1 ነገሥት 20:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)6 እርሱም፥ “ኢይዝራኤላዊውን ናቡቴን፦ የወይንህን ቦታ በገንዘብ ስጠኝ፤ ወይም ብትወድድ በፋንታው ሌላ የወይን ቦታ እሰጥሃለሁ ብዬ ተናገርሁት፤ እርሱ ግን የአባቶቼን ርስት አልሰጥህም ስለ አለኝ ነው” አላት። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም6 ሆኖም ነገ በዚሁ ጊዜ ቤተ መንግሥትህንና የሹማምትህን ቤቶች እንዲበረብሩ፣ ሹማምቴን እልካቸዋለሁ። እነርሱም ማንኛውንም ለአንተ ዋጋ ያለውን ሁሉ በእጃቸው በማስገባት ይወስዱታል።’ ” 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)6 አሁን ደግሞ ቤተ መንግሥትህንና የባለሥልጣኖችህን ቤት ሁሉ በርብረው ዋጋ ያለውን ንብረት ሁሉ ይዘው እንዲመጡ የጦር መኰንኖቼን እልካለሁ፤ እነርሱም ነገ ጧት በዚሁ ሰዓት እዚያ ይደርሳሉ።” 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም6 አሁን ደግሞ ቤተ መንግሥትህንና የባለሥልጣኖችህን ቤት ሁሉ በርብረው ዋጋ ያለውን ንብረት ሁሉ ይዘው እንዲመጡ የጦር መኰንኖቼን እልካለሁ፤ እነርሱም ነገ ጧት በዚሁ ሰዓት እዚያ ይደርሳሉ።” 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)6 እርሱም “ኢይዝራኤላዊውን ናቡቴን ‘የወይንህን ቦታ በገንዘብ ስጠኝ፤ ወይም ብትወድድ በፋንታው ሌላ የወይን ቦታ እሰጥሃለሁ፤’ ብዬ ተናገርሁት፤ እርሱ ግን ‘የወይን ቦታዬን አልሰጥህም፤’ ብሎ ስለ መለሰልኝ ነው፤” አላት። 参见章节 |