1 ሳሙኤል 14:40 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)40 እስራኤልንም ሁሉ፥ “እናንተ አንድ ወገን ትሆናላችሁ፤ እኔና ልጄ ዮናታንም አንድ ወገን እንሆናለን” አለ። ሕዝቡም ሳኦልን፥ “ደስ የሚያሰኝህን አድርግ” አሉት። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም40 ሳኦልም እስራኤላውያንን ሁሉ፣ “እናንተ በዚያ በኩል ቁሙ፤ እኔና ልጄ ዮናታን ደግሞ በዚህ በኩል እንቆማለን” አላቸው። ሰዎቹም፣ “መልካም መስሎ የታየህን አድርግ” ብለው መለሱለት። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)40 ለእስራኤላውያን ሁሉ፥ “እናንተ በዚያ በኩል ቁሙ፤ እኔና ልጄ ዮናታን ደግሞ በዚህ በኩል እንቆማለን” አላቸው። ሰዎቹም፥ “መልካም መስሎ የታየህን አድርግ” አሉት። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም40 ከዚያም በኋላ ሳኦል “እናንተ ሁላችሁም በዚያ በኩል ቁሙ፤ እኔና ልጄ ዮናታን ደግሞ በዚህ በኩል እንቆማለን” አላቸው። እነርሱም “መልካም መስሎ የታየህን አድርግ” አሉት። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)40 እስራኤልንም ሁሉ፦ እናንተ በአንድ ወገን ሁኑ፥ እኔና ልጄ ዮናታንም በሌላ ወገን እንሆናለን አለ። ሕዝቡም ሳኦልን ደስ የሚያሰኝህን አድርግ አሉት። 参见章节 |