Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ነገሥት 3:26 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

26 ደኅ​ነ​ኛ​ውም ሕፃን የነ​በ​ራት ሴት አን​ጀ​ትዋ ስለ ልጅዋ ታው​ኳ​ልና፥ “ጌታዬ ሆይ! አይ​ደ​ለም፤ ደኅ​ነ​ኛ​ውን ለእ​ር​ስዋ ስጣት እንጂ መግ​ደ​ልስ አት​ግ​ደ​ሉት” ብላ ለን​ጉሡ ተና​ገ​ረች። ያች​ኛ​ዪቱ ግን፥ “አካ​ፍ​ሉን እንጂ ለእ​ኔም ለእ​ር​ስ​ዋም አይ​ሁን” አለች።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

26 በሕይወት ያለው ልጅ እናት ለልጇ እጅግ ስለ ራራች ንጉሡን፣ “ጌታዬ ሆይ፤ እባክህ በሕይወት ያለውን ሕፃን ለርሷ ስጣት፤ አትግደለው” አለች። ሌላዪቱ ግን፣ “ለእኔም ሆነ ለአንቺ አይሰጥም፤ ሁለት ላይ ይከፈል!” አለች።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

26 እውነተኛይቱ እናት ግን ለልጇ በመራራት አዝና፥ “ንጉሥ ሆይ! እባክህ ልጁን አትግደለው! ለእርሷ ይሰጣት!” አለች። ሌላይቱ ሴት ግን “ለእኔም ለእርሷም አይሁን! ለሁለት ይቆረጥ!” አለች።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

26 እውነተኛይቱ እናት ግን ለልጅዋ በመራራት አዝና፥ “ንጉሥ ሆይ! እባክህ ልጁን አትግደለው! ለእርስዋ ይሰጣት!” አለች። ሌላይቱ ሴት ግን “ለእኔም ለእርስዋም አይሁን! ለሁለት ይቈረጥ!” አለች።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

26 ደኅነኛውም የነበራት ሴት አንጀትዋ ስለ ልጅዋ ናፍቆአልና “ጌታዬ ሆይ! ደኀነኛውን ለእርስዋ ስጣት እንጂ አትግደል፤” ብላ ለንጉሡ ተናገረች። ያችኛይቱ ግን “ይከፈል እንጂ ለእኔም ለአንቺም አይሁን፤” አለች።

参见章节 复制




1 ነገሥት 3:26
12 交叉引用  

ዮሴ​ፍም ታወከ፤ አን​ጀቱ ወን​ድ​ሙን ናፍ​ቆ​ታ​ልና፤ ሊያ​ለ​ቅ​ስም ወደደ፤ ወደ እል​ፍ​ኙም ገብቶ በዚያ አለ​ቀሰ።


ንጉ​ሡም፥ “ደኅ​ነ​ኛ​ውን ሕፃን ለሁ​ለት ቈር​ጣ​ችሁ ለአ​ን​ዲቱ አን​ዱን ክፍል፥ ለሁ​ለ​ተ​ኛ​ዪ​ቱም ሁለ​ተ​ኛ​ውን ክፍል ስጡ” አለ።


ንጉ​ሡም መልሶ እን​ዲህ አለ፥ “ለእ​ር​ስዋ ስጧት እንጂ መግ​ደ​ልስ አት​ግ​ደ​ሉት ላለ​ችው ሴት ስጡ​አት፤ እናቱ እር​ስዋ ናትና።”


አዲስ ምስ​ጋ​ናን በአፌ ጨመረ፥ ይህም የአ​ም​ላ​ካ​ችን ምስ​ጋ​ናው ነው፤ ብዙ​ዎች አይ​ተው ይፍሩ፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ይታ​መኑ።


“በውኑ ሴት፥ ልጅ​ዋን ትረ​ሳ​ለ​ችን? ከማ​ኅ​ፀ​ንዋ ለተ​ወ​ለ​ደ​ውስ አት​ራ​ራ​ምን? ሴት ይህን ብት​ረሳ፥ እኔ አን​ቺን አል​ረ​ሳ​ሽም።


በእ​ው​ነት ኤፍ​ሬም ለእኔ የተ​ወ​ደደ ልጅ ነው፤ ደስ የሚ​ያ​ሰ​ኝም ሕፃን ነው፤ በእ​ርሱ ላይ በተ​ና​ገ​ርሁ ቍጥር አስ​በ​ዋ​ለሁ፤ ስለ​ዚህ አን​ጀቴ ታወ​ከ​ች​ለት፤ ርኅ​ራ​ኄም እራ​ራ​ለ​ታ​ለሁ፥” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


እኔም “አም​ል​ኮ​ቴን ትተ​ሃል አልሁ፤ ኤፍ​ሬም ሆይ! እን​ዴት አደ​ር​ግ​ሃ​ለሁ? እስ​ራ​ኤል ሆይ! እን​ዴ​ትስ እደ​ግ​ፍ​ሃ​ለሁ? እን​ዴ​ትስ አደ​ር​ግ​ሃ​ለሁ? እንደ አዳማ ነውን? ወይስ እንደ ሲባዮ? ልቤ በው​ስጤ ተና​ው​ጣ​ለች፤ ምሕ​ረ​ቴም ተገ​ል​ጣ​ለች።


የማ​ያ​ስ​ተ​ውሉ፥ ዝን​ጉ​ዎች፥ ፍቅ​ርም፥ ምሕ​ረ​ትም የሌ​ላ​ቸው ናቸው።


በክ​ር​ስ​ቶስ ፍቅር ሁላ​ች​ሁን እን​ደ​ም​ወ​ዳ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ምስ​ክሬ ነው።


አሁ​ንም በክ​ር​ስ​ቶስ ደስታ፥ ወይም በፍ​ቅር የልብ መጽ​ና​ናት፥ ወይም የመ​ን​ፈስ አን​ድ​ነት፥ ወይም ማዘ​ንና መራ​ራ​ትም በእ​ና​ንተ ዘንድ ካለ፦


ፍቅር የሌላቸው፥ ዕርቅን የማይሰሙ፥ ሐሜተኞች፥ ራሳቸውን የማይገዙ፥ ጨካኞች፥ መልካም የሆነውን የማይወዱ፥


ነገር ግን የዚህ ዓለም ገንዘብ ያለው፥ ወንድሙም የሚያስፈልገው ሲያጣ አይቶ ያልራራለት ማንም ቢሆን፥ የእግዚአብሔር ፍቅር በእርሱ እንዴት ይኖራል?


跟着我们:

广告


广告