1 ሳሙኤል 10:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)2 ዛሬ ከእኔ በተለየህ ጊዜ በብንያም ግዛት በቤቴል አውራጃ በራሔል መቃብር አጠገብ ሁለት ሰዎች እየቸኰሉ ሲሄዱ ታገኛለህ፤ እነርሱም፦ ልትፈልጉአቸው ሂዳችሁ የነበራችሁላቸው አህዮች ተገኝተዋል፤ እነሆም፥ አባትህ ስለ አህዮቹ ማሰብ ትቶ፦ የልጄን ነገር እንዴት አደርጋለሁ? እያለ ስለ እናንተ ይጨነቃል ይሉሃል። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም2 ዛሬ ከእኔ ተለይተህ ስትሄድ፣ በብንያም ወሰን ላይ በምትገኘው ጼልጻህ በተባለች ስፍራ በራሔል መቃብር አጠገብ ሁለት ሰዎች ታገኛለህ። እነርሱም፣ ‘የምትፈልጋቸው አህዮች ተገኝተዋል፤ አሁን አባትህ ስለ አህዮቹ ማሰቡን ትቶ፣ “ስለ ልጄ ምን ባደርግ ይሻለኛል?” እያለ በመጨነቅ ላይ ነው’ ይሉሃል። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)2 ዛሬ ከእኔ ተለይተህ ስትሄድ፥ በብንያም ወሰን ላይ በምትገኘው ጼልጻህ በተባለች ስፍራ በራሔል መቃብር አጠገብ ሁለት ሰዎች ታገኛለህ። እነርሱም፥ ‘የምትፈልጋቸው አህዮች ተገኝተዋል፤ አሁን አባትህ ስለ አህዮቹ ማሰቡን ትቶ፥ ስለ ልጄ ምን ባደርግ ይሻለኛል?’ እያለ በመጨነቅ ላይ ነው” ይሉሃል። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም2 ዛሬ ከእኔ ተለይተህ በምትሄድበት ጊዜ፥ በብንያም ግዛት በሚገኘው ጼልጻሕ ተብሎ በሚጠራው ስፍራ ባለው በራሔል መቃብር አጠገብ ሁለት ሰዎች ታገኛለህ፤ እነርሱም ስትፈልጋቸው የነበሩ አህዮች መገኘታቸውንና አባትህም ስለ እነርሱ ማሰቡን ትቶ ስለ አንተ በመጨነቅ ‘እንግዲህ ስለ ልጄ ምን ላድርግ’ እያለ በመጠየቅ ላይ መሆኑን ይነግሩሃል። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)2 ዛሬ ከእኔ በተለየህ ጊዜ በብንያም ዳርቻ በጼልጻህ አገር ባለው በራሔል መቃብር አጠገብ ሁለት ሰዎች ታገኛለህ፥ እነርሱም፦ ልትሻቸው ሄደህ የነበርህላቸው አህዮች ተገኝተዋል፥ እነሆም፥ አባትህ ስለ አህዮች ማሰብ ትቶ፥ የልጄን ነገር እንዴት አደርጋለሁ? እያለ ስለ እናንተ ይጨነቃል ይሉሃል። 参见章节 |