Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ነገሥት 21:29 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

29 እነ​ዚ​ህም በእ​ነ​ዚያ ትይዩ ሰባት ቀን ያህል ሰፈሩ፤ በሰ​ባ​ተ​ኛ​ውም ቀን ተጋ​ጠሙ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ከሶ​ር​ያ​ው​ያን በአ​ንድ ቀን መቶ ሺህ እግ​ረኛ ገደሉ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

29 “አክዓብ ራሱን በፊቴ እንዴት እንዳዋረደ አየህን? ራሱን ስላዋረደ ይህን መከራ በዘመኑ አላመጣበትም፤ ነገር ግን ይህን በቤቱ ላይ የማመጣው በልጁ ዘመን ነው።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

29 እነዚህም በእነዚያ ትይዩ ሰባት ቀን ያህል ሰፈሩ፤ በሰባተኛውም ቀን ተጋጠሙ፤ የእስራኤልም ልጆች ከሶርያውያን በአንድ ቀን መቶ ሺህ እግረኛ ገደሉ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

29 “አክዓብ በእኔ ፊት ራሱን እንዴት እንዳዋረደ ተመልክተሃልን? ይህን ስላደረገ በሕይወቱ ሳለ መቅሠፍትን አላመጣበትም፤ የተባለውን መቅሠፍት በአክዓብ ቤተሰብ ላይ የማመጣው በልጁ የሕይወት ዘመን ይሆናል።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

29 እነዚህም በእነዚያ ትይዩ ሰባት ቀን ያህል ሰፈሩ፤ በሰባተኛውም ቀን ተጋጠሙ፥ የእስራኤልም ልጆች ከሶርያውያን በአንድ ቀን መቶ ሺህ እግረኛ ገደሉ።

参见章节 复制




1 ነገሥት 21:29
27 交叉引用  

ነገር ግን ከል​ጅህ እጅ እከ​ፍ​ለ​ዋ​ለሁ እንጂ ስለ አባ​ትህ ስለ ዳዊት ይህን በዘ​መ​ንህ አላ​ደ​ር​ግም።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሰው መጥቶ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ንጉሥ፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ሶር​ያ​ው​ያን፦ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ራ​ሮች አም​ላክ ነው እንጂ የሸ​ለቆ አም​ላክ አይ​ደ​ለም ብለ​ዋ​ልና ይህን ታላቅ ሠራ​ዊት ሁሉ በእ​ጅህ አሳ​ልፌ እሰ​ጠ​ዋ​ለሁ፤ እኔም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ታው​ቃ​ለህ” አለው።


በሰ​ማ​ር​ያም ሦስት ዓመት ተቀ​መጠ፤ በሶ​ር​ያና በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም መካ​ከል ጦር​ነት አል​ነ​በ​ረም።


ለአ​ክ​አ​ብም በሰ​ማ​ርያ ሰባ ልጆች ነበ​ሩት፤ ኢዩም ደብ​ዳቤ ጽፎ፥ የአ​ክ​አ​ብን ልጆች ለሚ​ያ​ሳ​ድጉ፥ ለሰ​ማ​ርያ አለ​ቆ​ችና ሽማ​ግ​ሌ​ዎች ወደ ሰማ​ርያ ላከ።


ኢዩም ከአ​ክ​አብ ቤት በኢ​ይ​ዝ​ራ​ኤል የቀ​ረ​ውን ሁሉ፥ ታላ​ላ​ቆ​ቹ​ንም ሁሉ፥ ወዳ​ጆ​ቹ​ንና ካህ​ና​ቱን ሁሉ ገደ​ላ​ቸው፤ ከእ​ነ​ርሱ አን​ድስ እንኳ አላ​ስ​ቀ​ረም።


ልብ​ህን አላ​ደ​ነ​ደ​ን​ህ​ምና፥ እነ​ር​ሱም ለጥ​ፋ​ትና ለመ​ር​ገም እን​ዲ​ሆኑ በዚህ ስፍ​ራና በሚ​ኖ​ሩ​በት ላይ የተ​ና​ገ​ር​ሁ​ትን ሰም​ተህ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ተዋ​ር​ደ​ሃ​ልና፥ ልብ​ስ​ህን ቀድ​ደ​ሃ​ልና፥ በፊ​ቴም አል​ቅ​ሰ​ሃ​ልና እኔ ደግሞ ሰም​ቼ​ሃ​ለሁ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


ኢዩም በእጁ ቀስ​ቱን ለጠጠ፤ ኢዮ​ራ​ም​ንም በጫ​ን​ቃው መካ​ከል ወጋው ፤ ፍላ​ጻ​ውም በልቡ አለፈ፤ ወደ ሰረ​ገ​ላ​ውም ውስጥ በጕ​ል​በቱ ላይ ወደቀ።


