1 ነገሥት 8:32 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)32 በሰማይ ስማ፤ አድርግም፤ በባሪያዎችህም በእስራኤል ላይ ዳኛ ሁን፤ በበደለኛውም ላይ ፍረድ፤ መንገዱንም በራሱ ላይ መልስበት፤ ጻድቁን አጽድቀው፤ እንደ ጽድቁም ክፈለው። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም32 ይህን በሰማይ ሆነህ ስማ፤ አድርግም፤ በባሪያዎችህ መካከል ፍረድ፤ ለበደለኛው ስለ አድራጎቱ የእጁን ክፈል፤ ከበደል ነጻ ለሆነውም ንጽሕናውን ይፋ በማድረግ ይህንኑ አረጋግጥለት። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)32 በሰማይ ሆነህ ስማ፥ አድርግም፥ ለአገልጋዮችህም ፍርድን ስጥ፤ በበደለኛውም ላይ ፍረድ፤ ስለአካሄዱም ቅጣው፤ ንጹሑንም ነጻ አውጣው፥ እንደ ጽድቁም ክፈለው። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም32 በሰማይ ሆነህ ስማ፤ ለአገልጋዮችህም ፍርድን ስጥ፤ ይኸውም በደል የሠራው ሰው በጥፋቱ መጠን እንዲቀጣ፥ ንጹሑም ነጻ እንዲወጣ አድርግ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)32 በሰማይ ስማ፤ አድርግም፤ በባሪያዎችህም ላይ ዳኛ ሁን፤ በበደለኛውም ላይ ፍረድ፤ መንገዱንም በራሱ ላይ መልስበት፤ ንጹሑን አጽደቀው፤ እንደ ጽድቁም ክፈለው። 参见章节 |