Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ነገሥት 2:27 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

27 በሴ​ሎም በዔሊ ቤት ላይ የተ​ና​ገ​ረው የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ይፈ​ጸም ዘንድ ሰሎ​ሞን አብ​ያ​ታ​ርን ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ክህ​ነት አወ​ጣው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

27 ስለዚህ እግዚአብሔር ስለ ዔሊ ቤት በሴሎ የተናገረውን ቃል ለመፈጸም፣ ሰሎሞን አብያታርን ከእግዚአብሔር ክህነት አስወገደው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

27 ስለዚህ ሰሎሞን አብያታርን የጌታ ካህን ሆኖ ከሚያገለግልበት የክህነት ሥልጣን ሽሮ አባረረው፤ በዚህም ዓይነት ጌታ በሴሎ ስለ ካህኑ ዔሊና ስለ ትውልዱ የተናገረው ቃል ተፈጸመ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

27 ከዚህም በኋላ ሰሎሞን አብያታርን የእግዚአብሔር ካህን ሆኖ ከሚያገለግልበት የክህነት ሥልጣን ሽሮ አባረረው፤ በዚህም ዐይነት እግዚአብሔር በሴሎ ስለ ካህኑ ዔሊና ስለ ትውልዱ የተናገረው ቃል ተፈጸመ።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

27 በሴሎም በዔሊ ቤት ላይ የተናገረው የእግዚአብሔር ቃል ይፈጸም ዘንድ ሰሎሞን አብያታርን ከእግዚአብሔር ክህነት አወጣው።

参见章节 复制




1 ነገሥት 2:27
13 交叉引用  

ንጉ​ሡም በእ​ርሱ ፋንታ የዮ​ዳ​ሄን ልጅ በን​ያ​ስን የሠ​ራ​ዊቱ አለቃ አድ​ርጎ ሾመ፤ መን​ግ​ሥ​ቱም በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ጸናች። በአ​ብ​ያ​ታ​ርም ፋንታ ካህ​ኑን ሳዶ​ቅን ሾመ።


የዮ​ዳ​ሄም ልጅ በን​ያስ የሠ​ራ​ዊት አለቃ ነበረ፤ ሳዶ​ቅና አብ​ያ​ታ​ርም ካህ​ናት ነበሩ፤


ነገር ግን ይህ ሁሉ የሆነ የነቢያት መጻሕፍት ይፈጸሙ ዘንድ ነው፤” አለ። በዚያን ጊዜ ደቀ መዛሙርቱ ሁሉ ትተውት ሸሹ።


“አቤቱ፥ ምስ​ክ​ር​ነ​ታ​ች​ንን ማን ያም​ነ​ናል? የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርስ ክንድ ለማን ተገ​ለጠ?” ያለው የነ​ቢዩ የኢ​ሳ​ይ​ያስ ቃል ይደ​ርስ ዘንድ።


እርስ በር​ሳ​ቸ​ውም፥ “ዕጣ እን​ጣ​ጣ​ልና ለደ​ረሰ ይድ​ረ​ሰው እንጂ አን​ቅ​ደ​ደው ተባ​ባሉ፤” ይህም “ልብ​ሶ​ችን ለራ​ሳ​ቸው ተካ​ፈሉ፤ በቀ​ሚ​ሴም ላይ ዕጣ ተጣ​ጣሉ” ያለው የመ​ጽ​ሐፍ ቃል ይፈ​ጸም ዘንድ ነው፤ ጭፍ​ሮ​ችም እን​ዲሁ አደ​ረጉ።


ከዚ​ህም በኋላ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ሁሉ እንደ ተፈ​ጸመ ባየ ጊዜ የመ​ጽ​ሐፉ ቃል ይፈ​ጸም ዘንድ “ተጠ​ማሁ” አለ።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ማኅ​በር ሁሉ በሴሎ ተሰ​በ​ሰቡ፤ በዚ​ያም የም​ስ​ክ​ሩን ድን​ኳን ተከሉ፤ ምድ​ሩም ጸጥ ብሎ ተገ​ዛ​ላ​ቸው።


ከአ​ኪ​ጦ​ብም ልጅ ከአ​ቤ​ሜ​ሌክ ልጆች ስሙ አብ​ያ​ታር የሚ​ባል አንዱ ልጅ አም​ልጦ ሸሸ፤ ዳዊ​ት​ንም ተከ​ተለ።


跟着我们:

广告


广告