Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ነገሥት 4:31 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

31 ከሰ​ዎ​ችም ሁሉ ይልቅ ብልህ ነበረ፤ ከኢ​ይ​ዝ​ራ​ኤ​ላ​ዊው ከኤ​ታ​ንና ከማ​ሖል ልጆች ከአ​ው​ና​ንና ከከ​ል​ቀድ፥ ከደ​ራ​ልም ይልቅ ጥበ​በኛ ነበረ። በዙ​ሪ​ያ​ውም ባሉ አሕ​ዛብ ሁሉ ዝናው ወጣ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

31 እርሱም ከማንም ሰው ይልቅ ጥበበኛ ነበር፣ ከኢይዝራኤላዊው ከኤታን፣ ከማሖል ልጆች ከሄማንና ከከልቀድ ደግሞም ከደራል ይልቅ ጥበበኛ ነበር፤ ዝናውም በዙሪያው ባሉት አሕዛብ ሁሉ ተሰማ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

31 እርሱ ከሰዎች ሁሉ የሚበልጥ ታላቅ ጥበበኛ ነበረ። ከኤዝራሐዊው ኤታን፥ የማሖል ልጆች ከሆኑት ከሄማን፥ ከካልኮልና ከዳርዓዕ የሚበልጥ ጥበበኛ ነበረ፤ ዝናውም ከፍ ብሎ በጐረቤት ሕዝቦች ሁሉ ዘንድ አስተጋባ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

31 እርሱ ከሰዎች ሁሉ የሚበልጥ ታላቅ ጥበበኛ ነበረ፤ ከኤዝራሐዊው ኤታን፥ የማሖል ልጆች ከሆኑት ከሄማን፥ ከካልኮልና ከዳርዓዕ የሚበልጥ ጥበበኛ ነበረ፤ ዝናውም ከፍ ብሎ በጐረቤት ሕዝቦች ሁሉ ዘንድ አስተጋባ፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

31 ከሰውም ሁሉ ይልቅ ከኢይዝራኤላዊው ከኤታንና ከማሖል ልጆች ከሄማንና ከከልቀድ ከደራልም ይልቅ ጥበበኛ ነበረ። በዙሪያውም ባሉ አሕዛብ ሁሉ ዝናው ወጣ።

参见章节 复制




1 ነገሥት 4:31
16 交叉引用  

የሳ​ባም ንግ​ሥት የሰ​ሎ​ሞ​ንን ስም፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ስም በሰ​ማች ጊዜ ሰሎ​ሞ​ንን በእ​ን​ቆ​ቅ​ልሽ ትፈ​ት​ነው ዘንድ መጣች።


ንጉ​ሡን ሰሎ​ሞ​ን​ንም አለ​ችው፥ “ስለ ነገ​ር​ህና ስለ ጥበ​ብህ በሀ​ገሬ ሳለሁ የሰ​ማ​ሁት ዝና እው​ነት ነው።


እነሆ፥ እኔ እንደ ቃልህ አድ​ር​ጌ​ል​ሃ​ለሁ፤ እነ​ሆም፥ ማንም የሚ​መ​ስ​ልህ ከአ​ንተ በፊት እን​ደ​ሌለ፥ ከአ​ን​ተም በኋላ እን​ዳ​ይ​ነሣ አድ​ርጌ ጥበ​በ​ኛና አስ​ተ​ዋይ ልቡና ሰጥ​ቼ​ሃ​ለሁ።


ኪራ​ምም የሰ​ሎ​ሞ​ንን ቃል ሰምቶ እጅግ ደስ አለ​ውና፥ “በዚህ ታላቅ ሕዝብ ላይ ጥበ​በኛ ልጅ ለዳ​ዊት የሰጠ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዛሬ ይመ​ስ​ገን” አለ።


ሌዋ​ው​ያ​ኑም የኢ​ዩ​ኤ​ልን ልጅ ኤማ​ንን፥ ከወ​ን​ድ​ሞ​ቹም የበ​ራ​ክ​ያን ልጅ አሳ​ፍን፥ ከወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ቸ​ውም ከሜ​ራሪ ልጆች የቂ​ሳ​ንን ልጅ ኢታ​ንን፥


መዘ​ም​ራ​ንም ኤማ​ንና አሳፍ ኤታ​ንም በናስ ጸና​ጽል ከፍ አድ​ር​ገው ያሰሙ ነበር።


የዛ​ራም ልጆች፤ ዘምሪ፥ ኤታን፥ ኤማን፥ ካል​ኮል፥ ዳራ፤ ሁሉም አም​ስት ነበሩ።


አገ​ል​ጋ​ዮ​ቹና ልጆቹ እነ​ዚህ ነበሩ፤ ከቀ​ዓት ልጆች ዘማ​ሪው ኤማን ነበረ፤ እር​ሱም የኢ​ዩ​ኤል ልጅ፥ የሳ​ሙ​ኤል ልጅ፤


የም​ድ​ርም ነገ​ሥ​ታት ሁሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በልቡ ያኖ​ረ​ውን ጥበ​ቡን ይሰሙ ዘንድ የሰ​ሎ​ሞ​ንን ፊት ሊያዩ ይመኙ ነበር።


አቤቱ፥ ምሕ​ረ​ት​ህን ለዘ​ለ​ዓ​ለም እዘ​ም​ራ​ለሁ። ጽድ​ቅ​ህ​ንም በአፌ ለልጅ ልጅ እና​ገ​ራ​ለሁ።


ንግሥተ ዓዜብ በፍርድ ቀን ከዚህ ትውልድ ጋር ተነሥታ ትፈርድበታለች፤ የሰሎሞንን ጥበብ ለመስማት ከምድር ዳር መጥታለችና፤ እነሆም ከሰሎሞን የሚበልጥ ከዚህ አለ።


ዝናውም ወደ ሶርያ ሁሉ ወጣ፤ በልዩ ልዩ ደዌና ሥቃይም ተይዘው የታመሙትን ሁሉ አጋንንትም ያደሩባቸውን በጨረቃም የሚነሣባቸውን ሽባዎችንም ወደ እርሱ አመጡ፤ ፈወሳቸውም።


የአ​ዜብ ንግ​ሥት በፍ​ርድ ቀን ከዚች ትው​ልድ ጋር ተነ​ሥታ ትፋ​ረ​ዳ​ቸ​ዋ​ለች፤ የሰ​ሎ​ሞ​ንን ጥበብ ልት​ሰማ ከም​ድር ዳርቻ መጥ​ታ​ለ​ችና፤ እነሆ፥ ከሰ​ሎ​ሞን የሚ​በ​ልጥ በዚህ አለ።


የተ​ሰ​ወረ የጥ​በ​ብና የም​ክር መዝ​ገብ ሁሉ በእ​ርሱ ዘንድ አለ።


跟着我们:

广告


广告