Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ሳሙኤል 2:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 ችግ​ረ​ኛ​ውን ከመ​ሬት ያነ​ሣ​ዋል፤ ምስ​ኪ​ኑ​ንም ከጕ​ድፍ ያነ​ሣ​ዋል፤ ከሕ​ዝቡ መኳ​ን​ንት ጋር ያስ​ቀ​ም​ጠው ዘንድ፥ የክ​ብ​ር​ንም ዙፋን ያወ​ር​ሰው ዘንድ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 እርሱ ድኻውን ከትቢያ ያነሣል፤ ምስኪኑንም ከጕድፍ ከፍ ከፍ ያደርጋል፤ ከመኳንንቱ ጋራ ያስቀምጣቸዋል፤ የክብር ዙፋንም ያወርሳቸዋል። “የምድር መሠረቶች የእግዚአብሔር ናቸውና፣ ዓለምን በእነርሱ ላይ አድርጓል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 ወደ ልዑላንም ደረጃ ከፍ ሊያደርጋቸው፥ የክብርንም ዙፋን ሊያወርሳቸው፥ እርሱ ድኾችን ከትቢያ፥ ምስኪኖችንም ከዐመድ ላይ ያነሣል፤ የምድር መሠረቶች የጌታ ናቸውና፥ በእነርሱ ላይም ዓለምን አኖረ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 እርሱ ድኾችን ከትቢያ ምስኪኖችንም ከዐመድ ላይ ያነሣል፤ ወደ ልዑላንም ደረጃ ከፍ ያደርጋቸዋል፤ የክብርም ዙፋን ያወርሳቸዋል የምድርን መሠረቶች የሠራ እግዚአብሔር ነው፤ በእነርሱም ላይ ዓለምን የፈጠረ እርሱ ነው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 ከሕዝቡ መኳንንት ጋር ያስቀምጣቸው ዘንድ፥ የክብርንም ዙፋን ያወርሳቸው ዘንድ፥ ችግረኛውን ከመሬት ያስነሣል፥ ምስኪኑንም ከጉድፍ ያስነሣል፥ የምድር መሠረቶች የእግዚአብሔር ናቸውና፥ በእነርሱ ላይም ዓለምን አደረገ።

参见章节 复制




1 ሳሙኤል 2:8
31 交叉引用  

ፈር​ዖ​ንም ልኮ ዮሴ​ፍን አስ​ጠ​ራው፤ ከግ​ዞት ቤትም አወ​ጡት፤ ራሱ​ንም ላጩት፤ ልብ​ሱ​ንም ለወጡ፤ ወደ ፈር​ዖ​ንም ገባ።


አንተ በቤቴ ላይ ተሾም፤ ሕዝ​ቤም ሁሉ ለቃ​ልህ ይታ​ዘዝ፤ እኔም ከዙ​ፋኔ በቀር ከአ​ንተ የም​በ​ል​ጥ​በት የለም።”


አሁ​ንም ዳዊ​ትን ባሪ​ያ​ዬን እን​ዲህ በለው፦ ሁሉን የሚ​ገዛ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ በሕ​ዝቤ በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ አለቃ ትሆን ዘንድ ከበግ ጥበቃ ወሰ​ድ​ሁህ፤


“እኔ ከመ​ሬት አን​ሥቼ በሕ​ዝቤ በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ አለቃ አድ​ር​ጌ​ሃ​ለሁ፤ አንተ ግን በከ​ንቱ ጣዖ​ታ​ቸው ያስ​ቈ​ጡኝ ዘንድ ሕዝ​ቤን እስ​ራ​ኤ​ልን በአ​ሳ​ታ​ቸው በኢ​ዮ​ር​ብ​ዓም መን​ገድ ሄድህ፤


ተነ​ሥ​ቶም ወደ ቤቱ ገባ፥ ዘይ​ቱ​ንም በራሱ ላይ አፍ​ስሶ እን​ዲህ አለው፥ “የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሕዝብ በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ንጉሥ ትሆን ዘንድ ቀባ​ሁህ።


