Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ነገሥት 21:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

19 እነ​ዚ​ህም የአ​ው​ራ​ጃ​ዎች አለ​ቆች ጐል​ማ​ሶች ከከ​ተ​ማ​ዪቱ ወጡ፤ ሠራ​ዊ​ትም ተከ​ተ​ላ​ቸው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 እንዲህም በለው፤ ‘እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ሰውየውን ገደልኸው፤ ደግሞ ርስቱን ልትወስድ?’ ከዚያም እንዲህ በለው፤ ‘እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ውሾች የናቡቴን ደም በላሱበት ቦታ የአንተንም ደም ውሾች እንዲሁ ይልሱታል!’ ”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

19 እነዚህም የአውራጆች አለቆች ጉልማሶች ከከተማይቱ ወጡ፤ ሠራዊትም ተከተላቸው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

19 እኔ እግዚአብሔር ስለ እርሱ የምለው ይህ ነው ‘ናቡቴን መግደልህ አንሶህ ሀብቱንም ልትወርስበት ነውን?’ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘ውሾች የናቡቴን ደም በላሱበት ስፍራ እንዲሁም የአንተን ደም ይልሱታል!’ ”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

19 እነዚህም የአውራጆች አለቆች ጕልማሶች ከከተማይቱ ወጡ፥ ሠራዊትም ተከተላቸው።

参见章节 复制




1 ነገሥት 21:19
23 交叉引用  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አለው፥ “ዕራ​ቁ​ት​ህን እን​ደ​ሆ​ንህ ማን ነገ​ረህ? ከእ​ርሱ እን​ዳ​ት​በላ ካዘ​ዝ​ሁህ ዛፍ በውኑ በላ​ህን?”


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እነሆ ከቤ​ትህ ክፉ ነገ​ርን አስ​ነ​ሣ​ብ​ሃ​ለሁ፤ ሚስ​ቶ​ች​ህ​ንም በዐ​ይ​ኖ​ችህ እያ​የህ እወ​ስ​ዳ​ለሁ፤ ለዘ​መ​ድ​ህም እሰ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ በዚ​ችም ፀሐይ ፊት ከሚ​ስ​ቶ​ችህ ጋር ይተ​ኛል።


አሁ​ንስ በፊቱ ክፉ ትሠራ ዘንድ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ነገር ለምን አቃ​ለ​ልህ? ኬጤ​ያ​ዊ​ውን ኦር​ዮን በሰ​ይፍ መት​ተ​ሃል፤ ሚስ​ቱ​ንም ለአ​ንተ ሚስት ትሆን ዘንድ ወስ​ደ​ሃል፤ እር​ሱ​ንም በአ​ሞን ልጆች ሰይፍ ገድ​ለ​ሃል።


ሰረ​ገ​ላ​ው​ንም በሰ​ማ​ርያ ምንጭ አጠ​ቡት። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በነ​ቢዩ አድሮ እንደ ተና​ገረ ውሾ​ችና ጅቦች ደሙን ላሱት። አመ​ን​ዝ​ሮች ሴቶ​ችም በደሙ ታጠ​ቡ​በት።


እነሆ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በአ​ክ​አብ ቤት ላይ ከተ​ና​ገ​ረው ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል በም​ድር ላይ አን​ዳች እን​ዳ​ይ​ወ​ድቅ አሁን ዕወቁ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በባ​ሪ​ያው በኤ​ል​ያስ ቃል የተ​ና​ገ​ረ​ውን አድ​ር​ጎ​አል” አላ​ቸው።


ደብ​ዳ​ቤ​ውም በደ​ረ​ሳ​ቸው ጊዜ የሀ​ገሩ ሰዎች የን​ጉ​ሡን ልጆች ሰባ​ውን ሰዎች ይዘው ገደ​ሉ​አ​ቸው፤ ራሳ​ቸ​ው​ንም በቅ​ር​ጫት አድ​ር​ገው ወደ እርሱ ወደ ኢይ​ዝ​ራ​ኤል ላኩ።


ኤል​ሳዕ ግን በቤቱ ተቀ​ምጦ ነበር፤ ሽማ​ግ​ሌ​ዎ​ችም ከእ​ርሱ ጋር ተቀ​ም​ጠው ነበር፤ ንጉ​ሡም በፊቱ ከሚ​ቆ​ሙት አንድ ሰው ላከ፤ መል​እ​ክ​ተ​ኛ​ውም ገና ሳይ​ደ​ርስ ለሽ​ማ​ግ​ሌ​ዎች፥ “ይህ የነ​ፍሰ ገዳይ ልጅ ራሴን ይቈ​ርጥ ዘንድ እንደ ላከ እዩ፤ መል​እ​ክ​ተ​ኛ​ውም በመጣ ጊዜ ደጁን ዘግ​ታ​ችሁ ከል​ክ​ሉት፤ በደ​ጅም ይቆም ዘንድ ተዉት፤ የጌ​ታው የእ​ግሩ ኮቴ በኋ​ላው ነው” አላ​ቸው።


ፍሬ​ዋን ለብ​ቻዬ ያለ ዋጋ በልቼ እንደ ሆነ፥ ባለ መሬ​ቱ​ንም አባ​ርሬ ነፍ​ሱን አሳ​ዝኜ እንደ ሆነ፥


ዐይ​ኖ​ቻ​ቸው እን​ዳ​ያዩ ይጨ​ልሙ፥ ጀር​ባ​ቸ​ውም ዘወ​ትር ይጉ​በጥ።


አቤቱ፥ ይቅር በለኝ፥ ጠላ​ቶቼም የሚ​ያ​መ​ጡ​ብ​ኝን መከራ እይ፥ ከሞት ደጆች ከፍ ከፍ የሚ​ያ​ደ​ር​ገኝ፤


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፍር​ድን ማድ​ረግ ያው​ቃል፤ ኀጢ​አ​ተ​ኛው በእ​ጆቹ ሥራ ተጠ​መደ።


ነቢዩ ኤር​ም​ያ​ስም ይህን ቃል ሁሉ ለይ​ሁዳ ንጉሥ ለሴ​ዴ​ቅ​ያስ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ነገ​ረው።


አለ​ቃ​ውም ሕዝ​ቡን ከይ​ዞ​ታ​ቸው ያወ​ጣ​ቸው ዘንድ ከር​ስ​ታ​ቸው በግድ አይ​ወ​ሰድ፤ ሕዝቤ ሁሉ ከየ​ይ​ዞ​ታ​ቸው እን​ዳ​ይ​ነ​ቀሉ ከገዛ ይዞ​ታው ለል​ጆቹ ርስ​ትን ይስጥ።”


ከተማን በደም ለሚሠራ፥ ከተማንም በኃጢአት ለሚመሠርት ወዮለት!


ከክፉ እንዲድን ጐጆውን በከፍታ ላይ ያደርግ ዘንድ ለቤቱ ክፉ ትርፍን ለሚሰበስብ ወዮለት!


አዶ​ኒ​ቤ​ዜ​ቅም፥ “የእ​ጆ​ቻ​ቸ​ውና የእ​ግ​ሮ​ቻ​ቸው አውራ ጣቶች የተ​ቈ​ረጡ ሰባ ነገ​ሥ​ታት ከገ​በ​ታዬ በታች ፍር​ፋሪ ይለ​ቅሙ ነበሩ፤ እኔ እን​ዳ​ደ​ረ​ግሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲሁ መለ​ሰ​ልኝ” አለ። ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ወሰ​ዱት፥ በዚ​ያም ሞተ።


跟着我们:

广告


广告