Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ነገሥት 22:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 እር​ሱም አለ፥ “እን​ዲህ አይ​ደ​ለም፤ እስ​ራ​ኤል ሁሉ ጠባቂ እን​ደ​ሌ​ላ​ቸው በጎች በተ​ራ​ሮች ላይ ተበ​ት​ነው አየሁ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አለ፦ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የእ​ነ​ዚህ አም​ላክ አይ​ደ​ለ​ምን? እያ​ን​ዳ​ንዱ በሰ​ላም ወደ ቤቱ ይመ​ለስ።”

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 ከዚያም ሚክያስ፣ “እስራኤል ሁሉ እረኛ እንደሌላቸው በጎች በተራሮች ላይ ተበታትነው አየሁ፤ እግዚአብሔርም፣ ‘እነዚህ ሰዎች ጌታ የላቸውም፤ እያንዳንዱም በሰላም ወደየቤቱ ይመለስ’ ብሏል” ሲል መለሰ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 ሚክያስም “መላው የእስራኤል ሠራዊት ጠባቂ እንደሌላቸው በጎች በኮረብታዎች ላይ ተበታትነው አያለሁ፤ ጌታም ‘እነዚህ ሰዎች መሪ የላቸውም፤ ስለዚህ ወደየቤታቸው በሰላም ይመለሱ ብሏል’ ሲል መለሰለት።”

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 ሚክያስም “መላው የእስራኤል ሠራዊት ጠባቂ እንደሌላቸው በጎች በኮረብታዎች ላይ ተበታትነው አያለሁ፤ እግዚአብሔርም ‘እነዚህ ሰዎች መሪ የላቸውም፤ ስለዚህ ወደየቤታቸው በሰላም ይመለሱ ብሎአል’ ሲል መለሰለት።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

17 እርሱም “እስራኤል ሁሉ ጠባቂ እንደሌላቸው በጎች በተራሮች ላይ ተበትነው አየሁ፤ እግዚአብሔርም ‘ለእነዚህ ጌታ የላቸውም፤ እያንዳንዱም በሰላም ወደ ቤቱ ይመለስ፤’ አለ፤” ብሎ ተናገረ።

参见章节 复制




1 ነገሥት 22:17
21 交叉引用  

ንጉ​ሡም፥ “በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስም እው​ነት ትነ​ግ​ረኝ ዘንድ ስንት ጊዜ አም​ል​ሃ​ለሁ?” አለው።


የተ​ረ​ፉ​ትም ሁሉ እንደ ተባ​ረረ ሚዳቋ፥ እንደ ባዘነ በግም ይሆ​ናሉ። የሚ​ሰ​በ​ስ​ባ​ቸ​ውም የለም፤ እን​ዲ​ሁም ሰው ሁሉ ወደ ወገኑ ይመ​ለ​ሳል፤ ሁሉም ሰው ወደ ሀገሩ ይሸ​ሻል።


ከጥ​ንት ከእ​ኔና ከአ​ንተ በፊት የነ​በሩ ነቢ​ያት በብዙ ሀገ​ርና በታ​ላ​ላቅ መን​ግ​ሥ​ታት ላይ ስለ ሰል​ፍና ስለ ክፉ ነገር ስለ ቸነ​ፈ​ርም ትን​ቢት ተና​ገሩ።


“እስ​ራ​ኤል የባ​ዘነ በግ ነው፤ አን​በ​ሶች አሳ​ደ​ዱት፤ መጀ​መ​ሪያ የአ​ሦር ንጉሥ በላው፥ በመ​ጨ​ረ​ሻም የባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ናቡ​ከ​ደ​ነ​ፆር አጥ​ን​ቱን ቈረ​ጠ​መው።”


“ሕዝቤ የጠፉ በጎች ሆነ​ዋል፤ እረ​ኞ​ቻ​ቸው አሳ​ቱ​አ​ቸው፤ በተ​ራ​ሮ​ችም ላይ የተ​ቅ​በ​ዘ​በዙ አደ​ረ​ጉ​አ​ቸው፤ ከተ​ራራ ወደ ኮረ​ብታ ዐለፉ፤ በረ​ታ​ቸ​ው​ንም ረሱ።


እኔም አየሁ፤ እነ​ሆም ከሰ​ሜን በኩል ዐውሎ ነፋ​ስና ታላቅ ደመና፥ የሚ​በ​ር​ቅም እሳት መጣ፤ በዙ​ሪ​ያ​ውም ፀዳል ነበረ፤ በመ​ካ​ከ​ልም በእ​ሳቱ ውስጥ የሚ​ብ​ለ​ጨ​ለጭ ነገር ነበረ።


የአሦር ንጉሥ ሆይ፥ እረኞችህ አንቀላፍተዋል፣ መኳንንቶችህም ዐርፈዋል፣ ሕዝብህም በተራሮች ላይ ተበትኖአል፥ የሚሰበስበውም የለም።


ተራፊም ከንቱነትን ተናግረዋልና፥ ምዋርተኞችም ውሸትን አይተዋልና፣ ሕልምንም የሚያዩ በሐሰት ተናግረዋል፥ በከንቱም ያጽናናሉ፣ እረኛም የላቸውምና እንደ በጎች ተቅበዝብዘዋል ተጨንቀውማል።


ሰይፍ ሆይ፥ ባልንጀራዬ በሆነው ሰው በእረኛዬ ላይ ንቃ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፣ እረኛውን ምታ፥ በጎቹም ይበተናሉ፣ እጄንም በታናናሾች ላይ እመልሳለሁ።


በም​ሳ​ሌም ይና​ገር ጀመር፤ እን​ዲ​ህም አለ፥ “የቢ​ዖር ልጅ በለ​ዓም እን​ዲህ ይላል፥ በት​ክ​ክል የሚ​ያይ ሰው እን​ዲህ ይላል፤


“የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል የሚ​ሰማ፥ ሁሉን የሚ​ችል የአ​ም​ላ​ክን ራእይ የሚ​ያይ፥ ተኝቶ ዐይ​ኖቹ የተ​ከ​ፈ​ቱ​ለት እን​ዲህ ይላል፦


በፊ​ታ​ቸው የሚ​ወ​ጣ​ው​ንና የሚ​ገ​ባ​ውን፥ የሚ​ያ​ስ​ወ​ጣ​ቸ​ው​ንና፥ የሚ​ያ​ስ​ገ​ባ​ቸ​ው​ንም፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ማኅ​በር እረኛ እን​ደ​ሌ​ለው መንጋ እን​ዳ​ይ​ሆን።”


ብዙ ሕዝብም ባየ ጊዜ፥ እረኛ እንደ ሌላቸው በጎች ተጨንቀው ተጥለውም ነበርና አዘነላቸው።


ኢየሱስም ወጥቶ ብዙ ሕዝብ አየና እረኛ እንደሌላቸው በጎች ስለ ነበሩ አዘነላቸው፤ ብዙም ነገር ያስተምራቸው ጀመር።


ቀድሞ ነቢ​ዩን ባለ ራእይ ይሉት ነበ​ርና አስ​ቀ​ድሞ በእ​ስ​ራ​ኤል ዘንድ ሰው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ለመ​ጠ​የቅ ሲሄድ፦ ኑ፤ ወደ ባለ ራእይ እን​ሂድ ይል ነበር።”


跟着我们:

广告


广告