Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ነገሥት 7:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 ከፍ​ርድ ሰቀላ ወደ ውስጥ፥ በሌ​ላ​ውም አደ​ባ​ባይ ውስጥ የነ​በ​ረ​ውን የሚ​ኖ​ር​በ​ትን ቤት እን​ዲሁ ሠራ፤ እን​ደ​ዚ​ህም ቤት ያለ ቤትን ሰሎ​ሞን ላገ​ባት ለፈ​ር​ዖን ልጅ ሠራ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 ከአዳራሹ በስተጀርባ ባለው አደባባይ መኖሪያው እንዲሆን የተሠራው ቤተ መንግሥትም የዚሁ ተመሳሳይ ነበር። ሰሎሞን ላገባት ለፈርዖን ልጅ ይህንኑ ቤተ መንግሥት የመሰለ አዳራሽ ሠራ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 ከችሎቱም አዳራሽ በስተ ኋላ በሚገኘው ሌላ አደባባይ ሰሎሞን የሚኖርበትን ሕንጻ እንደ ሌሎቹ ሕንጻዎች አድርጎ አሠራ፤ የግብጽ ንጉሥ ልጅ ለነበረችው ሚስቱም ተመሳሳይ መኖሪያ ቤት አሠራላት።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 ከችሎቱም አዳራሽ በስተ ኋላ በሚገኘው ሌላ አደባባይ ሰሎሞን የሚኖርበትን ሕንጻ እንደ ሌሎቹ ሕንጻዎች አድርጎ አሠራ፤ የግብጽ ንጉሥ ልጅ ለነበረችው ሚስቱም ተመሳሳይ መኖሪያ ቤት አሠራላት።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 ከፍርድ ሰቀላ ወደ ውስጥ፥ በሌላውም አደባባይ ውስጥ የነበረውን መኖሪያ ቤት እንዲሁ ሠራ። እንደዚሁም ያለ ቤት ሰሎሞን ላገባት ለፈርዖን ልጅ ቤት ሠራ።

参见章节 复制




1 ነገሥት 7:8
6 交叉引用  

ሰሎ​ሞ​ንም ለግ​ብፅ ንጉሥ ለፈ​ር​ዖን አማች ሆነ፤ የፈ​ር​ዖ​ን​ንም ልጅ አገባ፤ ቤቱ​ንና የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ቤት፥ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ዙሪያ ያለ​ውን ቅጥር ሠርቶ እስ​ኪ​ፈ​ጽም ድረስ ወደ ዳዊት ከተማ አም​ጥቶ አስ​ገ​ባት።


ይህም ሁሉ ከመ​ሠ​ረቱ ጀምሮ እስከ ጕል​ላቱ ድረስ በከ​በ​ረና በተ​ጠ​ረበ በው​ስ​ጥና በውጭ በልክ በተ​ከ​ረ​ከመ ድን​ጋይ ተሠ​ርቶ ነበር፤ በው​ጭ​ውም እስከ ታላቁ አደ​ባ​ባይ ድረስ እን​ዲሁ ነበረ።


የግ​ብ​ፅም ንጉሥ ፈር​ዖን ወጥቶ ጋዜ​ርን ያዘ፤ በእ​ሳ​ትም አቃ​ጠ​ላት፤ በሜ​ር​ጎብ ይኖሩ የነ​በ​ሩ​ትን ከነ​ዓ​ና​ው​ያ​ን​ንም ገደ​ላ​ቸው፤ ለል​ጁም ለሰ​ሎ​ሞን ሚስት እነ​ዚ​ያን አገ​ሮች ትሎት አድ​ርጎ ሰጥ​ቶ​አት ነበር።


የፈ​ር​ዖ​ን​ንም ልጅ ከዳ​ዊት ከተማ ሰሎ​ሞን ወደ ሠራ​ላት ወደ ቤቷ አመ​ጣት፤ በዚያ ጊዜም ሚሎ​ንን ሠራት።


ኢሳ​ይ​ያ​ስም ወደ መካ​ከ​ለ​ኛው አደ​ባ​ባይ ሲደ​ርስ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተና​ገ​ረው፤ እን​ዲ​ህም አለው፦


ሰሎ​ሞ​ንም፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታቦት የገ​ባ​ች​በት ስፍራ ቅዱስ ነውና ሚስቴ በእ​ስ​ራ​ኤል ንጉሥ በዳ​ዊት ቤት አት​ቀ​መ​ጥም” ሲል የፈ​ር​ዖ​ንን ልጅ ከዳ​ዊት ከተማ ወደ ሠራ​ላት ቤት አወ​ጣት።


跟着我们:

广告


广告