Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ሳሙኤል 20:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

21 እነ​ሆም፦ ሂድ ፍላ​ጻ​ዎ​ቹን ፈልግ ብዬ ብላ​ቴ​ና​ውን እል​ካ​ለሁ፤ ብላ​ቴ​ና​ው​ንም፦ እነሆ፥ ፍላ​ጻው ከአ​ንተ ወደ​ዚህ ነው፤ ይዘ​ኸው ወደ እኔ ና ያል​ሁት እንደ ሆነ፥ ሕያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን! ለአ​ንተ ሰላም ነውና ምንም ክፉ ነገር የለ​ብ​ህም።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 ከዚያም፣ ‘ሂድና ፍላጾቹን አምጣቸው’ ብዬ አንድ ልጅ እልካለሁ፤ ልጁንም፣ ‘እነሆ፤ ፍላጾቹ ያሉት፣ ከአንተ ወደዚህ ነው፤ ሄደህ አምጣቸው’ ያልሁት እንደ ሆነ፣ ሕያው እግዚአብሔርን! ክፉ ነገር አያገኝህም፤ አደጋም የለም፤ ውጣና ና።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 ከዚያም፥ ‘ሂድና ፍላጾቹን አምጣቸው’ ብዬ አንድ ልጅ እልካለሁ፤ ልጁንም፥ ‘እነሆ፤ ፍላጾቹ ያሉት፥ ከአንተ ወደዚህ ነው፤ ሄደህ አምጣቸው’ ያልሁት እንደሆነ፥ በሕያው ጌታ ስም! ክፉ ነገር አያገኝህም፤ ውጣና ና፤ አደጋ እንደማይኖርም እምልልሃለሁ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 ከዚያም በኋላ ፍላጻዎቹን እንዲያመጣ ልጁን እልካለሁ፤ ‘ፍላጻዎቹ ከአንተ ወደዚህ ናቸውና አምጣቸው!’ ካልሁት አንተ ከተደበቅኽበት ቦታ ልትወጣ ትችላለህ፤ ስለዚህ ምንም ችግር እንደማይደርስብህና ምንም አደጋ እንደሌለ በእግዚአብሔር ስም እምልልሃለሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

21 እነሆም፦ ሂድ ፍላጻዎችን ፈልግ ብዬ ብላቴናውን እልከዋለሁ፥ ብላቴናውንም፦ እነሆ፥ ፍላጻው ከአንተ ወደዚህ ነው፥ ይዘኸው ወደ እኔ ና ያልሁት እንደ ሆነ፥ ሕያው እግዚአብሔርን! ለአንተ ደኅንነት ነውና ምንም የለብህም።

参见章节 复制




1 ሳሙኤል 20:21
7 交叉引用  

በበ​ዓል ይምሉ ዘንድ ሕዝ​ቤን እን​ዳ​ስ​ተ​ማሩ በስሜ፦ ሕያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን! ብለው ይምሉ ዘንድ የሕ​ዝ​ቤን መን​ገድ ፈጽ​መው ቢማሩ፥ በዚያ ጊዜ በሕ​ዝቤ መካ​ከል ይመ​ሠ​ረ​ታሉ።


ሕያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን! ብሎ በእ​ው​ነ​ትና በቅ​ን​ነት፤ በጽ​ድ​ቅም ቢምል፥ አሕ​ዛብ በእ​ርሱ ይባ​ረ​ካሉ፤ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ያመ​ሰ​ግ​ናሉ።


እነ​ር​ሱም፦ ሕያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን! ቢሉ የሚ​ም​ሉት በሐ​ሰት ነው።”


ዳን ሆይ፥ ሕያው አም​ላ​ክ​ህን! ደግ​ሞም፦ ሕያው የቤ​ር​ሳ​ቤ​ህን አም​ላክ ብለው በሰ​ማ​ርያ መማ​ፀኛ የሚ​ምሉ፥ እነ​ርሱ ይወ​ድ​ቃሉ፥ ደግ​ሞም አይ​ነ​ሡም።”


እኔም በዓ​ላማ ላይ እወ​ረ​ው​ራ​ለሁ ብዬ ሦስት ፍላ​ጻ​ዎ​ችን ወደ ዓላ​ማው እወ​ረ​ው​ራ​ለሁ።


ብላ​ቴ​ና​ውን ግን፦ እነሆ፥ ፍላ​ጻው ከአ​ንተ ወዲያ ነው ያል​ሁት እንደ ሆነ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አሰ​ና​ብ​ቶ​ሃ​ልና መን​ገ​ድ​ህን ሂድ።


ብላ​ቴ​ና​ው​ንም፥ “ሮጠህ የም​ወ​ረ​ው​ራ​ቸ​ውን ፍላ​ጻ​ዎች ፈል​ግ​ልኝ” አለው። ብላ​ቴ​ና​ውም በሮጠ ጊዜ ዮና​ታን ፍላ​ጻ​ውን ወደ ማዶ አሳ​ልፎ ወረ​ወ​ረው።


跟着我们:

广告


广告