Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ነገሥት 6:38 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

38 በዐ​ሥራ አን​ደ​ኛ​ውም ዓመት ቡል በሚ​ባል በስ​ም​ን​ተ​ኛው ወር ቤቱ እንደ ክፍ​ሎ​ቹና እንደ ሥር​ዐቱ ሁሉ ተጨ​ረሰ። በሰ​ባት ዓመ​ትም ሠራው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

38 በዐሥራ አንደኛው ዓመት ቡል በተባለውም በስምንተኛው ወር ቤተ መቅደሱ በዝርዝር ጥናቱ መሠረት እንደ ታቀደው ተፈጸመ፤ ሠርቶ የጨረሰውም በሰባት ዓመት ጊዜ ውስጥ ነበር።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

38 ሰሎሞን በነገሠ በዐሥራ አንደኛ ዓመቱ፥ ቡል ተብሎ በሚጠራው በስምንተኛው ወር ላይ የቤተ መቅደሱ ሥራ ልክ በታቀደው መሠረት ሙሉ በሙሉ ተጠናቀቀ፤ ሰሎሞን ቤተ መቅደሱን ለመሥራት የፈጀበት ጊዜ ሰባት ዓመት ነበር።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

38 ሰሎሞን በነገሠ በዐሥራ አንደኛ ዓመቱ፥ ቡል ተብሎ በሚጠራው በስምንተኛው ወር ላይ የቤተ መቅደሱ ሥራ ልክ በታቀደው መሠረት ሙሉ በሙሉ ተጠናቀቀ፤ ሰሎሞን ቤተ መቅደሱን ለመሥራት የፈጀበት ጊዜ ሰባት ዓመት ነበር።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

38 በዐሥራ አንደኛውም ዓመት ቡል በሚባል በስምንተኛው ወር ቤቱ እንደ ክፍሎቹና እንደ ሥርዐቱ ሁሉ ተጨረሰ። በሰባትም ዓመት ውስጥ ሠራው።

参见章节 复制




1 ነገሥት 6:38
19 交叉引用  

የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ከግ​ብፅ ምድር ከወጡ አራት መቶ ሰማ​ንያ አራት ዓመት በሆነ ጊዜ፥ ሰሎ​ሞን በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ በነ​ገሠ በአ​ራ​ተ​ኛው ዓመት፥ ዚፍ በሚ​ባ​ለው በሁ​ለ​ተ​ኛው ወር የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት መሥ​ራት ጀመረ።


ሰሎ​ሞ​ንም ቤቱን ሠራው፤ ፈጸ​መ​ውም።


በአ​ራ​ተ​ኛው ዓመት ከሚ​ያ​ዝያ በሁ​ለ​ተ​ኛው ወር የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት መሠ​ረተ።


ቤቱ​ንም ሠርቶ ፈጸ​መው፤ የቤ​ቱ​ንም ጠፈር በዝ​ግባ ሳን​ቃ​ዎች አደ​ረገ።


ሰሎ​ሞ​ንም የራ​ሱን ቤት በዐ​ሥራ ሦስት ዓመት ሠራ፤ የቤ​ቱ​ንም ሥራ ሁሉ ጨረሰ።


ሰሎ​ሞ​ንም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤትና የን​ጉ​ሡን ቤት ሁለ​ቱን ቤቶች በሠ​ራ​በት በሃያ ዓመት ውስጥ፥


ዕው​ቀት እንደ ተሰ​ጠው የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት ይሠራ ዘንድ ዳዊት በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሕግ የተ​ጻ​ፈ​ውን ለልጁ ለሰ​ሎ​ሞን ሰጠው።


ዳዊ​ትም ልጁን ሰሎ​ሞ​ንን፥ “ጠን​ክር፤ ሰው ሁን፤ አይ​ዞህ፥ አድ​ር​ገ​ውም፤ አም​ላኬ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከአ​ንተ ጋር ነውና አት​ፍራ፤ አት​ደ​ን​ግ​ጥም፤ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤት አገ​ል​ግ​ሎት የሚ​ሆ​ነ​ውን ሥራ ሁሉ እስ​ክ​ት​ፈ​ጽም ድረስ እርሱ አይ​ተ​ው​ህም፤ አይ​ጥ​ል​ህ​ምም። እነሆ፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ሕንጻ ምሳሌ፥ የአ​ደ​ባ​ባዩ፥ የቤተ መዛ​ግ​ብቱ፥ የሰ​ገ​ነቱ፥ የው​ስጡ ቤተ መዛ​ግ​ብት፥ የስ​ር​የት ቤቱና፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ምሳሌ።


እን​ዲ​ህም ሆነ፤ ሰሎ​ሞን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤትና የራ​ሱን ቤት የሠ​ራ​በት ሃያ ዓመት በተ​ፈ​ጸመ ጊዜ፥


እነሆ፥ መሠ​ረቱ ከተ​ጣለ ጀምሮ ሰሎ​ሞን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት እስከ ፈጸመ ድረስ ሥራው ሁሉ የተ​ዘ​ጋጀ ነበረ። የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤት ተፈ​ጸመ።


እን​ደ​ዚ​ህም ብለው መለ​ሱ​ልን፦ እኛ የሰ​ማ​ይና የም​ድር አም​ላክ ባሪ​ያ​ዎች ነን፥ ከብ​ዙም ዘመን ጀምሮ ተሠ​ርቶ የነ​በ​ረ​ውን፥ ታላ​ቁም የእ​ስ​ራ​ኤል ንጉሥ ሠርቶ ፈጽ​ሞ​ላ​ቸው የነ​በ​ረ​ውን ቤት እን​ሠ​ራ​ለን።


እን​ዲ​ሁም የም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ሥራ ሁሉ ተፈ​ጸመ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዳ​ዘ​ዘው ሁሉ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች አደ​ረጉ፤ እን​ዲሁ አደ​ረጉ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሙሴን እን​ዳ​ዘዘ ሁሉ እን​ዲሁ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ሥራ​ውን ሁሉ ሠሩ።


ሙሴም ሥራ​ውን ሁሉ አየ፤ እነ​ሆም፥ አድ​ር​ገ​ውት ነበር፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዳ​ዘ​ዘው እን​ዲሁ አድ​ር​ገ​ውት ነበር፤ ሙሴም ባረ​ካ​ቸው።


የዘሩባቤል እጆች ይህን ቤት መሠረቱ፥ የእርሱም እጆች ይፈጽሙታል፣ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔርም ወደ እናንተ እንደ ላከኝ ታውቃላችሁ።


አይ​ሁ​ድም፥ “ይህ ቤተ መቅ​ደስ በአ​ርባ ስድ​ስት ዓመት ተሠራ፤ አን​ተስ በሦ​ስት ቀኖች ውስጥ ታነ​ሣ​ዋ​ለ​ህን?” አሉት።


跟着我们:

广告


广告