Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ነገሥት 21:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 ንጉሡ አክ​ዓ​ብም መልሶ፥ “ጌታዬ ሆይ! አንተ እን​ዳ​ልህ፤ እኔ የአ​ንተ ነኝ፤ ለእ​ኔም የሆ​ነው ሁሉ የአ​ንተ ነው” አለ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 ኢይዝራኤላዊው ናቡቴ፣ “ዐፅመ ርስቴን አልለቅልህም” ስላለው፣ አክዓብ ተበሳጭቶና ተቈጥቶ ወደ ቤቱ ገባ፤ አኵርፎም በዐልጋው ላይ ተኛ፤ ምግብም መብላት ተወ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 የእስራኤልም ንጉሥ መልሶ፦ “ጌታዬ ንጉሥ ሆይ፥ አንተ እንዳልህ ነው፥ እኔ ለእኔም የሆነው ሁሉ የአንተ ነው” አለ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 አክዓብ፥ የእዝራኤላዊው ናቡቴ “ከአባቶቼ የወረስኩትን ለአንተ አልሰጥህም!” ስላለው በንዴት እየተበሳጨ ወደ ቤቱ ገባ፤ ፊቱንም ወደ ግድግዳ አዙሮ በአልጋው ላይ ተጋደመ፤ ምግብ መብላትም አልፈቀደም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 የእስራኤል ንጉሥ መልሶ፦ ጌታዬ ንጉሥ ሆይ፥ አንተ እንዳልህ ነው፤ እኔ ለእኔም የሆነው ሁሉ የአንተ ነው አለ።

参见章节 复制




1 ነገሥት 21:4
21 交叉引用  

አም​ኖ​ንም ከእ​ኅቱ ከት​ዕ​ማር የተ​ነሣ እስ​ከ​ሚ​ታ​መም ድረስ እጅግ ተከዘ፤ ድን​ግ​ልም ነበ​ረ​ችና አን​ዳች ነገር ያደ​ር​ግ​ባት ዘንድ በዐ​ይኑ ፊት ጭንቅ ሆኖ​በት ነበር።


እር​ሱም፥ “የን​ጉሥ ልጅ ሆይ፥ ስለ​ምን በየ​ቀኑ እን​ዲህ ከሳህ? አት​ነ​ግ​ረ​ኝ​ምን?” አለው። አም​ኖ​ንም፥ “የወ​ን​ድ​ሜን የአ​ቤ​ሴ​ሎ​ምን እኅት ትዕ​ማ​ርን እወ​ድ​ዳ​ታ​ለሁ” አለው።


የሶ​ር​ያም ንጉሥ ወልደ አዴር ሠራ​ዊ​ቱን ሁሉ ሰበ​ሰበ፤ ወጥ​ቶም ሰማ​ር​ያን ከበ​ባት፤ እየ​ጠ​በ​ቃ​ቸ​ውም ተቀ​መጠ። ከእ​ር​ሱም ጋር ሠላሳ ሁለት ነገ​ሥ​ታት ነበሩ፤ ፈረ​ሶ​ችና ሰረ​ገ​ሎ​ችም ነበሩ፤ ወጥ​ተ​ውም ሰማ​ር​ያን ከበ​ቧት፥ ወጓ​ትም።


“ወልደ አዴር እን​ዲህ ይላል፦ ብር​ህና ወር​ቅህ የእኔ ነው፤ ሚስ​ቶ​ች​ህና ልጆ​ች​ህም የእኔ ናቸው።”


ደግ​ሞም መል​እ​ክ​ተ​ኞች ተመ​ል​ሰው መጥ​ተው እን​ዲህ አሉት፥ “ወልደ አዴር እን​ዲህ ይላል፦ ቀድ​መህ ብር​ህ​ንና ወር​ቅ​ህን፥ ሚስ​ቶ​ች​ህ​ንና ልጆ​ች​ህ​ንም ላክ​ልኝ ብዬ ልኬ​ብህ ነበር፤


ሰነ​ፉን ሰው ቍጣ ይገ​ድ​ለ​ዋ​ልና፥ ቅን​ዓ​ትም ሰነ​ፉን ያጠ​ፋ​ዋል።


በዐ​ይን ማየት በነ​ፍስ ከመ​ቅ​በ​ዝ​በዝ ይሻ​ላል፥ ይህ ደግሞ ከንቱ ነው፥ ነፋ​ስ​ንም እንደ መከ​ተል ነው።


ዮና​ስም ፈጽሞ አዘነ፤ ተከ​ዘም።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ዮና​ስን፥ “ፈጽ​መህ ታዝ​ና​ለ​ህን?” አለው።


ፀሐ​ይም በወ​ጣች ጊዜ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትኩስ የም​ሥ​ራቅ ነፋ​ስን አዘዘ፤ ዮና​ስ​ንም እስ​ኪ​ዝል ድረስ ፀሐይ ራሱን መታው፤ ለራ​ሱም ተስፋ ቈርጦ፥ “ከሕ​ይ​ወት ሞት ይሻ​ለ​ኛል” አለ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ዮና​ስን፥ “በውኑ ስለ​ዚች ቅል ታዝ​ና​ለ​ህን?” አለው። እር​ሱም፥ “እስ​ክ​ሞት ድረስ እጅግ አዝ​ኛ​ለሁ” አለ።


ለሰ​ይ​ጣ​ንም መን​ገ​ድን አት​ስ​ጡት።


ነገር ግን እያንዳንዱ በራሱ ምኞት ሲሳብና ሲታለል ይፈተናል።


እርሱ ግን፥ “አል​በ​ላም” ብሎ እንቢ አለ፤ ነገር ግን ብላ​ቴ​ኖ​ቹና ሴቲቱ አስ​ገ​ደ​ዱት፤ ቃላ​ቸ​ው​ንም ሰማ፤ ከም​ድ​ርም ተነ​ሥቶ በአ​ልጋ ላይ ተቀ​መጠ።


跟着我们:

广告


广告