Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ሳሙኤል 15:30 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

30 ሳኦ​ልም፥ “በድ​ያ​ለሁ፤ አሁ​ንም በሕ​ዝቤ ሽማ​ግ​ሌ​ዎች ፊትና በእ​ስ​ራ​ኤል ፊት እባ​ክህ አክ​ብ​ረኝ፤ ለአ​ም​ላ​ክ​ህም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እሰ​ግድ ዘንድ ከእኔ ጋር ተመ​ለስ” አለው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

30 ሳኦልም መልሶ፣ “ኀጢአት ሠርቻለሁ፤ ነገር ግን በሕዝቤ አለቆች ፊትና በእስራኤል ፊት አክብረኝ፤ ለአምላክህ ለእግዚአብሔር እሰግድ ዘንድ እባክህ ዐብረኸኝ ተመለስ” አለው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

30 ሳኦልም መልሶ፥ “ኃጢአት ሠርቻለሁ፤ ነገር ግን በሕዝቤ አለቆች ፊትና በእስራኤል ፊት አክብረኝ፤ ለአምላክህ ለጌታ እሰግድ ዘንድ እባክህ አብረኸኝ ተመለስ” አለው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

30 ሳኦልም “በእርግጥ በደል ሠርቼአለሁ፤ ይሁን እንጂ ሌላው ቢቀር በሕዝቤ መሪዎችና በእስራኤል ሕዝብ ሁሉ ፊት አክብረኝ፤ ለአምላክህ ለእግዚአብሔር እሰግድ ዘንድ ከእኔ ጋር አብረህ ሂድ” ሲል ለመነው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

30 እርሱም፦ በድያለሁ፥ አሁን ግን በሕዝቤ ሽማግሌዎች ፊትና በእስራኤል ፊት፥ እባክህ፥ አክብረኝ፥ ለአምላክህም ለእግዚአብሔር እሰግድ ዘንድ ከእኔ ጋር ተምለስ አለው።

参见章节 复制




1 ሳሙኤል 15:30
10 交叉引用  

ዳዊ​ትም ናታ​ንን፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን በድ​ያ​ለሁ” አለው። ናታ​ንም ዳዊ​ትን አለው፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ደግሞ ኀጢ​አ​ት​ህን አር​ቆ​ል​ሃል፤ አት​ሞ​ት​ምም።


ፈር​ዖ​ንም ልኮ ሙሴ​ንና አሮ​ንን ጠራ፤ “አሁ​ንም በደ​ልሁ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጻድቅ ነው፤ እኔና ሕዝቤ ግን ኀጢ​አ​ተ​ኞች ነን።


ጌታም አለ፥ “ይህ ሕዝብ በከ​ን​ፈ​ሮቹ ያከ​ብ​ረ​ኛ​ልና፥ ልቡ ግን ከእኔ የራቀ ነውና፥ በከ​ንቱ ያመ​ል​ኩ​ኛል፤ ሰው ሠራሽ ትም​ህ​ር​ትም ያስ​ተ​ም​ራሉ፤


እነሆ፥ ነፍሱ ኰርታለች፥ በውስጡም ቅን አይደለችም፣ ጻድቅ ግን በእምነቱ በሕይወት ይኖራል።


ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ክብር ይልቅ የሰ​ውን ክብር ወደ​ዋ​ልና።


ከባ​ል​ን​ጀ​ራ​ችሁ ክብ​ርን የም​ት​መ​ርጡ፥ ከአ​ንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ክብ​ርን የማ​ትሹ እና​ንተ እን​ዴት ልታ​ምኑ ትች​ላ​ላ​ችሁ?


የአምልኮት መልክ አላቸው፤ ኀይሉን ግን ክደዋል፤ ከእነዚህ ደግሞ ራቅ።


ሳሙ​ኤ​ልም ከሳ​ኦል በኋላ ተመ​ለሰ፤ ሳኦ​ልም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰገደ።


ሳኦ​ልም፥ “በድ​ያ​ለሁ፤ ልጄ ዳዊት ሆይ! ተመ​ለስ፤ ዛሬ ነፍሴ በዐ​ይ​ንህ ፊት ከብ​ራ​ለ​ችና ከዚህ በኋላ ክፉ አላ​ደ​ር​ግ​ብ​ህም፤ እነሆ፥ ስን​ፍና እንደ አደ​ረ​ግ​ሁና፥ እጅግ ብዙም እንደ ሳትሁ ዐወ​ቅሁ” አለ።


跟着我们:

广告


广告