Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ነገሥት 7:38 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

38 ዐሥ​ሩ​ንም የናስ መታ​ጠ​ቢያ ሰን ሠራ፤ አንዱ መታ​ጠ​ቢያ ሰን አርባ የባ​ዶስ መስ​ፈ​ሪያ ያነሣ ነበር፤ እያ​ን​ዳ​ን​ዱም መታ​ጠ​ቢያ ሰን አራት ክንድ ነበረ፤ በዐ​ሥ​ሩም መቀ​መ​ጫ​ዎች ላይ በእ​ያ​ን​ዳ​ንዱ አንድ አንድ መታ​ጠ​ቢያ ሰን ይቀ​መጥ ነበር።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

38 ከዚያም ለእያንዳንዱ የዕቃ ማስቀመጫ የሚሆን፣ እያንዳንዱ አርባ የባዶስ መስፈሪያ የሚይዝ ዐሥር የናስ መታጠቢያ ገንዳ ሠራ፤ ስፋቱም አራት ክንድ ነበር።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

38 ሑራም ለእያንዳንዱ የዕቃ ማስቀመጫ ዐሥር መታጠቢያ ገንዳዎችን ሠራ፤ እያንዳንዱም ገንዳ ዙሪያ አጋማሽ ስፋት አንድ ሜትር ከሰማንያ ሳንቲ ሜትር ያኽል ሲሆን፥ ስምንት መቶ ሊትር ያኽል ውሃ ይይዝ ነበር።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

38 ሑራም ለእያንዳንዱ የዕቃ ማስቀመጫ ዐሥር መታጠቢያ ገንዳዎች ሠራ፤ እያንዳንዱ ገንዳ ዙሪያ አጋማሽ ስፋት አንድ ሜትር ከሰማንያ ሳንቲ ሜትር ያኽል ሲሆን፥ ስምንት መቶ ሊትር ያኽል ውሃ ይይዝ ነበር፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

38 ዐሥሩንም የናስ መታጠቢያ ሰን ሠራ፤ አንዱ መታጠቢያ ሰን አርባ የባዶስ መስፈሪያ ያነሣ ነበር፤ እያንዳንዱም መታጠቢያ ሰን አራት ክንድ ነበረ፤ በዐሥሩም መቀመጫዎች ላይ በእያንዳንዱ አንድ አንድ መታጠቢያ ሰን ይቀመጥ ነበር።

参见章节 复制




1 ነገሥት 7:38
12 交叉引用  

ዐሥ​ርም የናስ መቀ​መ​ጫ​ዎ​ችን ሠራ፤ የአ​ን​ዱም መቀ​መጫ ርዝ​መት አራት ክንድ፥ ወር​ዱም አራት ክንድ፥ ቁመ​ቱም ሦስት ክንድ ነበረ።


አም​ስ​ቱ​ንም መቀ​መ​ጫ​ዎች በቤቱ ቀኝ፥ አም​ስ​ቱ​ንም በቤቱ ግራ አኖ​ራ​ቸው፤ ኩሬ​ው​ንም በቤቱ ቀኝ በአ​ዜብ ፊት ለፊት በስ​ተ​ም​ሥ​ራቅ አኖ​ረው።


ለሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት የሚ​ሆ​ነ​ውን መሠ​ዊ​ያና ዕቃ​ው​ንም ሁሉ፥ የመ​ታ​ጠ​ቢ​ያ​ውን ሰንና መቀ​መ​ጫ​ው​ንም ትቀ​ባ​በ​ታ​ለህ።


የመ​ታ​ጠ​ቢ​ያ​ውን ሰንና መቀ​መ​ጫ​ው​ንም በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ደጃፍ ከሚ​ያ​ገ​ለ​ግሉ ከሴ​ቶች መስ​ተ​ዋት ከናስ አደ​ረገ።


በዚያ ቀን ለዳዊት ቤትና በኢየሩሳሌም ለሚኖሩ ከኃጢአትና ከርኵሰት የሚያነጻ ምንጭ ይከፈታል።


እን​ግ​ዲህ ከክፉ ሕሊና ለመ​ን​ጻት ልባ​ች​ንን ተረ​ጭ​ተን፥ ሰው​ነ​ታ​ች​ን​ንም በጥሩ ውኃ ታጥ​በን በተ​ረ​ዳ​ን​በት እም​ነት በቅን ልብ እን​ቅ​ረብ።


እነ​ዚ​ህም እስከ መታ​ደስ ዘመን ድረስ የተ​ደ​ረጉ፥ ስለ ምግ​ብና ስለ መጠ​ጥም፥ ስለ ልዩ ልዩ ጥም​ቀ​ትም የሚ​ሆኑ የሥጋ ሥር​ዐ​ቶች ብቻ ናቸው።


ነገር ግን እርሱ በብርሃን እንዳለ በብርሃን ብንመላለስ ለእያንዳንዳችን ኅብረት አለን፥ የልጁም የኢየሱስ ክርስቶስ ደም ከኃጢአት ሁሉ ያነጻናል።


እኔም “ጌታ ሆይ! አንተ ታውቃለህ፤” አልሁት። አለኝም “እነዚህ ከታላቁ መከራ የመጡ ናቸው፤ ልብሳቸውንም አጥበው በበጉ ደም አነጹ።


跟着我们:

广告


广告