Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ሳሙኤል 17:52 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

52 የእ​ስ​ራ​ኤ​ልና የይ​ሁዳ ሰዎ​ችም ተነ​ሥ​ተው እልል አሉ፤ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ን​ንም እስከ ጌትና እስከ አስ​ቀ​ሎና በር ድረስ አሳ​ደ​ዱ​አ​ቸው። የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም በድ​ኖ​ቻ​ቸው እስከ ጌትና እስከ አቃ​ሮን በሮች ድረስ በመ​ን​ገድ ላይ ወደቁ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

52 ከዚህ በኋላ የእስራኤልና የይሁዳ ሰዎች ተነሥተው እየፎከሩ ፍልስጥኤማውያንን እስከ ጋት መግቢያና እስከ አቃሮን በሮች ድረስ አሳደዷቸው። የፍልስጥኤማውያንም ሬሳ ከሽዓራይም አንሥቶ እስከ ጋት ከዚያም እስከ ዔቅሮን በሮች ባለው መንገድ ላይ ወድቆ ነበር።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

52 ከዚህ በኋላ የእስራኤልና የይሁዳ ሰዎች ተነሥተው እየፎከሩ ፍልስጥኤማውያንን እስከ ጋት መግቢያና እስከ ዔቅሮን በሮች ድረስ አሳደዷቸው። የፍልስጥኤማውያንም ሬሳ ከሸዓራይም አንሥቶ እስከ ጋትና ከዚያም እስከ ዔቅሮን በሮች ባለው መንገድ ላይ ወደቀ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

52 ከዚህ በኋላ የእስራኤልና የይሁዳ ሰዎች ድምፃቸውን ከፍ አድርገው እየፎከሩ እነርሱን በመከተል እስከ ጋትና እስከ ዔቅሮን የቅጽር በሮች ድረስ አሳደዱአቸው፤ የፍልስጥኤማውያን ሬሳ እስከ ጋትና እስከ ዔቅሮን ድረስ ወደ ሻዕራይም በሚያደርሰው መንገድ ሁሉ ወደቀ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

52 የእስራኤልና የይሁዳ ሰዎች ተነሥተው እልል አሉ፥ ፍልስጥኤማውያንንም እስከ ጌትና እስከ አስቀሎና በር ድረስ አሳደዱአቸው። ፍልስጥኤማውያንም ከሸዓራይም ጀምሮ እስከ ጌትና እስከ አቃሮን ድረስ በመንገድ ላይ የተመቱት ወደቁ።

参见章节 复制




1 ሳሙኤል 17:52
10 交叉引用  

የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሰዎች በጮኹ ጊዜ እርሱ ተነ​ሥቶ እጁ እስ​ከ​ሚ​ደ​ክ​ምና ከሰ​ይፉ ጋር እስ​ኪ​ጣ​በቅ ድረስ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንን መታ፤ በዚ​ያም ቀን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታላቅ መድ​ኀ​ኒት አደ​ረገ፤ ሕዝ​ቡም ከእ​ርሱ በኋላ የሞ​ቱ​ትን ለመ​ግ​ፈፍ ብቻ ተመ​ለሱ።


እነሆ፥ ክፉ ነገር አመ​ጣ​ብ​ሃ​ለሁ፤ እሳ​ትን ከኋ​ላህ አነ​ድ​ዳ​ለሁ፤ ዐጥር ተጠ​ግቶ እስ​ከ​ሚ​ሸን ድረስ የአ​ክ​ዓ​ብን ዘር አጠ​ፋ​ዋ​ለሁ፤ በእ​ስ​ራ​ኤል ውስጥ ያሉ​ት​ንም፥ የሌ​ሉ​ት​ንም እነ​ቅ​ላ​ለሁ፤


ድን​በ​ሩም ወደ አቃ​ሮን ደቡብ ይወ​ጣል፤ ወደ ሰሜን ወገን ይመ​ለ​ሳል፤ ድን​በሩ ወደ ሰቆት ይወ​ጣል፤ ወደ ደቡ​ብም ያል​ፋል፤ በሌ​ብና በኩ​ልም ይወ​ጣል፤ የድ​ን​በ​ሩም መውጫ በባ​ሕሩ አጠ​ገብ ነበረ።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሰዎች ከን​ፍ​ታ​ሌ​ምና ከአ​ሴር፥ ከም​ና​ሴም ሁሉ ተሰ​ብ​ስ​በው ምድ​ያ​ምን አሳ​ደዱ።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሰዎች ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንን ከማ​ሳ​ደድ ተመ​ል​ሰው ሰፈ​ራ​ቸ​ውን በዘ​በዙ።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ታቦት ወደ አስ​ቀ​ሎና ላኩ​አት። የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታቦት ወደ አስ​ቀ​ሎና በመ​ጣች ጊዜ አስ​ቀ​ሎ​ና​ው​ያን፥ “እኛ​ንና ሕዝ​ባ​ች​ንን ልታ​ስ​ገ​ድ​ሉን የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን አም​ላክ ታቦት ለምን አመ​ጣ​ች​ሁ​ብን?” ብለው ጮኹ።


ልከ​ውም የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንን አለ​ቆች ወደ እነ​ርሱ ሰበ​ሰ​ቡና፥ “በእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ ታቦት ምን እና​ድ​ርግ?” አሉ፤ የጌት ሰዎ​ችም፥ “የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ ታቦት ወደ እኛ ትዙር” ብለው መለሱ። የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ ታቦ​ትም ወደ ጌት ሄደች።


跟着我们:

广告


广告