Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ሳሙኤል 15:33 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

33 ሳሙ​ኤ​ልም አጋ​ግን፥ “ሰይ​ፍህ ሴቶ​ችን ልጆች አልባ እን​ዳ​ደ​ረ​ገ​ቻ​ቸው እን​ዲሁ እና​ትህ በሴ​ቶች መካ​ከል ልጅ አልባ ትሆ​ና​ለች” አለ፥ ሳሙ​ኤ​ልም አጋ​ግን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት በጌ​ል​ጌላ ወጋው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

33 ሳሙኤልም፣ “ሰይፍህ ሴቶችን ልጅ አልባ እንዳደረገቻቸው፣ እናትህም በሴቶች መካከል ልጅ አልባ ትሆናለች” ሲል አጋግን ጌልገላ ላይ በእግዚአብሔር ፊት ቈራረጠው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

33 ሳሙኤልም፥ “ሰይፍህ ሴቶችን ልጅ አልባ እንዳደረገቻቸው፥ እናትህም በሴቶች መካከል ልጅ አልባ ትሆናለች” ሲል አጋግን ጌልገላ ላይ በጌታ ፊት ቆራረጠው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

33 በዚህም ጊዜ ሳሙኤል “የአንተ ሰይፍ ብዙዎች እናቶችን ልጅ አልባ እንዳደረገቻቸው፥ የአንተም እናት ልጅ አልባ ሆና ትቀራለች” አለው። ከዚህም በኋላ በጌልገላ በሚገኘው በእግዚአብሔር መሠዊያ ፊት አጋግን ቈራርጦ ጣለው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

33 ሳሙኤልም፦ ሰይፍህ ሴቶችን ልጆች አልባ እንዳደረገቻቸው እንዲሁ እናትህ በሴቶች መካከል ልጅ አልባ ትሆናለች አለ፥ ሳሙኤልም አጋግን በእግዚአብሔር ፊት በጌልገላ ቆራረጠው።

参见章节 复制




1 ሳሙኤል 15:33
17 交叉引用  

የሰ​ውን ደም የሚ​ያ​ፈ​ስስ ሁሉ ስለ​ዚያ ደም ፈንታ ደሙ ይፈ​ስ​ሳል፤ ሰውን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መልክ ፈጥ​ሬ​ዋ​ለ​ሁና።


ኤል​ያ​ስም ሕዝ​ቡን፥ “የበ​ዓ​ልን ነቢ​ያት ያዙ፤ ከእ​ነ​ርሱ አንድ ሰው እን​ኳን የሚ​ያ​መ​ልጥ አይ​ኑር፤” አላ​ቸው። ያዙ​አ​ቸ​ውም፤ ኤል​ያ​ስም ወደ ቂሶን ወንዝ ወስዶ፥ በዚያ እየ​ወጋ ጣላ​ቸው።


እን​ዲ​ህም ሆነ፤ ሙሴ እጁን በአ​ነሣ ጊዜ እስ​ራ​ኤል ድል ያደ​ርግ ነበር ፤ እጁ​ንም በአ​ወ​ረደ ጊዜ ዐማ​ሌቅ ድል ያደ​ርግ ነበር።


ዐይን በዐ​ይን፥ ጥርስ በጥ​ርስ፥ እጅ በእጅ፥ እግር በእ​ግር፥


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሥ​ዋ​ዕት በባ​ሶራ፥ ታላ​ቅም እርድ በኤ​ዶ​ም​ያስ ምድር አለ​ውና የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰይፍ በደም ተሞ​ል​ታ​ለች፤ በበግ ስብ፥ በፍ​የል ደምም፥ በአ​ው​ራም በግ ስብ ወፍ​ራ​ለች።


ስለ​ዚህ ልጆ​ቻ​ቸ​ውን ለራብ ስጥ፤ ለሰ​ይ​ፍም እጅ አሳ​ል​ፈህ ስጣ​ቸው፤ ሚስ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም የወ​ላድ መካ​ንና መበ​ለ​ቶች ይሁኑ፤ ወን​ዶ​ቻ​ቸ​ውም በሞት ይጥፉ፤ ጐል​ማ​ሶ​ቻ​ቸ​ውም በጦ​ር​ነት ጊዜ በሰ​ይፍ ይመቱ።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ሥራ በቸ​ልታ የሚ​ያ​ደ​ርግ ርጉም ይሁን፤ ሰይ​ፉ​ንም ከደም የሚ​ከ​ለ​ክል ርጉም ይሁን።


ስለ​ዚህ ነቢ​ያ​ቶ​ቻ​ች​ሁን አጨ​ድ​ኋ​ቸው፤ በአ​ፌም ቃል ገደ​ል​ኋ​ቸው፤ ፍር​ዴም እንደ ብር​ሃን ይወ​ጣል።


በዚ​ያም ተራራ ላይ የተ​ቀ​መጡ ዐማ​ሌ​ቃ​ዊና ከነ​ዓ​ናዊ ወረዱ፤ መት​ተ​ዋ​ቸ​ውም እስከ ኤርማ ድረስ አሳ​ደ​ዱ​አ​ቸው። ወደ ከተ​ማም ተመ​ለሱ።


ምሕረትን ለማያደርግ ምሕረት የሌለበት ፍርድ ይሆናልና፤ ምሕረትም በፍርድ ላይ ይመካል።


የቅዱሳንንና የነቢያትን ደም ስላፈሰሱ ደምን ደግሞ አጠጥተሃቸዋል፤ የሚገባቸው ነውና፤” ብሎ ሲናገር ሰማሁ።


እርስዋ እንደ ሰጠች መጠን ብድራት መልሱላት፤ እንደ ሥራዋም ሁለት እጥፍ ደርቡባት፤ በቀላቀለችው ጽዋ ሁለት እጥፍ አድርጋችሁ ቀላቅሉባት፤


አዶ​ኒ​ቤ​ዜ​ቅም፥ “የእ​ጆ​ቻ​ቸ​ውና የእ​ግ​ሮ​ቻ​ቸው አውራ ጣቶች የተ​ቈ​ረጡ ሰባ ነገ​ሥ​ታት ከገ​በ​ታዬ በታች ፍር​ፋሪ ይለ​ቅሙ ነበሩ፤ እኔ እን​ዳ​ደ​ረ​ግሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲሁ መለ​ሰ​ልኝ” አለ። ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ወሰ​ዱት፥ በዚ​ያም ሞተ።


በፊ​ቴም ወደ ጌል​ገላ ትወ​ር​ዳ​ለህ፤ እኔም እነሆ፥ የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕት አቀ​ርብ ዘንድ፥ የደ​ኅ​ን​ነ​ት​ንም መሥ​ዋ​ዕት እሠዋ ዘንድ ወደ አንተ እወ​ር​ዳ​ለሁ፤ እኔ ወደ አንተ እስ​ክ​መ​ጣና የም​ታ​ደ​ር​ገ​ውን እስ​ከ​ም​ነ​ግ​ርህ ድረስ ሰባት ቀን ትቈ​ያ​ለህ።”


ሳሙ​ኤ​ልም፥ “የአ​ማ​ሌ​ቅን ንጉሥ አጋ​ግን አም​ጡ​ልኝ” አለ። አጋ​ግም እየ​ተ​ን​ቀ​ጠ​ቀጠ ወደ እርሱ መጣ። አጋ​ግም፥ “በውኑ ሞት እን​ደ​ዚህ መራራ ነውን?” አለ።


跟着我们:

广告


广告