰገደችለት፦ እኔንስ ለመቀበል በምን ነገር በፊትህ ሞገስ አገኘሁ? እኔ እንግዳ አይደለሁምን? አለችው።


ብላ​ቴ​ና​ውም በሄደ ጊዜ ዳዊት ከኤ​ር​ገብ ተነሣ፤ በም​ድ​ርም ላይ በግ​ን​ባሩ ተደፋ፤ ሦስት ጊዜም ሰገደ፤ እርስ በእ​ር​ሳ​ቸ​ውም ተሳ​ሳሙ፤ ለረ​ዥም ሰዓ​ትም ተላ​ቀሱ።


ዳዊ​ትም በዚህ ቃል ሰዎ​ቹን ከለ​ከ​ላ​ቸው። በሳ​ኦ​ልም ላይ ተነ​ሥ​ተው ይገድ​ሉት ዘንድ አል​ፈ​ቀ​ደ​ላ​ቸ​ውም፤ ሳኦ​ልም ከዋ​ሻው ተነ​ሥቶ መን​ገ​ዱን ሄደ።


በእ​ግ​ሩም ላይ ወደ​ቀች፤ እን​ዲ​ህም አለች፥ “ጌታዬ ሆይ! ይህ ኀጢ​ኣት በእኔ ላይ ይሁን፤ እኔ ባሪ​ያህ በጆ​ሮህ ልና​ገር፥ የባ​ሪ​ያ​ህ​ንም ቃል አድ​ምጥ።


ተነ​ሥ​ታም በግ​ን​ባ​ርዋ በም​ድር ወድቃ ሰገ​ደ​ችና፥ “እነሆ፥ እኔ ገረ​ድህ የጌ​ታ​ዬን ሎሌ​ዎች እግር አጥብ ዘንድ አገ​ል​ጋይ ነኝ” አለች።


跟着我们:

广告


广告