Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ሳሙኤል 10:25 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

25 ሳሙ​ኤ​ልም የን​ጉ​ሡን ሥር​ዐት ነገ​ራ​ቸው፤ በመ​ጽ​ሐ​ፍም ጻፈው፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት አኖ​ረው። ሳሙ​ኤ​ልም ሕዝ​ቡን ሁሉ ወደ እየ​ቤ​ታ​ቸው አሰ​ና​በ​ታ​ቸው። ሕዝ​ቡም ሁሉ ወደ እየ​ቤ​ታ​ቸው ሄዱ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

25 ሳሙኤልም ለንጉሥ የሚገባውን ወግና ሥርዐት ለሕዝቡ ገልጾ ካስረዳ በኋላ በመጽሐፍ ጽፎ በእግዚአብሔር ፊት አኖረው። ከዚህ በኋላ ሳሙኤል እያንዳንዱን ሰው ወደየቤቱ አሰናበተ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

25 ሳሙኤልም ለንጉሥ የሚገባውን ተግባርና ሥርዓት ለሕዝቡ ገልጦ ካስረዳ በኋላ በመጽሐፍ ጽፎ በጌታ ፊት አኖረው። ከዚህ በኋላ ሳሙኤል እያንዳንዱን ሰው ወደየቤቱ አሰናበተ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

25 ሳሙኤልም ለሕዝቡ፥ ለአንድ ንጉሥ ሊደረግለት የሚገባውን ሥርዓት አስረዳቸው፤ ያንንም በመጽሐፍ ጽፎ በእግዚአብሔር ፊት አስቀመጠው፤ ከዚያም በኋላ ሕዝቡን ሁሉ ወደየቤቱ አሰናበተ፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

25 ሳሙኤልም የመንግሥቱን ወግ ነገረ፥ በመጽሐፍም ጻፈው በእግዚአብሔርም ፊት አኖረው። ሳሙኤልም ሕዝቡን ሁሉ ወደ እየቤታቸው አሰናበታቸው።

参见章节 复制




1 ሳሙኤል 10:25
13 交叉引用  

ዮዳ​ሄም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሕዝብ ይሆኑ ዘንድ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርና በን​ጉሡ፥ በሕ​ዝ​ቡም መካ​ከል ቃል ኪዳን አደ​ረገ፤ ደግ​ሞም በን​ጉ​ሡና በሕ​ዝቡ መካ​ከል ቃል ኪዳን አደ​ረገ።


“ይህን የሕግ መጽ​ሐፍ ውሰዱ፤ በዚ​ያም በእ​ና​ንተ ላይ ምስ​ክር እን​ዲ​ሆን በአ​ም​ላ​ካ​ችሁ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ኪዳን ታቦት አጠ​ገብ አኑ​ሩት።


ለገዦችና ለባለ ሥልጣኖች የሚገዙና የሚታዘዙ፥ ለበጎ ሥራ ሁሉ የተዘጋጁ፥ ማንንም የማይሰድቡ፥ የማይከራከሩ፥ ገሮች፥ ለሰው ሁሉ የዋህነትን ሁሉ የሚያሳዩ እንዲሆኑ ኣሳስባቸው።


ኢያ​ሱም መረ​ቃ​ቸው፤ አሰ​ና​በ​ታ​ቸ​ውም፤ ወደ ቤታ​ቸ​ውም ሄዱ።


ሳሙ​ኤ​ልም ሕዝ​ቡን፥ “ኑ፤ ወደ ጌል​ገላ እን​ሂድ፤ በዚ​ያም መን​ግ​ሥ​ቱን እና​ጽና” አላ​ቸው።


አሁ​ንም ቃላ​ቸ​ውን ስማ፤ ነገር ግን ጽኑ ምስ​ክር መስ​ክ​ር​ባ​ቸው፤ በእ​ነ​ር​ሱም ላይ የሚ​ነ​ግ​ሠ​ውን የን​ጉ​ሡን ሥር​ዐት ንገ​ራ​ቸው።”


跟着我们:

广告


广告