Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ነገሥት 7:50 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

50 ከጥሩ ወር​ቅም የተ​ሠ​ሩ​ትን ጽዋ​ዎ​ችና ጕጠ​ቶች፥ ድስ​ቶ​ቹ​ንና ጭል​ፋ​ዎ​ቹ​ንም፥ ማን​ደ​ጃ​ዎ​ቹ​ንም፥ ጽን​ሐ​ሖ​ችን፥ ለው​ስ​ጠ​ኛ​ውም ቤት ለቅ​ድ​ስተ ቅዱ​ሳን ደጆች፥ ለቤተ መቅ​ደ​ሱም ደጆች የሚ​ሆ​ኑ​ትን የወ​ርቅ ማጠ​ፊ​ያ​ዎች አሠራ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

50 ከንጹሕ ወርቅ የተሠሩ ጽዋዎችን፣ የመብራት መኰስተሪያዎችን፣ ለመርጫ የሚሆኑ ጐድጓዳ ሳሕኖችን፣ ጭልፋዎችን፣ የዕጣን ማቅረቢያ ዕቃዎችን፣ ለውስጠኛው ክፍል ለቅድስተ ቅዱሳኑ በሮችና እንዲሁም ለቤተ መቅደሱ በሮች የሚሆኑ የወርቅ ማጠፊያዎችን።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

50 ጽዋዎች፥ የዐመድ ማጠራቀሚያዎች፥ ጐድጓዳ ሳሕኖች፥ የዕጣን ማቅረቢያ ዕቃዎች፥ ማንደጃዎች፥ ለቅድስተ ቅዱሳን በሮችና ለቤተ መቅደሱ ውጫዊ በሮች የሚያገለግሉ ማጠፊያዎች ነበሩ። እነዚህ ሁሉ ዕቃዎች ከወርቅ የተሠሩ ናቸው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

50 ጽዋዎች፥ የዐመድ ማጠራቀሚያዎች፥ ጐድጓዳ ሳሕኖች፥ የዕጣን ማቅረቢያ ዕቃዎች፥ ማንደጃዎች፥ ለቅድስተ ቅዱሳን በሮችና ለቤተ መቅደሱ ውጫዊ በሮች የሚያገለግሉ ማጠፊያዎች ነበሩ። እነዚህ ሁሉ ዕቃዎች ከወርቅ የተሠሩ ናቸው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

50 ከጥሩ ወርቅም የተሠሩትን ጽዋዎችና ጕጠቶች፥ ድስቶቹንና ጭልፋዎቹንም፥ ማንደጃዎቹንም፥ ለውስጠኛውም ቤት ለቅድስተ ቅዱሳን ደጆች ለቤተ መቅደሱም ደጆች የሚሆኑትን የወርቅ ማጠፊያዎች አሠራ።

参见章节 复制




1 ነገሥት 7:50
11 交叉引用  

ነገር ግን ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ከሚ​መ​ጣው ገን​ዘብ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት የሚ​ሆኑ የብር መዝ​ጊ​ያ​ዎች፥ ጽዋ​ዎ​ችና ጕጠ​ቶች፥ ድስ​ቶ​ችም፥ መለ​ከ​ቶ​ችም፥ የወ​ር​ቅና የብር ዕቃ​ዎ​ችም አል​ተ​ሠ​ሩም ነበር።


የአ​በ​ዛ​ዎች አለ​ቃም ጥና​ዎ​ቹን ከወ​ር​ቅና ከብር የተ​ሠሩ መኰ​ስ​ተ​ሪ​ያ​ዎ​ች​ንም ወሰደ።


ለማ​ፍ​ሰ​ሻም ይሆኑ ዘንድ ወጭ​ቶ​ች​ዋን፥ ጭል​ፋ​ዎ​ች​ዋ​ንም፥ መቅ​ጃ​ዎ​ች​ዋ​ንም፥ ጽዋ​ዎ​ች​ዋ​ንም አድ​ርግ፤ እነ​ር​ሱ​ንም ከጥሩ ወርቅ አድ​ር​ጋ​ቸው።


መኰ​ስ​ተ​ሪ​ያ​ዎ​ች​ዋን፥ የኵ​ስ​ታሪ ማድ​ረ​ጊ​ያ​ዎ​ች​ዋ​ንም ከጥሩ ወርቅ አድ​ርግ።


ለመ​ሠ​ዊ​ያው ክዳን ሥራ​ለት፤ መሸ​ፈ​ኛ​ውን፥ ጽዋ​ዎ​ቹን፥ የሥጋ ሜን​ጦ​ዎ​ቹን፥ የእ​ሳት መጫ​ሪ​ያ​ዎ​ቹ​ንም አድ​ርግ። ዕቃ​ው​ንም ሁሉ ከናስ አድ​ርግ።


የአ​ዛ​ዦ​ችም አለቃ ጽዋ​ዎ​ቹን፥ ማን​ደ​ጃ​ዎ​ቹን፥ ድስ​ቶ​ቹ​ንና ምን​ቸ​ቶ​ቹን፥ መቅ​ረ​ዞ​ቹ​ንና ጭል​ፋ​ዎ​ቹን፥ መን​ቀ​ሎ​ች​ንም፥ የወ​ር​ቁን ዕቃ በወ​ርቅ፥ የብ​ሩ​ንም ዕቃ በብር አድ​ርጎ፥ ወሰደ።


በመ​ቅ​ደ​ሱም ፊት ርዝ​መ​ቱን አርባ ክንድ፥ ወር​ዱ​ንም ሃያ ክንድ አድ​ርጎ ለካና፥ “ይህ ቅድ​ስተ ቅዱ​ሳን ነው” አለኝ።


በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት ከአ​ለው መሠ​ዊያ ላይ የእ​ሳት ፍም አም​ጥቶ ጥና​ውን ይሞ​ላል፤ ከተ​ወ​ቀ​ጠ​ውም ልቅ​ምና ደቃቅ ዕጣን እጁን ሙሉ ይወ​ስ​ዳል፤ ወደ መጋ​ረ​ጃ​ውም ውስጥ ያመ​ጣ​ዋል።


በዚያ ቀን በፈረሶች ሻኵራ ላይ፦ ለእግዚአብሔር የተቀደሰ ተብሎ ይጻፋል፣ በእግዚአብሔርም ቤት ያሉ ምንቸቶች በመሠዊያው ፊት እንዳሉ ዳካዎች ይሆናሉ።


ዕጣ​ንም የተ​ሞሉ ዐሥራ ሁለት የወ​ርቅ ጭል​ፋ​ዎች፥ እያ​ን​ዳ​ንዱ በመ​ቅ​ደሱ ሰቅል ሚዛን ዐሥር ዐሥር ሰቅል ነበረ፤ የጭ​ል​ፋ​ዎቹ ወርቅ ሁሉ መቶ ሃያ ሰቅል ነበረ።


跟着我们:

广告


广告