Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ሳሙኤል 20:42 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

42 ዮና​ታ​ንም ዳዊ​ትን፥ “በሰ​ላም ሂድ፤ እነሆ፥ እኛ ሁለ​ታ​ችን በእ​ኔና በአ​ንተ፥ በዘ​ሬና በዘ​ርህ መካ​ከል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለዘ​ለ​ዓ​ለም ምስ​ክር ይሁን ብለን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስም ተማ​ም​ለ​ናል” አለው። ዳዊ​ትም ተነ​ሥቶ ሄደ፤ ዮና​ታ​ንም ወደ ከተማ ገባ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

42 ዮናታንም ዳዊትን፤ “ ‘በአንተና በእኔ፣ በዘሮችህና በዘሮቼ መካከል እግዚአብሔር ለዘላለም ምስክር ነው’ ተባብለን ወዳጅነታችን እንዲጸና በእግዚአብሔር ስም ስለ ተማማልን እንግዲህ በሰላም ሂድ” አለው። ከዚያም ዳዊት ተነሥቶ ሄደ፤ ዮናታንም ወደ ከተማ ተመለሰ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

42 ዮናታንም ዳዊትን፤ “ ‘በአንተና በእኔ፥ በዘሮችህና በዘሮቼ መካከል ጌታ ለዘለዓለም ምስክር ነው’ ተባብለን ወዳጅነታችን እንዲጸና በጌታ ስም ስለ ተማማልን እንግዲህ በሰላም ሂድ” አለው። ከዚያም ዳዊት ተነሥቶ ሄደ፤ ዮናታንም ወደ ከተማ ተመለሰ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

42 ከዚህ በኋላ ዮናታን ዳዊትን እንዲህ አለው፦ “በሰላም ሂድ፤ እኔና አንተ በዘሬና በዘርህ መካከል እግዚአብሔር ለዘለዓለም ይሁን ብለን በእግዚአብሔር ስም ተማምለናል።” ዳዊት ተነሥቶ ሄደ፤ ዮናታንም ወደ ከተማ ተመለሰ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

42 ዮናታንም ዳዊትን፦ በደኅና ሂድ፥ እነሆ፥ እኛ ሁለታችን በእኔና በአንተ፥ በዘሬና በዘርህ መካከል ለዘላለም እግዚአብሔር ይሁን ብለን በእግዚአብሔር ስም ተማምለናል አለው። ዳዊትም ተነሥቶ ሄደ፥ ዮናታንም ወደ ከተማ ገባ።

参见章节 复制




1 ሳሙኤል 20:42
10 交叉引用  

ዳዊ​ትም፥ “ስለ ዮና​ታን ቸር​ነት አደ​ር​ግ​ለት ዘንድ ከሳ​ኦል ቤት የቀረ አንድ ሰው አለን?” አለ።


“እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊቱን ወደ አንተ ያንሣ፥ ሰላ​ም​ንም ይስ​ጥህ።


ሴቲ​ቱ​ንም አላት፥ “እም​ነ​ትሽ አድ​ኖ​ሻል፤ በሰ​ላም ሂጂ።”


የወ​ህኒ ቤቱ ጠባ​ቂም በሰማ ጊዜ ሄዶ ገዢ​ዎቹ “ይፈቱ” ብለው እንደ ላኩ ይህን ነገር ለጳ​ው​ሎ​ስና ለሲ​ላስ ነገ​ራ​ቸው፤ “አሁ​ንም ውጡና በሰ​ላም ሂዱ” አላ​ቸው።


ዔሊም፥ “በሰ​ላም ሂጂ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም አም​ላክ ከአ​ንቺ ጋር ይሁን የለ​መ​ን​ሽ​ው​ንም ልመና ሁሉ ይስ​ጥሽ” ብሎ መለ​ሰ​ላት።


ብሞ​ትም ቸር​ነ​ት​ህን እስከ ዘለ​ዓ​ለም ከቤቴ አት​ተው፤ ደግ​ሞም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የዳ​ዊ​ትን ጠላ​ቶች ሁሉ እያ​ን​ዳ​ን​ዱን ከም​ድር ፊት ባጠ​ፋ​ቸው ጊዜ የዮ​ና​ታን ስም በዳ​ዊት ቤት ይገ​ኛል።”


ዮና​ታ​ንም፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከዳ​ዊት ጠላ​ቶች እጅ ይፈ​ል​ገው” ብሎ ከዳ​ዊት ቤት ጋር ቃል ኪዳን አደ​ረገ።


ሁለ​ቱም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ቃል ኪዳን አደ​ረጉ፤ ዳዊ​ትም በቄኒ ውስጥ ተቀ​መጠ፤ ዮና​ታ​ንም ወደ ቤቱ ሄደ።


ዳዊ​ትም ያመ​ጣ​ች​ውን ከእ​ጅዋ ተቀ​ብሎ፥ “በሰ​ላም ወደ ቤትሽ ሂጂ፤ እነሆ፥ ቃል​ሽን እንደ ሰማሁ፥ ፊት​ሽ​ንም እን​ዳ​ከ​በ​ርሁ ተመ​ል​ከቺ” አላት።


跟着我们:

广告


广告