Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ነገሥት 8:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

21 ከግ​ብ​ፅም ምድር ባወ​ጣ​ቸው ጊዜ ከአ​ባ​ቶ​ቻ​ችን ጋር ያደ​ረ​ገው የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ኪዳን ላለ​ባት ታቦት ስፍ​ራን በዚያ አደ​ር​ግ​ሁ​ላት።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 ከግብጽ ባወጣቸው ጊዜ ከአባቶቻችን ጋራ የገባው የእግዚአብሔር ኪዳን በውስጡ ላለበት ታቦት መኖሪያ ስፍራ በዚያ አዘጋጅቻለሁ።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 ከግብጽ ምድር ባወጣቸው ጊዜ ከቀድሞ አባቶቻችን ጋር ጌታ ያደረገው ቃል ኪዳን ላለበት ታቦት ማኖሪያ አዘጋጅቼአለሁ።”

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 እግዚአብሔር ከግብጽ ምድር ባወጣቸው ጊዜ ከቀድሞ አባቶቻችን ጋር ቃል ኪዳን የገባበት የድንጋይ ጽላት ለሚገኝበትም ታቦት ማኖሪያ የሚሆን ቦታ በቤተ መቅደሱ ውስጥ አዘጋጅቼአለሁ።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

21 ከግብጽም ምድር ባወጣቸው ጊዜ ከአባቶቻችን ጋር ያደረገው የእግዚአብሔር ቃል ኪዳን ላለበት ታቦት ስፍራ በዚያ አደረግሁለት።”

参见章节 复制




1 ነገሥት 8:21
8 交叉引用  

በታ​ቦ​ቷም ውስጥ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ከግ​ብፅ ምድር በወጡ ጊዜ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከእ​ነ​ርሱ ጋር ቃል ኪዳን ባደ​ረገ ጊዜ ሙሴ በኮ​ሬብ ካስ​ቀ​መ​ጣ​ቸው የቃል ኪዳን ጽላት ከሚ​ባ​ሉት ከሁ​ለቱ የድ​ን​ጋይ ጽላት በቀር ምንም አል​ነ​በ​ረ​ባ​ትም።


አሁ​ንም አም​ላ​ካ​ች​ሁን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትፈ​ልጉ ዘንድ ልባ​ች​ሁ​ንና ነፍ​ሳ​ች​ሁን ስጡ፤ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ስም ወደ​ሚ​ሠ​ራው ቤት የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የቃል ኪዳ​ኑን ታቦ​ትና የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ንዋየ ቅድ​ሳት ታመጡ ዘንድ ተነ​ሥ​ታ​ችሁ የአ​ም​ላ​ክን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መቅ​ደስ ሥሩ።”


ሙሴም ደሙን ወስዶ በሕ​ዝቡ ላይ ረጨው፤ በዚህ ቃል ሁሉ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከእ​ና​ንተ ጋር ያደ​ረ​ገው የቃል ኪዳኑ ደም እነሆ” አለ።


በዚ​ያም አርባ ቀንና አርባ ሌሊት በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ነበረ፤ እን​ጀ​ራም አል​በ​ላም፤ ውኃም አል​ጠ​ጣም። በጽ​ላ​ቱም ዐሥ​ሩን የቃል ኪዳን ቃሎች ጻፈ።


“ይህን የሕግ መጽ​ሐፍ ውሰዱ፤ በዚ​ያም በእ​ና​ንተ ላይ ምስ​ክር እን​ዲ​ሆን በአ​ም​ላ​ካ​ችሁ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ኪዳን ታቦት አጠ​ገብ አኑ​ሩት።


ከአ​ርባ ቀንና ከአ​ርባ ሌሊ​ትም በኋላ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሁለ​ቱን የድ​ን​ጋይ ጽላት፥ የቃል ኪዳ​ኑን ጽላት ሰጠኝ።


ሁለ​ቱን የድ​ን​ጋይ ጽላት፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከእ​ና​ንተ ጋር የተ​ማ​ማ​ለ​ባ​ቸ​ውን የቃል ኪዳን ጽላት እቀ​በል ዘንድ ወደ ተራራ በወ​ጣሁ ጊዜ፥ በተ​ራ​ራው አርባ ቀንና አርባ ሌሊት ተቀ​ምጬ ነበር፤ እን​ጀራ አል​በ​ላ​ሁም፤ ውኃም አል​ጠ​ጣ​ሁም።


跟着我们:

广告


广告