Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ነገሥት 22:30 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

30 የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ንጉሥ የይ​ሁ​ዳን ንጉሥ ኢዮ​ሣ​ፍ​ጥን፥ “ልብ​ሴን ለውጬ ወደ ሰልፍ እገ​ባ​ለሁ፤ አንተ ግን የእ​ኔን ልብስ ልበስ” አለው። የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ንጉሥ ልብ​ሱን ለውጦ ወደ ሰልፍ ገባ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

30 የእስራኤልም ንጉሥ ኢዮሣፍጥን፣ “እኔ ልብሴን ለውጬ ወደ ጦርነቱ እገባለሁ፤ አንተ ግን ልብሰ መንግሥትህን ልበስ” አለው። ስለዚህ የእስራኤል ንጉሥ ልብሱን ለውጦ ሌላ ሰው መስሎ ወደ ጦርነቱ ገባ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

30 አክዓብም ኢዮሣፍጥን “ወደ ጦርነት ለመሄድ ስንነሣ እኔ ሌላ ሰው መስዬ ለመታየት ሌላ ልብስ እለብሳለሁ፤ አንተ ግን ልብሰ መንግሥትህን ልበስ” አለው፤ ስለዚህ የእስራኤል ንጉሥ አክዓብ ሌላ ልብስ ለብሶ ማንነቱን በመሰወር ዘመተ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

30 አክዓብም ኢዮሣፍጥን “ወደ ጦርነት ለመሄድ ስንነሣ እኔ ሌላ ሰው መስዬ ለመታየት ሌላ ልብስ እለብሳለሁ፤ አንተ ግን ልብሰ መንግሥትህን ልበስ” አለው፤ ስለዚህ የእስራኤል ንጉሥ አክዓብ ሌላ ልብስ ለብሶ ማንነቱን በመሰወር ዘመተ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

30 የእስራኤልም ንጉሥ ኢዮሣፍጥን “ልብሴን ለውጬ ወደ ሰልፍ እገባለሁ፤ አንተ ግን ልብስህን ልበስ፤” አለው። የእስራኤልም ንጉሥ ልብሱን ለውጦ ወደ ሰልፍ ገባ።

参见章节 复制




1 ነገሥት 22:30
10 交叉引用  

ኢዮ​አ​ብም ወደ ቴቁሔ ልኮ ከዚያ ብል​ሃ​ተኛ ሴት አስ​መ​ጣና፥ “አል​ቅሺ፤ የኀ​ዘ​ንም ልብስ ልበሺ፤ ዘይ​ትም አት​ቀቢ፤ ስለ ሞተ ሰውም ብዙ ዘመን እን​ደ​ም​ታ​ለ​ቅስ ሴት ሁኚ፤


ኢዮ​ር​ብ​ዓ​ምም ሚስቱ ሐኖ​ንን፥ “ተነሺ፥ ራስ​ሽን ለውጪ የኢ​ዮ​ር​ብ​ዓ​ምም ሚስት እንደ ሆንሽ ማንም አይ​ወቅ፤ ወደ ሴሎም ሂጂ፤ ስለ​ዚ​ህም ሕፃን ከደ​ዌው ይድን እን​ደ​ሆነ ጠይቂ፤ እነሆ፥ በዚህ ሕዝብ ላይ እን​ደ​ም​ነ​ግሥ የነ​ገ​ረኝ ነቢዩ አኪያ በዚያ አለ።


የእ​ስ​ራ​ኤል ንጉሥ አክ​ዓ​ብና የይ​ሁዳ ንጉሥ ኢዮ​ሣ​ፍ​ጥም ከጦር መሣ​ሪ​ያ​ቸው ጋር በሰ​ማ​ርያ በር መግ​ቢያ አጠ​ገብ በአ​ደ​ባ​ባይ በዙ​ፋ​ኖ​ቻ​ቸው ላይ ተቀ​ም​ጠው ነበር፤ ነቢ​ያ​ቱም ሁሉ በፊ​ታ​ቸው ትን​ቢት ተና​ገሩ።


የእ​ስ​ራ​ኤል ንጉ​ሥም ኢዮ​ሣ​ፍ​ጥን፥ “ልብ​ሴን ለውጬ ወደ ጦር​ነት እገ​ባ​ለሁ፤ አንተ ግን የእ​ኔን ልብስ ልበስ” አለው። የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ንጉሥ ልብ​ሱን ለወጠ፤ ወደ ሰል​ፍም ገባ።


ኢዮ​ስ​ያስ ግን ይዋ​ጋው ዘንድ ተጽ​ናና እንጂ ፊቱን ከእ​ርሱ አል​መ​ለ​ሰም፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አፍ የተ​ነ​ገ​ረ​ውን የኒ​ካ​ዑን ቃል አል​ሰ​ማም፤ በመ​ጊ​ዶ​ንም ሸለቆ ይዋጋ ዘንድ መጣ።


እስከ መቼ በነ​ፍሴ ኀዘ​ንን አኖ​ራ​ለሁ? እስከ መቼ ልቤ ሁል​ጊዜ ትጨ​ነ​ቅ​ብ​ኛ​ለች? እስከ መቼ ጠላ​ቶች በላዬ ይታ​በ​ያሉ?


ጥበብና ብርታት፥ ምክርም፥ በኃጥእ ዘንድ የሉም።


ሰው በስ​ውር ቦታ ቢሸ​ሸግ፥ እኔ አላ​የ​ው​ምን? ሰማ​ይ​ንና ምድ​ር​ንስ የሞ​ላሁ እኔ አይ​ደ​ለ​ሁ​ምን? ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


ሳኦ​ልም መል​ኩን ለውጦ፥ ሌላ ልብ​ስም ለብሶ ሄደ፤ ሁለ​ትም ሰዎች ከእ​ርሱ ጋር ነበሩ፤ በሌ​ሊ​ትም ወደ ሴቲቱ መጡ። ሳኦ​ልም፥ “እባ​ክሽ በመ​ና​ፍ​ስት አም​ዋ​ር​ቺ​ልኝ፤ የም​ል​ሽ​ንም አስ​ነ​ሽ​ልኝ” አላት።


跟着我们:

广告


广告