Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ሳሙኤል 20:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 ዮና​ታ​ንም ዳዊ​ትን እንደ ነፍሱ ይወ​ድድ ነበ​ርና እንደ ገና ማለ​ለት።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 ዮናታን ከፍቅሩ የተነሣ ዳዊት እንደ ገና እንዲምልለት አደረገ፤ ዳዊትን የሚወድደውም እንደ ራሱ አድርጎ ነበርና።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 ዮናታን ከፍቅሩ የተነሣ ዳዊትን የሚወደውም እንደ ራሱ አድርጎ ነበርና ዳዊት እንደገና እንዲምልለት አደረገ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 ዮናታን ዳዊትን እንደ ራሱ አድርጎ ይወደው ስለ ነበር “በእርግጥ እንደምትወደኝ ለመግለጥ እንደገና ማልልኝ” አለው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

17 ዮናታንም ዳዊትን እንደ ነፍሱ ይወድድ ነበርና እንደ ገና ማለለት።

参见章节 复制




1 ሳሙኤል 20:17
7 交叉引用  

ወን​ድሜ ዮና​ታን ሆይ፥ እኔ ስለ አንተ እጨ​ነ​ቃ​ለሁ፤ አንተ በእኔ ዘንድ እጅግ የተ​ወ​ደ​ድህ ነበ​ርህ፤ ከሴት ፍቅር ይልቅ ፍቅ​ርህ ለእኔ ድንቅ ነበረ።


ሁልጊዜ ወዳጅ ይኑርህ፥ ወንድሞች በመከራ ጊዜ ጠቃሚዎች ይሆናሉ፥ ስለዚህ ይወለዳሉና።


የሳ​ፋ​ንም ልጅ የአ​ኪ​ቃም ልጅ ጎዶ​ል​ያስ ለእ​ነ​ር​ሱና ለሰ​ዎ​ቻ​ቸው እን​ዲህ ብሎ ማለ፥ “ለከ​ለ​ዳ​ው​ያን ትገዙ ዘንድ አት​ፍሩ፤ በም​ድር ተቀ​መጡ፤ ለባ​ቢ​ሎ​ንም ንጉሥ ተገዙ፤ መል​ካ​ምም ይሆ​ን​ላ​ች​ኋል።


“የአ​ባ​ትህ ወይም የእ​ና​ትህ ልጅ ወን​ድ​ምህ ወይም ወንድ ልጅህ ወይም ሴት ልጅህ ወይም አብ​ራህ የም​ት​ተኛ ሚስ​ትህ ወይም እንደ ነፍ​ስህ ያለ ወዳ​ጅህ በስ​ውር፦ ና፥ ሄደን አን​ተም አባ​ቶ​ች​ህም የማ​ታ​ው​ቋ​ቸ​ውን ሌሎች አማ​ል​ክት እና​ም​ልክ ብሎ ቢያ​ስ​ትህ፥


እን​ዲ​ህም ሆነ፤ ዳዊት ለሳ​ኦል መን​ገ​ሩን በፈ​ጸመ ጊዜ የዮ​ና​ታን ነፍስ በዳ​ዊት ነፍስ ታሰ​ረች፤ ዮና​ታ​ንም እንደ ነፍሱ ወደ​ደው።


ዮና​ታ​ንም እንደ ነፍሱ ስለ ወደ​ደው ዮና​ታ​ንና ዳዊት ቃል ኪዳን አደ​ረጉ።


跟着我们:

广告


广告