Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ሳሙኤል 14:35 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

35 ሳኦ​ልም በዚያ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሠ​ዊ​ያን ሠራ፤ ይኸ​ውም ሳኦል ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሠ​ራው የመ​ጀ​መ​ሪያ መሠ​ዊያ ነው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

35 ሳኦልም ለእግዚአብሔር መሠዊያ ሠራ፤ መሠዊያ ሲሠራም ይህ የመጀመሪያ ጊዜው ነበር።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

35 ሳኦልም ለጌታ መሠዊያ ሠራ፤ ለጌታ መሠዊያ ሲሠራም ይህ የመጀመሪያ ጊዜው ነበር።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

35 ሳኦልም በዚያ ለእግዚአብሔር መሠዊያ ሠራ፤ ይህም እርሱ የሠራው መሠዊያ የመጀመሪያው ነበር።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

35 ሳኦልም ለእግዚአብሔር መሠዊያን ሠራ፥ ይኸውም ለእግዚአብሔር የሠራው መጀመሪያ መሠዊያ ነው።

参见章节 复制




1 ሳሙኤል 14:35
10 交叉引用  

በዚ​ያም ዳዊት ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሠ​ዊያ ሠራ፤ የሚ​ቃ​ጠ​ልና የሰ​ላም መሥ​ዋ​ዕ​ት​ንም አቀ​ረበ። ሰሎ​ሞ​ንም በኋላ ዘመን በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ ጨመረ፤ ያን​ጊዜ አነ​ስ​ተኛ ነበ​ርና። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ስለ ሀገ​ሪቱ የተ​ለ​መ​ነ​ውን ሰማ፤ መቅ​ሠ​ፍ​ቱም ከእ​ስ​ራ​ኤል ተከ​ለ​ከለ።


እስ​ራ​ኤል ፈጣ​ሪ​ውን ረስ​ቶ​አል፤ መስ​ገ​ጃ​ዎ​ች​ንም ሠር​ቶ​አል፤ ይሁ​ዳም የተ​መ​ሸ​ጉ​ትን ከተ​ሞች አብ​ዝ​ቶ​አል፤ እኔ ግን በከ​ተ​ሞች ላይ እሳ​ትን እሰ​ድ​ዳ​ለሁ፤ መሠ​ረ​ቶ​ቻ​ቸ​ው​ንም ትበ​ላ​ለች።


የአምልኮት መልክ አላቸው፤ ኀይሉን ግን ክደዋል፤ ከእነዚህ ደግሞ ራቅ።


ወደ እግዚአብሔር ቅረቡ ወደ እናንተም ይቀርባል። እናንተ ኀጢአተኞች! እጆቻችሁን አንጹ፤ ሁለት አሳብም ያላችሁ እናንተ! ልባችሁን አጥሩ።


በነ​ጋ​ውም ሕዝቡ ማል​ደው ተነሡ፤ በዚ​ያም መሠ​ዊያ ሠሩ፤ የሚ​ቃ​ጠ​ልና የደ​ኅ​ን​ነት መሥ​ዋ​ዕ​ት​ንም አቀ​ረቡ።


ጌዴ​ዎ​ንም በዚያ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሠ​ዊያ ሠራ፤ ስሙ​ንም እስከ ዛሬ ድረስ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰላም” ብሎ ጠራው። እር​ሱም እስከ ዛሬ ድረስ ለኤ​ዝሪ አባት በሆ​ነ​ችው በኤ​ፍ​ራታ አለ።


ሳኦ​ልም፥ “በሕ​ዝቡ መካ​ከል እየ​ዞ​ራ​ችሁ፦ እያ​ን​ዳ​ንዱ ሰው በሬ​ው​ንና በጉን ወደ እኔ ያቅ​ርብ፥ በዚ​ህም እረ​ዱና ብሉ፤ ከደ​ሙም ጋር በመ​ብ​ላ​ታ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አት​በ​ድሉ” በሉ​አ​ቸው አለ። እያ​ን​ዳ​ን​ዱም ሰው ሁሉ በእጁ ያለ​ውን በዚ​ያች ሌሊት አቀ​ረበ፤ በዚ​ያም አረ​ደው።


ሳሙ​ኤ​ልም አንድ ድን​ጋይ ወስዶ በመ​ሴ​ፋና በአ​ሮ​ጌው ከተማ መካ​ከል አኖ​ረው፤ ስሙ​ንም፥ “እስከ አሁን ድረስ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ረድ​ቶ​ናል” ሲል “አቤ​ን​ኤ​ዜር” ብሎ ጠራው። እብነ ረድ​ኤት ማለት ነው።


ቤቱም በዚያ ነበ​ረና ወደ አር​ማ​ቴም ይመ​ለስ ነበር፤ በዚ​ያም በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ይፈ​ርድ ነበር፤ በዚ​ያም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሠ​ዊያ ሠራ።


ሳሙ​ኤ​ልም አንድ የበግ ጠቦት ወስዶ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፈጽሞ የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት አድ​ርጎ ከሕ​ዝቡ ጋር አቀ​ረ​በው፤ ሳሙ​ኤ​ልም ስለ እስ​ራ​ኤል ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጮኸ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሰማው።


跟着我们:

广告


广告