Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ሳሙኤል 21:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 ዳዊ​ትም ለካ​ህኑ መልሶ፥ “ከሴ​ቶች ተለ​ይ​ተን ወደ መን​ገድ ከወ​ጣን ዛሬ ሦስ​ተኛ ቀና​ችን ነው። እኔም ብላ​ቴ​ኖ​ቼም ንጹ​ሓን ነን። ነገር ግን ዛሬ ሰው​ነቴ ንጽ​ሕት ስለ ሆነች ነው እንጂ ይህች መን​ገድ የነ​ጻች አይ​ደ​ለ​ችም” አለው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 ዳዊትም “እንደተለመደው ሁሉ ከወጣሁ ጊዜ ጀምሮ ሴቶች ከእኛ ተጠብቀዋል፤ ባልተቀደሰ ተልእኮ ውስጥ እንኳ የሰዎቹ ዕቃዎች የተቀደሱ ናቸው፤ ታዲያ ዛሬማ እንዴት!” ሲል ለካህኑ መለሰ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 ዳዊትም “እንደተለመደው ሁሉ ከወጣሁ ጊዜ ጀምሮ ሴቶች ከእኛ ተጠብቀዋል፤ በተራ ተልእኮ ውስጥ እንኳ የሰዎቹ ዕቃዎች የተቀደሱ ናቸው፤ ዛሬማ ምንኛ የበለጠ ቅዱሳን መሆን ይገባቸዋል?” ሲል መለሰ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 ዳዊትም ለካህኑ መልሶ “ከብላቴኖቼ ጋር ወደ ተልእኮ በምሄድበት ጊዜ ሁሉ ከሴቶች እንርቃለን፤ ተራ ተልእኮ እንኳ በምናደርግበት ጊዜ ብላቴኖቼ ንጽሕናቸውን ይጠብቃሉ። ዛሬማ ምንኛ የበለጠ ቅዱሳን መሆን ይገባቸዋል?”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 ዳዊትም ለካህኑ መልሶ፦ በእውነት ከወጣን ጀምረን እኛ ሰውነታችንን ከሴቶች ሦስት ቀን ጠብቀናል፥ የብላቴኖችም ዕቃ የተቀደሰች ናት፥ ስለዚህ ዛሬ እቃቸው የተቀደሰች በመሆንዋ እንጀራው እንደሚበላ እንጀራ ይሆናል አለው።

参见章节 复制




1 ሳሙኤል 21:5
10 交叉引用  

ሙሴም ከተ​ራ​ራው ወደ ሕዝቡ ወረደ፤ ሕዝ​ቡ​ንም ቀደሰ፤ ልብ​ሳ​ቸ​ው​ንም አጠቡ።


ሕዝ​ቡ​ንም፥ “ለሦ​ስ​ተ​ኛው ቀን ተዘ​ጋጁ፤ ወደ ሴቶ​ቻ​ች​ሁም አት​ቅ​ረቡ” አለ።


በገ​በ​ታም ላይ ኅብ​ስተ ገጹን ሁል​ጊዜ በፊቴ ታደ​ር​ጋ​ለህ።


ለአ​ሮ​ንና ለል​ጆ​ቹም ይሁን፤ በእ​ሳት ከተ​ደ​ረ​ገው ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቍር​ባን ለዘ​ለ​ዓ​ለም ሥር​ዐት ለእ​ርሱ ቅዱሰ ቅዱ​ሳን ነውና በተ​ቀ​ደሰ ስፍራ ይብ​ሉት።”


በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ካለው የቅ​ድ​ስና መሶብ አንድ የቂጣ እን​ጎቻ፥ አን​ድም የዘ​ይት እን​ጀራ፥ አን​ድም ስስ ቂጣ ወስዶ በስ​ቡና በቀኝ ወርቹ ላይ አኖ​ራ​ቸው።


ጌታ​ች​ንም እን​ዲህ አለው፥ “ተነ​ሥና ሂድ፤ በአ​ሕ​ዛ​ብና በነ​ገ​ሥ​ታት፥ በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆ​ችም ፊት ስሜን ይሸ​ከም ዘንድ ለእኔ የተ​መ​ረጠ ዕቃ አድ​ር​ጌ​ዋ​ለ​ሁና።


ለጸ​ሎት እን​ድ​ት​ተጉ ከም​ት​ስ​ማ​ሙ​በት ጊዜ ብቻ በቀር፥ ባልና ሚስት አት​ለ​ያዩ፤ ዳግ​መኛ ሰይ​ጣን ድል እን​ዳ​ያ​ደ​ር​ጋ​ችሁ በአ​ን​ድ​ነት ኑሩ፤ ሰው​ነ​ታ​ችሁ ደካማ ነውና ።


የእግዚአብሔር ፈቃድ እንዲህ ቢሆን፥ ክፉ ስለ ማድረግ ሳይሆን በጎ ስለ ማድረግ መከራን ብትቀበሉ ይሻላችኋልና።


跟着我们:

广告


广告