Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ነገሥት 7:40 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

40 ኪራ​ምም ምን​ቸ​ቶ​ች​ንና መጫ​ሪ​ያ​ዎ​ችን፥ ድስ​ቶ​ች​ንም ሠራ፤ ኪራ​ምም ለን​ጉሡ ለሰ​ሎ​ሞን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት የሠ​ራ​ውን ሥራ ሁሉ ጨረሰ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

40 ኪራምም ምንቸቶችን፣ መጫሪያዎችንና ጐድጓዳ ሳሕኖችን ሠራ። ኪራምም ለእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ አገልግሎት ለንጉሥ ሰሎሞን የሠራውን ሥራ ሁሉ ፈጸመ እነዚህም፦

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

40 ሑራም ድስቶችን፥ መጫሪያዎችንና ጐድጓዳ ሳሕኖችን ሠራ፤ በዚህ ዓይነትም ለንጉሥ ሰሎሞን ሊሠራለት የጀመረውን የጌታን ቤት ሥራ ፈጸመ፤ ከሠራቸውም ነገሮች ዋና ዋናዎቹ የሚከተሉት ናቸው፦

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

40 ሑራም ድስቶችን፥ መጫሪያዎችንና ጐድጓዳ ሳሕኖችን ሠራ፤ በዚህ ዐይነትም ለንጉሥ ሰሎሞን ሊሠራለት የጀመረውን የእግዚአብሔርን መቅደስ ሥራ ፈጸመ፤ ከሠራቸውም ነገሮች ዋና ዋናዎቹ የሚከተሉት ናቸው፦

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

40 ኪራምም ምንቸቶችንና መጫሪያዎችን ድስቶችንም ሠራ፤ ኪራምም ለንጉሡ ለሰሎሞን በእግዚአብሔር ቤት የሠራውን ሥራ ሁሉ ጨረሰ።

参见章节 复制




1 ነገሥት 7:40
12 交叉引用  

መቀ​መ​ጫ​ዎ​ች​ንም እን​ዲሁ ሠራ፤ እርስ በር​ሳ​ቸ​ውም አያ​ይዞ ሰን​በር ባለው ክፈፍ ሠራ​ቸው።


አም​ስ​ቱ​ንም መቀ​መ​ጫ​ዎች በቤቱ ቀኝ፥ አም​ስ​ቱ​ንም በቤቱ ግራ አኖ​ራ​ቸው፤ ኩሬ​ው​ንም በቤቱ ቀኝ በአ​ዜብ ፊት ለፊት በስ​ተ​ም​ሥ​ራቅ አኖ​ረው።


ሁለ​ቱ​ንም አዕ​ማድ፥ በሁ​ለ​ቱም አዕ​ማድ ራስ ላይ የነ​በ​ሩ​ትን ኩብ የሚ​መ​ስ​ሉ​ትን ጕል​ላ​ቶች፥ በሁ​ለ​ቱም አዕ​ማድ ላይ የነ​በ​ሩ​ትን ሁለ​ቱን ጕል​ላ​ቶች የሚ​ሸ​ፍ​ኑ​ትን ሁለ​ቱን መር​በ​ቦች፥


ከሚ​ጢ​ብ​ሐ​ትና ከተ​መ​ረ​ጡት ከአ​ድ​ር​አ​ዛር ከተ​ሞች ዳዊት እጅግ ብዙ ናስ ወሰደ፤ ከዚ​ህም ሰሎ​ሞን የና​ሱን ኩሬና ዓም​ዶች የና​ሱ​ንም ዕቃ ሠራ።


ደግ​ሞም ዐሥር የመ​ታ​ጠ​ቢያ ሰኖ​ችን ሠራ፤ ለሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውም መሥ​ዋ​ዕት የሚ​ቀ​ር​በው ነገር ሁሉ ይታ​ጠ​ብ​ባ​ቸው ዘንድ አም​ስ​ቱን በቀኝ፥ አም​ስ​ቱ​ንም በግራ አኖ​ራ​ቸው፤ ባሕሩ ግን ካህ​ናት ይታ​ጠ​ቡ​በት ነበር።


ዐሥ​ሩ​ንም የወ​ርቅ ገበ​ታ​ዎች ሠርቶ አም​ስ​ቱን በቀኝ፥ አም​ስ​ቱ​ንም በግራ በመ​ቅ​ደሱ ውስጥ አኖ​ራ​ቸው። አንድ መቶም የወ​ርቅ ጽዋ​ዎ​ችን ሠራ።


ሙሴም የደ​ሙን እኵ​ሌታ ወስዶ በቆሬ ውስጥ አደ​ረ​ገው፤ የደ​ሙ​ንም እኵ​ሌታ በመ​ሠ​ዊ​ያው ረጨው።


ለመ​ሠ​ዊ​ያው ክዳን ሥራ​ለት፤ መሸ​ፈ​ኛ​ውን፥ ጽዋ​ዎ​ቹን፥ የሥጋ ሜን​ጦ​ዎ​ቹን፥ የእ​ሳት መጫ​ሪ​ያ​ዎ​ቹ​ንም አድ​ርግ። ዕቃ​ው​ንም ሁሉ ከናስ አድ​ርግ።


跟着我们:

广告


广告