Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ነገሥት 19:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 ኤል​ያ​ስም ያን በሰማ ጊዜ ፊቱን በመ​ጐ​ና​ጸ​ፊ​ያው ሸፈነ፤ ወጥ​ቶም በዋ​ሻው ደጃፍ ቆመ። እነ​ሆም፥ “ኤል​ያስ ሆይ፥ ወደ​ዚህ ለምን መጣህ?” የሚል ቃል ወደ እርሱ መጣ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 ኤልያስም ይህን ሲሰማ፣ ፊቱን በመጐናጸፊያው ሸፍኖ ወጣና በዋሻው ደጃፍ ቆመ። ከዚያም፣ “ኤልያስ ሆይ፤ እዚህ ምን ታደርጋለህ?” የሚል ድምፅ ሰማ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 ኤልያስ የሹክሹክታውን ድምፅ በሰማ ጊዜ ፊቱን በመጐናጸፊያው ሸፈነ፤ ወጥቶም በዋሻው መግቢያ በር አጠገብ ቆመ፤ አንድ ድምፅም “ኤልያስ ሆይ! እዚህ ምን ታደርጋለህ?” ሲል ጠየቀው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 ኤልያስ የሹክሹክታውን ድምፅ በሰማ ጊዜ ፊቱን በመጐናጸፊያው ሸፈነ፤ ወጥቶም በዋሻው መግቢያ በር አጠገብ ቆመ፤ አንድ ድምፅም “ኤልያስ ሆይ! እዚህ ምን ታደርጋለህ?” ሲል ጠየቀው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 ኤልያስም ያን በሰማ ጊዜ ፊቱን በመጎናጸፊያው ሸፈነ፤ ወጥቶም በዋሻው ደጃፍ ቆመ። እነሆ “ኤልያስ ሆይ! በዚህ ምን ታደርጋለህ?” የሚል ድምፅ ወደ እርሱ መጣ።

参见章节 复制




1 ነገሥት 19:13
11 交叉引用  

የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መል​አክ፥ “የሦራ አገ​ል​ጋይ አጋር ሆይ፥ ከወ​ዴት መጣሽ? ወዴ​ትስ ትሄ​ጂ​ያ​ለሽ?” አላት። እር​ስ​ዋም፥ “እኔ ከእ​መ​ቤቴ ከሦራ ፊት እኰ​በ​ል​ላ​ለሁ” አለች።


አክ​ዓ​ብም ሊበ​ላና ሊጠጣ ወጣ። ኤል​ያ​ስም ወደ ቀር​ሜ​ሎስ አናት ወጣ፤ ፊቱ​ንም በጕ​ል​በቱ መካ​ከል አቀ​ር​ቅሮ በግ​ን​ባሩ ወደ ምድር ተደፋ።


እዚ​ያም ወዳለ ዋሻ ገባ፤ በዚ​ያም አደረ፤ እነ​ሆም፥ “ኤል​ያስ ሆይ! ምን አመ​ጣህ?” የሚል የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ወደ እርሱ መጣ።


ኤል​ያ​ስም መጠ​ም​ጠ​ሚ​ያ​ውን ወስዶ ጠቀ​ለ​ለው፤ የዮ​ር​ዳ​ኖ​ስ​ንም ውኃ መታ​በት፤ ውኃ​ውም ወዲ​ህና ወዲያ ተከ​ፈለ፤ ሁለ​ቱም በደ​ረቅ ተሻ​ገሩ። ወጥ​ተ​ውም በም​ድረ በዳው ቆሙ።


እስከ አል​ፍም ድረስ እጄን በላ​ይህ እጋ​ር​ዳ​ለሁ፤ እጄ​ንም ፈቀቅ አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ በዚያ ጊዜ ጀር​ባ​ዬን ታያ​ለህ፤ ፊቴ ግን ለአ​ንተ አይ​ታ​ይም።”


ሱራ​ፌ​ልም በዙ​ሪ​ያው ቆመው ነበር፤ ለእ​ያ​ን​ዳ​ን​ዱም ስድ​ስት ክንፍ ነበ​ረው፤ በሁ​ለቱ ክን​ፎ​ቻ​ቸው ፊታ​ቸ​ውን ይሸ​ፍኑ ነበር፤ በሁ​ለ​ቱም ክን​ፎ​ቻ​ቸው እግ​ሮ​ቻ​ቸ​ውን ይሸ​ፍኑ ነበር፤ በሁ​ለ​ቱም ክን​ፎ​ቻ​ቸው ይበ​ርሩ ነበር።


እኔም፥ “ከን​ፈ​ሮች የረ​ከ​ሱ​ብኝ ሰው በመ​ሆኔ፥ ከን​ፈ​ሮ​ቻ​ቸው በረ​ከ​ሱ​ባ​ቸው ሕዝብ መካ​ከል በመ​ቀ​መጤ ዐይ​ኖች የሠ​ራ​ዊ​ትን ጌታ ንጉ​ሡን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ስለ አዩ ጠፍ​ቻ​ለ​ሁና ወዮ​ልኝ!” አልሁ።


ዮና​ስም ከከ​ተ​ማ​ዪቱ ወጣ፤ በከ​ተ​ማ​ዪ​ቱም ፊት ለፊት ተቀ​መጠ፤ በከ​ተ​ማ​ዪ​ቱም የሚ​ሆ​ነ​ውን እስ​ኪ​ያይ ድረስ በዚያ ለራሱ ዳስ ሠርቶ ከጥ​ላው በታች ተቀ​መጠ።


በመ​ጋዝ የሰ​ነ​ጠ​ቁ​አ​ቸው፥ በድ​ን​ጋይ የወ​ገ​ሩ​አ​ቸው፥ በሰ​ይ​ፍም ስለት የገ​ደ​ሉ​ዋ​ቸው አሉ፤ ማቅ፥ ምን​ጣ​ፍና የፍ​የል ሌጦ ለብ​ሰው ዞሩ፤ ተጨ​ነቁ፤ ተቸ​ገሩ፤ መከራ ተቀ​በሉ፤ ተራቡ፥ ተጠ​ሙም።


跟着我们:

广告


广告