Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ሳሙኤል 12:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 ሳሙ​ኤ​ልም፥ “በእጄ ምንም እን​ዳ​ላ​ገ​ኛ​ችሁ ዛሬ በዚ​ህች ቀን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ምስ​ክር ነው፤ እርሱ የቀ​ባ​ውም ምስ​ክር ነው” አላ​ቸው፤ እነ​ር​ሱም፥ “አዎ ምስ​ክር ነው” አሉ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 ሳሙኤልም፣ “በእጄ ምንም እንዳላገኛችሁ እግዚአብሔርና እርሱ የቀባው ዛሬ በእናንተ ላይ ምስክሮች ናቸው” አላቸው። እነርሱም፣ “እርሱ ምስክር ነው” አሉ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 ሳሙኤልም፥ “በእጄ ምንም እንዳላገኛችሁ ጌታና እርሱ የቀባው ዛሬ በእናንተ ላይ ምስክሮች ናቸው” አላቸው። እነርሱም፥ “እርሱ ምስክር ነው” አሉ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 ሳሙኤልም “እንግዲህ ዛሬ በፊታችሁ ንጹሕ ሆኜ ስለ መገኘቴ እግዚአብሔርና እርሱ የመረጠው ንጉሥ ምስክሮች ናቸው” አለ። ሕዝቡም “አዎ! እግዚአብሔር ምስክር ነው!” ሲሉ መለሱለት።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 እርሱም፦ በእጄ ምንም እንዳላገኛችሁ እግዚአብሔርና እርሱ የቀባው ዛሬ በእናንተ ላይ ምስክሮች ናቸው አላቸው፥ እነርሱም፦ ምስክር ነው አሉ።

参见章节 复制




1 ሳሙኤል 12:5
14 交叉引用  

ልጆ​ችን ብት​በ​ድ​ላ​ቸው ወይም በላ​ያ​ቸው ላይ ሚስ​ቶ​ችን ብታ​ገ​ባ​ባ​ቸው እነሆ፥ ከእኛ ጋር ያለ ሰው እን​ደ​ሌለ አስ​ተ​ውል፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእ​ኔና በአ​ንተ መካ​ከል ምስ​ክር ነው።”


መሬት ሥጋ​ዬን ይሸ​ፍ​ነው ይሆን? ደሜስ ይፈ​ስስ ይሆን? የም​ጮ​ህ​በ​ትስ ቦታ አላ​ገኝ ይሆን?


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ይህን ቃል ለኢ​ዮብ ከተ​ና​ገረ በኋላ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቴማ​ና​ዊ​ውን ኤል​ፋ​ዝን እን​ዲህ አለው፥ “እንደ ባሪ​ያዬ እንደ ኢዮብ አን​ዲት ቅን ነገ​ርን በፊቴ አል​ተ​ና​ገ​ራ​ች​ሁ​ምና አን​ተና ሁለቱ ባል​ን​ጀ​ሮ​ችህ በድ​ላ​ች​ኋል።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን በጠ​ራ​ሁት ጊዜ ከጠ​ላ​ቶቼ እድ​ና​ለሁ።


የሰ​ረ​ቀው ደኅና ሆኖ በእጁ ቢገኝ፥ በሬ ወይም በግ ቢሆን፥ የሰ​ረ​ቀ​ውን ያህል ሁለት እጥፍ ይክ​ፈል።


ጲላ​ጦ​ስም፥ “እው​ነት ምን​ድ​ነው?” አለው፤ ይህ​ንም ተና​ግሮ ዳግ​መኛ ወደ አይ​ሁድ ወጣና እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “እኔ አን​ዲት ስን​ኳን በደል አላ​ገ​ኘ​ሁ​በ​ትም።


ታላቅ ውካ​ታም ሆነ፤ ከፈ​ሪ​ሳ​ው​ያ​ንም ወገን የሆኑ ጸሐ​ፍት ተነ​ሥ​ተው ይጣ​ሉና ይከ​ራ​ከሩ ጀመሩ፤ “በዚህ ሰው ላይ ያገ​ኘ​ነው ክፉ ነገር የለም፤ መን​ፈስ ወይም መል​አክ ተና​ግ​ሮት እንደ ሆነ እንጃ፥ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጋር አን​ጣላ” አሉ።


እን​ዲሁ እኔም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርና በሰው ፊት ሁል​ጊዜ የማ​ታ​ወ​ላ​ውል ሕሊና ትኖ​ረኝ ዘንድ እጋ​ደ​ላ​ለሁ።


ወይም እኔ በሸ​ንጎ ቆሜ ሳለሁ ያገ​ኙ​ብኝ በደል እንደ አለ እነ​ዚህ ራሳ​ቸው ይመ​ስ​ክሩ።


የሚ​ያ​ጠ​ራ​ጥ​ረ​ኝና ትዝ የሚ​ለኝ ነገር የለም፤ በዚ​ህም ራሴን አላ​መ​ጻ​ድ​ቅም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይመ​ረ​ም​ረ​ኛ​ልና።


በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቸር​ነ​ትና ይቅ​ርታ መመ​ኪ​ያ​ች​ንና የነ​ፃ​ነ​ታ​ችን ምስ​ክር ይህቺ ናትና፥ በሥ​ጋዊ ጥበብ ሳይ​ሆን፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጸጋ በዚህ ዓለም፥ ይል​ቁ​ንም በእ​ና​ንተ ዘንድ ተመ​ላ​ለ​ስን።


እነ​ር​ሱም ሳሙ​ኤ​ልን፥ “ግፍም አላ​ደ​ረ​ግ​ህ​ብ​ንም፤ የቀ​ማ​ኸን የለም፤ አላ​ሠ​ቃ​የ​ኸ​ንም፤ ከእ​ኛም ከማ​ንም እጅ ምንም አል​ወ​ሰ​ድ​ህም” አሉት።


ዳዊ​ትም አቢ​ሳን፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በቀ​ባው ላይ እጁን የሚ​ዘ​ረጋ ንጹሕ አይ​ሆ​ን​ምና አት​ግ​ደ​ለው” አለው።


跟着我们:

广告


广告