እን​ዲ​ህም አለ፥ “ከእ​ናቴ ማኅ​ፀን ራቁ​ቴን ወጥ​ቻ​ለሁ፥ ራቁ​ቴ​ንም ወደ ምድር እመ​ለ​ሳ​ለሁ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰጠ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ነሣ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እንደ ፈቀደ ሆነ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ብ​ሔር ስም የተ​ባ​ረከ ይሁን።”


ቍስ​ሉ​ንም ያክ​ክ​በት ዘንድ ገል ወሰደ፥ ከከ​ተ​ማም ወጥቶ በአ​መድ ላይ ተቀ​መጠ።


የሠ​ራ​ውን ድንቅ ዐስቡ፥ ተአ​ም​ራ​ቱን፥ የአ​ፉ​ንም ፍርድ።


አቤቱ፥ አን​ተን ታመ​ንሁ፤ ለዘ​ለ​ዓ​ለም አል​ፈር፤ ጠላ​ቶቼ በእኔ አይ​ሣ​ቁ​ብኝ።


በዚ​ያም የቀ​ስ​ትን ኀይል፥ ጋሻን፥ ጦር​ንና ሰል​ፍ​ንም ሰበረ፤ በዚ​ያም ቀን​ዶ​ችን ሰበረ።


አንተ በዘ​ለ​ዓ​ለም ተራ​ሮች ሆነህ በድ​ንቅ ታበ​ራ​ለህ።


አንተ ግን፥ ግሩም ነህ፤ ቍጣ​ህን ማን ይቃ​ወ​ማል?


በመ​ን​ግ​ሥቱ ችግ​ረኛ ቢሆ​ንም ከግ​ዞት ቤት ለመ​ን​ገሥ ወጥ​ቶ​አ​ልና።


በታ​መነ ስፍራ እንደ ችን​ካር እተ​ክ​ለ​ዋ​ለሁ፤ በአ​ባ​ቱም ቤት የክ​ብር ዙፋን አስ​ቀ​ም​ጠ​ዋ​ለሁ።


እር​ሱም የክ​ብሩ መን​ጸ​ባ​ረ​ቅና የመ​ልኩ ምሳሌ ሆኖ፥ ሁሉን በሥ​ል​ጣኑ ቃል እየ​ደ​ገፈ ኀጢ​አ​ታ​ች​ንን በራሱ ካነጻ በኋላ፥ በሰ​ማ​ያት በግ​ር​ማው ቀኝ ተቀ​መጠ።


የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ! ስሙ፤ እግዚአብሔር በእምነት ባለ ጠጎች እንዲሆኑ ለሚወዱትም ተስፋ ስለ እርሱ የሰጣቸውን መንግሥት እንዲወርሱ የዚህን ዓለም ድኾች አልመረጠምን?


መንግሥትም፥ ለአባቱም ለእግዚአብሔር ካህናት እንድንሆን ላደረገ፥ ለእርሱ ከዘላለም እስከ ዘላለም ድረስ ክብርና ኀይል ይሁን፤ አሜን።


ከእንግዲህም ወዲህ ሌሊት አይሆንም፤ ጌታ አምላክም በእነርሱ ላይ ያበራላቸዋልና የመብራት ብርሃንና የፀሐይ ብርሃን አያስፈልጋቸውም፤ ለዘላለምም እስከ ዘላለም ይነግሣሉ።


እኔ ደግሞ ድል እንደ ነሣሁ ከአባቴም ጋር በዙፋኑ ላይ እንደተቀመጥሁ፥ ድል ለነሣው ከእኔ ጋር በዙፋኔ ላይ ይቀመጥ ዘንድ እሰጠዋለሁ።


ሳሙ​ኤ​ልም ሳኦ​ልን አለው፥ “በፊቱ ምንም ታናሽ ብት​ሆን ለእ​ስ​ራ​ኤል ነገ​ዶች አለቃ አል​ሆ​ን​ህ​ምን? እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ንጉሥ ትሆን ዘንድ ቀባህ።


跟着我们:

广告


广告