Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ሳሙኤል 1:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

21 ሰው​ዬ​ውም ሕል​ቃና ከቤተ ሰቡ ሁሉ ጋር የዓ​መ​ቱን መሥ​ዋ​ዕ​ትና ስእ​ለ​ቱን፥ የም​ድ​ሩ​ንም ዐሥ​ራት ሁሉ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያቀ​ርብ ዘንድ ወጣ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 ሰውየውም ሕልቃና ለእግዚአብሔር ዓመታዊውን መሥዋዕት ለመሠዋት ስእለቱን ለማድረስ ቤተ ሰቡን ሁሉ ይዞ ወደ ሴሎ ወጣ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 ሰውዬውም ሕልቃና ቤተሰቡን ሁሉ ይዞ ለጌታ ዓመታዊውን መሥዋዕት ለመሠዋት፥ ስእለቱንም ለማድረስ ወደ ሴሎ ወጣ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 ሕልቃና ከቤተሰቡ ጋር ዓመታዊ መሥዋዕትና ስእለት ወደ እግዚአብሔር ለማቅረብ ወደ ሴሎ ወጣ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

21 ሰውዮውም ሕልቃና ከቤተ ሰቡ ሁሉ ጋር የዓመቱን መሥዋዕትና ስእለቱን ለእግዚአብሔር ያቀርብ ዘንድ ወጣ።

参见章节 复制




1 ሳሙኤል 1:21
7 交叉引用  

ጽድ​ቅ​ንና ፍር​ድን በማ​ድ​ረግ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መን​ገድ ይጠ​ብቁ ዘንድ፥ ልጆ​ቹ​ንና ቤቱን ያዝ​ዛ​ቸው ዘንድ እን​ዳ​ለው አው​ቃ​ለ​ሁና፤ ይህም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለአ​ብ​ር​ሃም የተ​ና​ገ​ረ​ውን ሁሉ ያደ​ር​ግ​ላ​ቸው ዘንድ ነው።”


በመ​ከ​ራዬ ቀን ፊት​ህን ከእኔ አት​መ​ልስ፤ ጆሮ​ህን ወደ እኔ አዘ​ን​ብል፤ በጠ​ራ​ሁህ ቀን ፈጥ​ነህ ስማኝ።


በዚ​ያን ጊዜ አም​ላ​ካ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስሙ ይጠ​ራ​በት ዘንድ ወደ​ዚያ ወደ መረ​ጠው ስፍራ፥ እኔ የማ​ዝ​ዛ​ች​ሁን ሁሉ፥ የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕ​ታ​ች​ሁን፥ ቍር​ባ​ና​ች​ሁ​ንም፥ ዐሥ​ራ​ታ​ች​ሁ​ንም፥ ከእ​ጃ​ችሁ ሥራ ቀዳ​ም​ያ​ቱን የተ​መ​ረ​ጠ​ው​ንም መባ​ች​ሁን ሁሉ፥ ለአ​ም​ላ​ካ​ች​ሁም የተ​ሳ​ላ​ች​ሁ​ትን ሁሉ ውሰዱ።


ወደ​ዚ​ያም የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕ​ታ​ች​ሁን፥ ቍር​ባ​ና​ች​ሁ​ንም፥ ዐሥ​ራ​ታ​ች​ሁ​ንም፥ ቀዳ​ም​ያ​ታ​ች​ሁን፥ ስዕ​ለ​ታ​ች​ሁ​ንም፥ በፈ​ቃ​ዳ​ችሁ የም​ታ​ቀ​ር​ቡ​ትን፥ የላ​ማ​ች​ሁ​ንና የበ​ጋ​ች​ሁ​ንም በኵ​ራት ውሰዱ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ታመ​ልኩ ዘንድ ባት​ወ​ድዱ ግን፥ አባ​ቶ​ቻ​ችሁ በወ​ንዝ ማዶ ሳሉ ያመ​ለ​ኩ​አ​ቸ​ውን አማ​ል​ክት፥ ወይም በም​ድ​ራ​ቸው ያላ​ች​ሁ​ባ​ቸ​ውን የአ​ሞ​ሬ​ዎ​ና​ው​ያ​ንን አማ​ል​ክት ታመ​ልኩ እንደ ሆነ፥ የም​ታ​መ​ል​ኩ​ትን ዛሬ ምረጡ። እኔና ቤቴ ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እና​መ​ል​ካ​ለን፤ እርሱ ቅዱስ ነውና።”


ያም ሰው በሴሎ ይሰ​ግድ ዘንድ፥ ለሠ​ራ​ዊት ጌታም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይሠዋ ዘንድ ከከ​ተ​ማው ከአ​ር​ማ​ቴም በየ​ዓ​መቱ ይወጣ ነበር። የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ካህ​ናት ሁለቱ የዔሊ ልጆች አፍ​ኒ​ንና ፊን​ሐስ በዚያ ነበሩ።


እና​ቱም ታናሽ መደ​ረ​ቢያ ሠራ​ች​ለት፤ በየዓ​መ​ቱም መሥ​ዋ​ዕት ለመ​ሠ​ዋት ከባ​ልዋ ጋር ስት​ወጣ ትወ​ስ​ድ​ለት ነበር።


跟着我们:

广告


广告