እር​ሱም፥ “ወደ ታች ወር​ው​ሩ​አት” አላ​ቸው፤ ወረ​ወ​ሩ​አ​ትም፥ ደም​ዋም በግ​ን​ቡና በፈ​ረ​ሶች መግ​ሪያ ላይ ተረጨ፥ ረገ​ጡ​አ​ትም።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እንደ ተመ​ለ​ሱና እንደ ተፀ​ፀቱ ባየ ጊዜ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል፥ “ከተ​መ​ለሱ አላ​ጠ​ፋ​ቸ​ውም፤ ከጥ​ቂት ቀንም በኋላ አድ​ና​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ቍጣ​ዬም በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ላይ አይ​ፈ​ስ​ስም” ሲል ወደ ሰማያ መጣ።


አቤቱ፥ አሕ​ዛብ ያመ​ሰ​ግ​ኑ​ሃል፥ አሕ​ዛብ ሁሉ ያመ​ሰ​ግ​ኑ​ሃል። አሕ​ዛብ ደስ ይላ​ቸ​ዋል፥ ሐሤ​ትም ያደ​ር​ጋሉ።


ሙሴና አሮ​ንም ወደ ፈር​ዖን ገቡ፤ አሉ​ትም፥ “የዕ​ብ​ራ​ው​ያን አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እኔን ማፈ​ርን እስከ መቼ እንቢ ትላ​ለህ? ያመ​ል​ኩኝ ዘንድ ሕዝ​ቤን ልቀቅ።


አት​ስ​ገ​ድ​ላ​ቸው፤ አታ​ም​ል​ካ​ቸ​ውም፤ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ክህ ቀና​ተኛ አም​ላክ ነኝና። በሚ​ጠ​ሉኝ እስከ ሦስ​ተ​ኛና አራ​ተኛ ትው​ልድ ድረስ የአ​ባ​ቶ​ችን ኀጢ​አት በል​ጆች ላይ የማ​መጣ፤


ይህ ሁሉ የእጄ ሥራ ነው፤ ይህም ሁሉ የእኔ ነው፥” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ “ወደ የዋ​ሁና ወደ ጸጥ​ተ​ኛው፥ ከቃ​ሌም የተ​ነሣ ወደ​ሚ​ን​ቀ​ጠ​ቀጥ ሰው ከአ​ል​ሆነ በቀር ወደ ማን እመ​ለ​ከ​ታ​ለሁ?


በቃሉ የም​ት​ን​ቀ​ጠ​ቀጡ ሆይ፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ስሙ፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስም ይከ​ብር ዘንድ፦ ደስ​ታ​ች​ሁም ይገ​ለጥ ዘንድ፥ እነ​ር​ሱም ያፍሩ ዘንድ የሚ​ጠ​ሏ​ች​ሁ​ንና የሚ​ጸ​የ​ፉ​አ​ች​ሁን ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን በሏ​ቸው።


እነ​ር​ሱስ በይ​ሁዳ ከተ​ሞች ውስ​ጥና በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም መን​ገ​ዶች የሚ​ያ​ደ​ር​ጉ​ትን አታ​ይ​ምን?


እግዚአብሔርም ከክፉ መንገዳቸው እንደተመለሱ ሥራቸውን አየ፤ እግዚአብሔርም ያደርግባቸው ዘንድ ከተናገረው ክፉ ነገር ተመለሰ፤ አላደረገውምም።


በደልን ይቅር የሚል፥ የርስቱንም ቅሬታ ዓመፅ የሚያሳልፍ እንደ አንተ ያለ አምላክ ማን ነው? ምሕረትን ይወድዳልና ቍጣውን ለዘላለም አይጠብቅም።


ወደ ሴቲ​ቱም ዘወር ብሎ ስም​ዖ​ንን እን​ዲህ አለው፥ “ይህ​ቺን ሴት ታያ​ታ​ለ​ህን? እኔ ወደ ቤትህ ገባሁ፤ ለእ​ግ​ሮች ውኃ ስንኳ አል​ሰ​ጠ​ኸ​ኝም፤ እር​ስዋ ግን አል​ቅሳ በእ​ን​ባዋ እግ​ሬን አራ​ሰች፤ በጠ​ጕ​ር​ዋም አበ​ሰች።


ወይስ በቸ​ር​ነቱ ብዛት በመ​ታ​ገሡ፥ ለአ​ን​ተም እሺ በማ​ለቱ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አላ​ዋቂ ልታ​ደ​ር​ገው ታስ​ባ​ለ​ህን? የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርስ ቸር​ነቱ አን​ተን ወደ ንስሓ እን​ዲ​መ​ል​ስህ አታ​ው​ቅ​ምን?


ለአንዳንዶች የሚዘገይ እንደሚመስላቸው ጌታ ስለ ተስፋ ቃሉ አይዘገይም፤ ነገር ግን ሁሉ ወደ ንስሓ እንዲደርሱ እንጂ ማንም እንዳይጠፋ ወዶ ስለ እናንተ ይታገሣል።


跟着我们:

广告


广告