Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ሳሙኤል 17:51 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

51 ዳዊ​ትም ሮጦ በፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ዊው ላይ ቆመ፤ ሰይ​ፉ​ንም ይዞ ከሰ​ገ​ባው መዘ​ዘው፤ ገደ​ለ​ውም፤ ራሱ​ንም ቈረ​ጠው። ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም ዋና​ቸው እንደ ሞተ ባዩ ጊዜ ሸሹ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

51 ዳዊት ሮጦ በላዩ ላይ ቆመ፤ ከዚያም የፍልስጥኤማዊውን ሰይፍ ከሰገባው መዝዞ አወጣው፤ እርሱንም ከገደለው በኋላ ራሱን በሰይፍ ቈረጠው። ፍልስጥኤማውያንም ጀግናቸው መሞቱን ባዩ ጊዜ ሸሹ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

51 ዳዊት ሮጦ በላዩ ላይ ቆመ፤ ከዚያም የፍልስጥኤማዊውን ሰይፍ ከሰገባው መዞ አወጣው፤ እርሱንም ከገደለው በኋላ ራሱን በሰይፍ ቆረጠው። ፍልስጥኤማውያንም ጀግናቸው መሞቱን ባዩ ጊዜ ሸሹ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

51 ወደ እርሱም ሮጦ በመሄድ በላዩ ላይ ቆመ፤ የጎልያድንም ሰይፍ ከሰገባው በመምዘዝ ራሱን ቈረጠው። ፍልስጥኤማውያንም የእነርሱ ዝነኛ ተዋጊ ጎልያድ መገደሉን ባዩ ጊዜ ሸሹ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

51 ዳዊትም ሮጦ በፍልስጥኤማዊው ላይ ቆመ፥ ሰይፉንም ይዞ ከሰገባው መዘዘው፥ ገደለውም፥ ራሱንም ቆረጠው። ፍልስጥኤማውያንም ዋናቸው እንደ ሞተ ባዩ ጊዜ ሸሹ።

参见章节 复制




1 ሳሙኤል 17:51
10 交叉引用  

እር​ሱም ልዩ የሆ​ነ​ውን ግብ​ፃዊ ሰው ገደለ፤ ግብ​ፃ​ዊ​ውም በእጁ ዛቢ​ያው እንደ ድል​ድይ ዕን​ጨት የሆነ ጦር ነበ​ረው፤ በና​ያስ ግን በትር ይዞ ወደ እርሱ ወረደ፤ ከግ​ብ​ፃ​ዊ​ውም እጅ ጦሩን ነጥቆ በገዛ ጦሩ ገደ​ለው።


ወደ ቤትም በገቡ ጊዜ ኢያ​ቡ​ስቴ በእ​ል​ፍኙ በም​ን​ጣፉ ላይ ተኝቶ ሳለ መቱት፥ ገደ​ሉ​ትም፤ ራሱ​ንም ቈር​ጠው ወሰ​ዱት፥ በዓ​ረ​ባም መን​ገድ ሌሊ​ቱን ሁሉ ሄዱ።


የእ​ሳት ኀይ​ልን አጠፉ፤ ከሰ​ይፍ ስለት አመ​ለጡ፤ ከድ​ካ​ማ​ቸው በረቱ፤ በጦ​ር​ነት ኀይ​ለ​ኞች ሆኑ፤ የባ​ዕድ ጭፍ​ሮ​ች​ንም አባ​ረሩ።


ልጆች በሥ​ጋና በደም አንድ ናቸ​ውና፤ እርሱ ደግሞ በዚህ ከእ​ነ​ርሱ ጋር አንድ ሆነ፤ ለእ​ነ​ር​ሱም እንደ ወን​ድም ሆነ​ላ​ቸው፤ መል​አከ ሞትን በሞቱ ይሽ​ረው ዘንድ፥ ይኸ​ውም ሰይ​ጣን ነው።


ዳዊ​ትም ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ዊ​ውን በወ​ን​ጭ​ፍና በድ​ን​ጋይ አሸ​ነ​ፈው፤ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ዊ​ው​ንም መትቶ ገደለ ፤ በዳ​ዊ​ትም እጅ ሰይፍ አል​ነ​በ​ረም።


ዳዊ​ትም ተነሣ በዚ​ያም ቀን ከሳ​ኦል ፊት ሸሸ፤ ወደ ጌትም ንጉሥ ወደ አን​ኩስ መጣ።


ካህ​ኑም፥ “በኤላ ሸለቆ የገ​ደ​ል​ኸው የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ዊው የጎ​ል​ያድ ሰይፍ እነሆ፥ በመ​ጐ​ና​ጸ​ፊያ ተጠ​ቅ​ልላ አለች፤ የም​ት​ወ​ስ​ዳት ከሆነ ውሰ​ዳት፤ ከእ​ር​ስዋ በቀር ሌላ ከዚህ የለ​ምና” አለው። ዳዊ​ትም፥ “ከእ​ር​ስዋ በቀር ሌላ ከሌለ እር​ስ​ዋን ስጠኝ” አለው። እር​ሱም ሰጠው።


አገ​ላ​ብ​ጠ​ውም የጦር መሣ​ሪ​ያ​ዎ​ችን ገፈፉ፤ በዙ​ሪ​ያ​ቸ​ውም ላሉ ለጣ​ዖ​ታ​ቱና ለሕ​ዝቡ የም​ሥ​ራች ይነ​ግሩ ዘንድ ወደ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ሀገር ሁሉ ላኩ።


跟着我们:

广告


广告