Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ሳሙኤል 22:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

20 ከአ​ኪ​ጦ​ብም ልጅ ከአ​ቤ​ሜ​ሌክ ልጆች ስሙ አብ​ያ​ታር የሚ​ባል አንዱ ልጅ አም​ልጦ ሸሸ፤ ዳዊ​ት​ንም ተከ​ተለ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

20 የአኪጦብ ልጅ፣ የአቢሜሌክ ልጅ አብያታር ግን አምልጦ ዳዊት ወዳለበት ሸሸ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

20 የአኪጦብ ልጅ፥ የአቢሜሌክ ልጅ አብያታር ግን አምልጦ ዳዊት ወዳለበት ሸሸ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

20 ነገር ግን አብያታር የሚባል ከአቤሜሌክ ወንዶች ልጆች አንዱ ብቻ አምልጦ በመሄድ ከዳዊት ጋር ተቀላቀለ፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

20 ከአኪጦብም ልጅ ከአቢሜሌክ ልጆች ስሙ አብያታር የሚባል አንዱ ልጅ አምልጦ ወደ ዳዊት ሸሸ።

参见章节 复制




1 ሳሙኤል 22:20
15 交叉引用  

እነ​ሆም፥ ደግሞ፥ ሳዶ​ቅና ከእ​ር​ሱም ጋር ሌዋ​ው​ያን ሁሉ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ኪዳን ታቦት አመጡ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ታቦት አስ​ቀ​መጡ፤ ሕዝ​ቡም ሁሉ ከከ​ተ​ማ​ዪቱ ፈጽሞ እስ​ኪ​ያ​ልፉ ድረስ አብ​ያ​ታር ወጣ።


ሱሳም ጸሓፊ ነበረ፤ ሳዶ​ቅና አብ​ያ​ታ​ርም ካህ​ናት ነበሩ፤


ሴራ​ውም ከሶ​ር​ህያ ልጅ ከኢ​ዮ​አ​ብና ከካ​ህኑ ከአ​ብ​ያ​ታር ጋር ነበረ፤ እነ​ር​ሱም አዶ​ን​ያ​ስን ተከ​ት​ለው ይረ​ዱት ነበር።


ዳዊ​ትም ካህ​ና​ቱን ሳዶ​ቅ​ንና አብ​ያ​ታ​ርን፥ ሌዋ​ው​ያ​ን​ንም፥ ኡር​ኤ​ልን፥ ዓሣ​ያን፥ ኢዮ​ኤ​ልን፥ ሰማ​ያን፥ ኤሊ​ኤ​ልን፥ አሚ​ና​ዳ​ብ​ንም ጠርቶ፦


የአ​ኪ​ጦ​ብም ልጅ ሳዶ​ቅና የአ​ብ​ያ​ታር ልጅ አቤ​ሜ​ሌክ ካህ​ናት ነበሩ፤ ሱሳ ጸሓፊ ነበረ።


እነሆ፥ ዐውሎ ነፋስ ከም​ድረ በዳ ድን​ገት መጥቶ ቤቱን በአ​ራት ማዕ​ዘኑ መታው፥ ቤቱም በብ​ላ​ቴ​ኖቹ ላይ ወደቀ፥ እነ​ር​ሱም ሞቱ፤ እኔም ብቻ​ዬን አም​ልጬ እነ​ግ​ርህ ዘንድ መጣሁ።”


የዔሊ ልጅ፥ የፊ​ን​ሐስ ልጅ፥ የዮ​ካ​ብድ ወን​ድም፥ የአ​ኪ​ጦብ ልጅ በሴሎ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ካህን የሆነ፥ ኤፉ​ድም የለ​በሰ አኪያ አብሮ ነበር፤ ሕዝ​ቡም ዮና​ታን እንደ ሄደ አላ​ወ​ቁም ነበር።


በዐ​ይ​ኖቹ የሚ​ፈ​ጽም በነ​ፍ​ሱም የሚ​ተጋ ሰውን ከመ​ሠ​ዊ​ያዬ አላ​ጠ​ፋም። ከቤ​ትህ የሚ​ቀ​ሩት ሰዎች ሁሉ ግን በጐ​ል​ማ​ሶች ሰይፍ ይሞ​ታሉ።


አብ​ያ​ታ​ርም ሳኦል የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ካህ​ናት እንደ ፈጀ ለዳ​ዊት ነገ​ረው።


እን​ዲ​ህም ሆነ፤ የአ​ቤ​ሜ​ሌክ ልጅ አብ​ያ​ታር ወደ ዳዊት ወደ ቂአላ በኰ​በ​ለለ ጊዜ ኤፉ​ዱን ይዞ ወርዶ ነበር።


ዳዊ​ትም ሳኦል በእ​ርሱ ለክ​ፋት ዝም እን​ደ​ማ​ይል ዐወቀ፤ ዳዊ​ትም ካህ​ኑን አብ​ያ​ታ​ርን፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ኤፉድ ወደ​ዚህ አምጣ” አለው።


ዳዊ​ትም የአ​ቤ​ሜ​ሌ​ክን ልጅ ካህ​ኑን አብ​ያ​ታ​ርን፥ “ኤፉ​ዱን አቅ​ር​ብ​ልኝ” አለው፤ አብ​ያ​ታ​ርም ኤፉ​ዱን ለዳ​ዊት አቀ​ረ​በ​ለት።


በዚ​ያም ቀን አንድ የብ​ን​ያም ሰው ከሰ​ልፍ እየ​በ​ረረ ወደ ሴሎ መጣ፤ ልብ​ሱም ተቀ​ድዶ ነበር፤ በራ​ሱም ላይ ትቢያ ነስ​ንሶ ነበር።


跟着我们:

广告


广告