Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ሳሙኤል 13:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

19 ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም፥ “ዕብ​ራ​ው​ያን ሰይ​ፍና ጦር እን​ዳ​ይ​ሠሩ” ብለው ነበ​ርና በእ​ስ​ራ​ኤል ምድር ሁሉ ብረት ሠሪ አል​ተ​ገ​ኘም።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 ፍልስጥኤማውያን፣ “ዕብራውያን ሰይፍ ወይም ጦር ለራሳቸው አይሥሩ” ብለው ስለ ነበር፣ በመላው የእስራኤል ምድር የእጅ ጥበብ ባለሙያ አልተገኘም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

19 በመላው የእስራኤል ምድር ብረት አቅልጦ ሠሪ አይገኝም ነበር፤ ምክንያቱም ፍልስጥኤማውያን፥ “ዕብራውያን ሰይፍ ወይም ጦር ለራሳቸው አይሥሩ” ብለው ስለ ነበር ነው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

19 ዕብራውያን ሰይፍና ጦር እንዳይሠሩ ፍልስጥኤማውያን ቊጥጥር ያደርጉባቸው ስለ ነበር በዚያን ዘመን በእስራኤል ብረት አቅልጠው የሚሠሩ ጠቢባን አልነበሩም፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

19 ፍልስጥኤማውያንም፦ ዕብራውያን ሰይፍና ጦር እንዳይሠሩ ብለው ነበርና በእስርኤል ምድር ሁሉ ብረተ ሠሪ አልተገኘም።

参见章节 复制




1 ሳሙኤል 13:19
6 交叉引用  

ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ም​ንም አጠ​ፋት፥ አለ​ቆ​ቹ​ንም ሁሉ፥ ጽኑ​ዓ​ኑ​ንና ኀያ​ላ​ኑን ሁሉ፥ ጠራ​ቢ​ዎ​ቹ​ንም ሁሉ፥ ብረት ሠራ​ተ​ኞ​ቹ​ንም ሁሉ ዐሥር ሺህ ምር​ኮ​ኞ​ችን ሁሉ አፈ​ለሰ፤ ከሀ​ገሩ ድሆች በቀር ማንም አል​ቀ​ረም።


እነሆ፥ ፍሙን በወ​ናፍ እን​ደ​ሚ​ያ​ናፋ፥ ለሥ​ራ​ውም መሣ​ሪያ እን​ደ​ሚ​ያ​ወጣ ብረት ሠሪ የፈ​ጠ​ር​ሁሽ አይ​ደ​ለም፤ እኔ ግን ለመ​ል​ካም ፈጠ​ር​ሁሽ እንጂ ለጥ​ፋት አይ​ደ​ለም።


የባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ናቡ​ከ​ደ​ነ​ፆር የይ​ሁ​ዳን ንጉሥ የኢ​ዮ​አ​ቄ​ምን ልጅ ኢኮ​ን​ያ​ንን፥ የይ​ሁ​ዳ​ንም አለ​ቆች፥ ብል​ሃ​ተ​ኞ​ች​ንና እስ​ረ​ኞ​ችን፥ ጓደ​ኞ​ቻ​ቸ​ው​ንም ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ማርኮ ወደ ባቢ​ሎን ከአ​ፈ​ለ​ሳ​ቸው በኋላ፥ እነሆ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መቅ​ደስ ፊት የተ​ቀ​መጡ ሁለት የበ​ለስ ቅር​ጫ​ቶ​ችን አሳ​የኝ።


ይህም የሆ​ነው ንጉሡ ኢኮ​ን​ያ​ንና እቴ​ጌ​ዪቱ፥ ጃን​ደ​ረ​ቦ​ቹም፥ የይ​ሁ​ዳና የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም አለ​ቆች ነጻ​ዎ​ችና እሥ​ረ​ኞች፥ ብል​ሃ​ተ​ኞ​ችና ብረት ሠራ​ተ​ኞ​ችም ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ከወጡ በኋላ ነው።


አዲ​ሶች አማ​ል​ክ​ትን መረጡ፤ በዚያ ጊዜ ሰልፍ በበ​ሮች ሆነ፤ በአ​ርባ ሺህ በእ​ስ​ራ​ኤል ዘንድ ጦርና ጋሻ አል​ታ​ዩም።


እስ​ራ​ኤ​ልም ሁሉ ማረ​ሻ​ው​ንና ማጭ​ዱን፥ መጥ​ረ​ቢ​ያ​ው​ንና መቈ​ፈ​ሪ​ያ​ውን ይስሉ ዘንድ ወደ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ይወ​ርዱ ነበር።


跟着我们:

广告


广告