1 ነገሥት 21:27 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)27 የእስራኤልም ልጆች ተቈጠሩ፤ ሊገጥሙአቸውም ወጡ፤ የእስራኤልም ልጆች እንደ ሁለት ትናንሽ የፍየል መንጋዎች ሆነው በፊታቸው ሰፈሩ፤ ሶርያውያን ግን ምድርን ሞልተዋት ነበር። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም27 አክዓብም ይህን ቃል ሲሰማ ልብሱን ቀደደ፤ ማቅ ለብሶ፤ ጾመ፤ በማቅ ላይ ተኛ በሐዘን ኵርምት ብሎም ይሄድ ነበር። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)27 የእስራኤልም ልጆች ተሰለፉ፥ ሊገጥሙአቸውም ወጡ፥ የእስራኤልም ልጆች እንደ ሁለት ትናንሾች የፍየል መንጋዎች ሆነው በፊታቸው ሰፈሩ፥ ሶርያውያን ግን ምድሩን ሞልተው ነበር። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም27 ኤልያስ ንግግሩን ከፈጸመ በኋላ አክዓብ ልብሱን በመቅደድና አውልቆ በመጣል ማቅ ለበሰ፤ እህል መቅመስንም እምቢ አለ፤ ማቁንም እንደ ለበሰ ይተኛ ነበር፤ ሲሄድም ከጭንቀቱ ብዛት የተነሣ ፊቱ ጠቊሮ ይታይ ነበር። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)27 የእስራኤልም ልጆች ተሰለፉ፥ ሊገጥሙአቸውም ወጡ፤ የእስራኤልም ልጆች እንደ ሁለት ትናንሾች የፍየል መንጋዎች ሆነው በፊታቸው ሰፈሩ፤ ሶርያውያን ግን ምድሩን ሞልተው ነበር። 参见章节 |