Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ሳሙኤል 1:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

20 የመ​ው​ለ​ጃ​ዋም ወራት በደ​ረሰ ጊዜ ሐና ወንድ ልጅ ወለ​ደች፤ እር​ስ​ዋም፥ “ከሠ​ራ​ዊት ጌታ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለም​ኜ​ዋ​ለሁ” ስትል ስሙን “ሳሙ​ኤል” ብላ ጠራ​ችው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

20 ስለዚህ ሐና ፀነሰች፤ የእርግዝናዋ ወራት በተፈጸመ ጊዜም ወንድ ልጅ ወለደች፤ ስሙንም፤ “ከእግዚአብሔር ለምኜዋለሁ” ስትል ሳሙኤል አለችው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

20 ስለዚህ ሐና ፀነሰች፤ የእርግዝናዋ ወራት በተፈጸመ ጊዜም ወንድ ልጅ ወለደች፤ “ከጌታ ለምኜዋለሁ” ስትል ስሙን “ሳሙኤል” ብላ ጠራችው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

20 ወዲያውኑ ፀነሰች፤ ወንድ ልጅም ወለደች፤ እርስዋም “ከእግዚአብሔር ለምኜ ያገኘሁት ነው” ስትል ስሙን “ሳሙኤል” አለችው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

20 የመፅነስዋም ወራት ካለፈ በኋላ ሐና ወንድ ልጅ ወለደች፥ እርስዋም፦ ከእግዚአብሔር ለምኜዋለሁ ስትል ስሙን ሳሙኤል ብላ ጠራችው።

参见章节 复制




1 ሳሙኤል 1:20
13 交叉引用  

የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መል​አ​ክም አላት፥ “እነሆ፥ አንቺ ፀን​ሰ​ሻል፤ ወንድ ልጅ​ንም ትወ​ል​ጃ​ለሽ፤ ስሙ​ንም ይስ​ማ​ኤል ብለሽ ትጠ​ሪ​ዋ​ለሽ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሥቃ​ይ​ሽን ሰም​ቶ​አ​ልና።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ራሔ​ልን አሰ​ባት፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ተለ​መ​ናት፤ ማኅ​ፀ​ን​ዋ​ንም ከፈ​ተ​ላት፤ ፀነ​ሰ​ችም፤


አዳ​ምም ዳግ​መኛ ሚስ​ቱን ዐወ​ቃት፤ ፀነ​ሰ​ችም፤ ወንድ ልጅ​ንም ወለ​ደች። ስሙ​ንም ቃየል በገ​ደ​ለው በአ​ቤል ፈንታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሌላ ዘር ተክ​ቶ​ል​ኛል ስትል ሴት አለ​ችው።


ስሙ​ንም ከሥ​ራዬ፥ ከእጄ ድካ​ምና እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከረ​ገ​ማት ምድር ይህ ያሳ​ር​ፈኝ ዘንድ አለው ሲል “ኖኅ” ብሎ ጠራው።


ያግ​ቤ​ጽም፥ “እባ​ክህ፥ መባ​ረ​ክን ባር​ከኝ፥ ሀገ​ሬ​ንም አስ​ፋው፤ እጅ​ህም ከእኔ ጋር ትሁን፤ እን​ዳ​ያ​ሳ​ዝ​ነ​ኝም ምል​ክት አድ​ር​ግ​ልኝ” ብሎ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን አም​ላክ ጠራ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የለ​መ​ነ​ውን ሰጠው።


ዐይ​ኖቼን ወደ ተራ​ሮች አነ​ሣሁ፤ ረድ​ኤቴ ከወ​ዴት ይምጣ?


ሕፃ​ኑም በአ​ደገ ጊዜ ወደ ፈር​ዖን ልጅ ወሰ​ደ​ችው፤ ለእ​ር​ስ​ዋም ልጅ ሆነ​ላት። እኔ ከውኃ አው​ጥ​ቼ​ዋ​ለ​ሁና ስት​ልም ስሙን ሙሴ ብላ ጠራ​ችው ።


ያችም ሴት ፀነ​ሰች፤ ወንድ ልጅም ወለ​ደች፤ ሙሴም፥ “በሌላ ምድር መጻ​ተኛ ነኝ” ሲል ስሙን ጌር​ሳም ብሎ ጠራው። ዳግ​መ​ኛም ፀነ​ሰች፤ ወንድ ልጅም ወለ​ደች፤ ስሙ​ንም ኤል​ኤ​ዜር አለው፤ የአ​ባቴ ፈጣሪ ረዳቴ ነው ሲል።


ልጅም ትወልዳለች፤ እርሱ ሕዝቡን ከኀጢአታቸው ያድናቸዋልና ስሙን ኢየሱስ ትለዋለህ።”


እን​ግ​ዲህ ምን እላ​ለሁ? ስለ ጌዴ​ዎን፥ ስለ ባርቅ፥ ስለ ሶም​ሶን፥ ስለ ዮፍ​ታሔ፥ ስለ ዳዊት፥ ስለ ሳሙ​ኤ​ልና ስለ ሌሎች ነቢ​ያት እነ​ግ​ራ​ችሁ ዘንድ ጊዜዬ አጭር ነውና።


跟着我们:

广告


广告