Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ሳሙኤል 15:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

20 ሳኦ​ልም ሳሙ​ኤ​ልን፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ስለ​ሰ​ማሁ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በላ​ከኝ መን​ገድ ሄጃ​ለሁ፤ የአ​ማ​ሌ​ቅን ንጉሥ አጋ​ግ​ንም አም​ጥ​ቻ​ለሁ፤ አማ​ሌ​ቃ​ው​ያ​ን​ንም ፈጽሜ አጥ​ፍ​ቻ​ለሁ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

20 ሳኦልም ሳሙኤልን መልሶ እንዲህ አለው፤ “እግዚአብሔርን ታዝዣለሁ፤ እግዚአብሔር በላከኝ መሠረት ሄጃለሁ፤ አማሌቃውያንን በሙሉ አጥፍቼ ንጉሣቸውን አጋግን አምጥቻለሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

20 ሳኦልም መልሶ እንዲህ አለ፤ “የጌታን ቃል ታዝዣለሁ፤ ጌታ በላከኝ መሠረት ሄጃለሁ፤ አማሌቃውያንን በሙሉ አጥፍቼ ንጉሣቸውን አጋግን አምጥቻለሁ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

20 ሳኦልም እንዲህ ሲል መለሰ፤ “እኔ የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ፈጽሜአለሁ፤ ባዘዘኝም መሠረት ዘምቻለሁ፤ ንጉሥ አጋግን ብቻ ማርኬ ሳመጣ ሌሎችን ዐማሌቃውያን ሁሉ ገድያለሁ፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

20 ሳኦልም ሳሙኤልን፦ የእግዚአብሔርን ቃል ሰምቻለሁ፥ እግዚአብሔርም በላከኝ መንገድ ሄጃለሁ፥ የአማሌቅን ንጉሥ አጋግን አምጥቻለሁ፥ አማሌቃውያንንም ፈጽሜ አጥፍቻለሁ።

参见章节 复制




1 ሳሙኤል 15:20
12 交叉引用  

እኔ ንጹሕ ነኝ፥ አል​በ​ደ​ል​ሁ​ምና፤ እኔ ጻድቅ ነኝ፥ ኀጢ​አ​ት​ንም አል​ሠ​ራ​ሁም።


ኢዮብ እን​ዲህ ብሎ​አ​ልና፦ እኔ ጻድቅ ነኝ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን ፍር​ዴን አስ​ወ​ገደ፤


“አንተ ተዋ​ቅ​ሰህ ምን ትላ​ለህ? ወይስ፦ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት እኔ ጻድቅ ነኝ የም​ትል አንተ ማን ነህ?


ወይም ፍር​ዴን መቃ​ወ​ም​ህን ተው፥ ጽድ​ቅህ እን​ድ​ት​ገ​ለጥ እንጂ እኔ በሌላ መን​ገድ የም​ፈ​ር​ድ​ብህ ይመ​ስ​ል​ሃ​ልን?


ጐበዙም “ይህንማ ሁሉ ከሕፃንነቴ ጀምሬ ጠብቄአለሁ፤ ደግሞስ የሚጐድለኝ ምንድር ነው?” አለው።


ራሱን ሊያ​ከ​ብር ባል​ን​ጀ​ራ​ው​ንም ሊንቅ ወድዶ፥ “ባል​ን​ጀ​ራዬ ማነው?” አለው።


ፈሪ​ሳ​ዊ​ውም ቆመና እን​ዲህ ብሎ ጸለየ፦ ‘አቤቱ እንደ ሌሎች ሰዎች፥ እንደ ቀማ​ኞ​ችና እንደ ዐመ​ፀ​ኞች፥ እንደ አመ​ን​ዝ​ሮ​ችም፥ ወይም እን​ደ​ዚህ ቀራጭ ያላ​ደ​ረ​ግ​ኸኝ አመ​ሰ​ግ​ን​ሃ​ለሁ።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ጽድቅ አያ​ው​ቁ​አ​ት​ምና በራ​ሳ​ቸ​ውም ጽድቅ ጸን​ተው ሊኖሩ ወደዱ፤ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጽድቅ ግን መገ​ዛት ተሳ​ና​ቸው።


ሳሙ​ኤ​ልም ወደ ሳኦል መጣ፤ ሳኦ​ልም፥ “አንተ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ባ​ረ​ክህ ሁን፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያዘ​ዘ​ውን ሁሉ ፈጽ​ሜ​አ​ለሁ” አለው።


አሁ​ንም ሄደህ አማ​ሌ​ቅ​ንና ኢያ​ሬ​ምን ምታ፤ ያላ​ቸ​ው​ንም ሁሉ ፈጽ​መህ አጥፋ፤ ከእ​ነ​ር​ሱም የም​ታ​ድ​ነው የለም። አጥ​ፋ​ቸው፤ መከ​ራም አጽ​ና​ባ​ቸው፤ የእ​ነ​ርሱ የሆ​ነ​ውን ሁሉ አጥፋ፤ ለያ​ቸ​ውም፤ አት​ማ​ራ​ቸ​ውም፤ ወን​ዱ​ንና ሴቱን፥ ብላ​ቴ​ና​ው​ንና ሕፃ​ኑን፥ በሬ​ው​ንና በጉን፥ ግመ​ሉ​ንና አህ​ያ​ውን ግደል።”


የአ​ማ​ሌ​ቅ​ንም ንጉሥ አጋ​ግን በሕ​ይ​ወቱ ማረ​ከው፤ የኢ​ያ​ሬ​ም​ንም ሕዝብ ሁሉ በሰ​ይፍ ስለት ፈጽሞ አጠ​ፋ​ቸው።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል አል​ሰ​ማ​ህ​ምና፥ በአ​ማ​ሌ​ቅም ላይ ታላቅ የሆነ ቍጣ​ውን አላ​ደ​ረ​ግ​ህ​ምና ስለ​ዚህ ዛሬ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይህን ነገር አድ​ር​ጎ​ብ​ሃል።


跟着我们:

广告


广告